መቼ ነው? January 26, 2014 05:59 am by Editor 1 Comment መቼ ነው ይሄ ቀን – ከኛ ቤት ’ሚያልፈው ለመኖር መደፋት – ተረት የሚሆነው? መቼ ነው ወገኔ – መኖር የሚችለው እንደሰው ለመኖር – ሰውን እሚመስለው? መቼ ነው ረሃቡ – ተረታሁ የሚለው እሳቱ እሳት ሁኖ – ኑሮን ’ሚያበስለው? መቼ ነው ይሄ ቀን – ተረት እሚሆነው መኖር አለመኖር – መሆኑ እሚያከትመው? Share on FacebookTweetFollow us
YeKanadaw Kebede says January 28, 2014 12:48 am at 12:48 am አለቀ የፍዳችንን ማለቂያ ከቀናት አንዱን ቆጥሬ ተስፋ ስንቅ ስለሆነ፤ ‘ነገ’ ለማለት ሞክሬ ዛሬ መሽቶ አልነጋ አለኝ ጊዜም አለቀ መሰለኝ 27012014 Reply
YeKanadaw Kebede says
አለቀ
የፍዳችንን ማለቂያ ከቀናት አንዱን ቆጥሬ
ተስፋ ስንቅ ስለሆነ፤ ‘ነገ’ ለማለት ሞክሬ
ዛሬ መሽቶ አልነጋ አለኝ
ጊዜም አለቀ መሰለኝ
27012014