የጤንነት ሚስጢር
ማንም ህመምተኛ የወሰደው ኪኒን
ያድነኛል ብሎ ከቻለ ለማመን
ስላስተላለፈ ለአዕምሮው መልዕክት
በርግጥም ይችላል ጥሩ ፈውስ ማግኘት
በሰውነትህ ውስጥ ህመም የሚኖረው
በሽታውን ትኩረት ስትሰጠው ብቻ ነው
የጤና መዛባት ስሜት ከተሰማህ
ህመሙን አታስፋ ለሰዎች ተናግረህ
ስዎች ስለህመም ሲያወሩ ማዳመጥ
መንገዱን መክፈት ነው እንዲባባስ ይበልጥ
ህመማቸው ጸንቶ ቢወተውቱ እንኳን
በመልካም ነገሮች ለውጠህ ወሬውን
ባነጋገር ብቃት ትችላለህ ማዳን
የአዕምሮ ፈጠራን የእርጅቻለሁ እምነት
ከራስህ መንጭቀህ ይገባሃል ማውጣት
ወጣት ነኝ አሁንም ብለህ በማተኮር
ደስታን ጤናን ይዘህ ትችላለህ መኖር
ስለዚህ አረጀሁ ብለህ በመጨነቅ
ህመም እያወራህ እድሜህን ከመሰቅ
ራስህ ራስህን በዚህ ዘዴ ጠብቅ
******************************
The Secret (ሚስጢሩ…) ክፍል አንድን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡
The Secret (ሚስጢሩ…) ክፍል ሁለትን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡
The Secret (ሚስጢሩ…) ክፍል ሶስትን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡
The Secret (ሚስጢሩ…) ክፍል አራትን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡
The Secret (ሚስጢሩ…) ክፍል አምስትን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡
The Secret (ሚስጢሩ…) ክፍል ስድስትን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡
Leave a Reply