ጉሮሮህን ጠራርገህ፤ ምላስህን ሳልና
እንደ ሽንኩርት የምልጠው
እንደ ኪኒን የምውጠው
ጥሩ ቃላት ምረጥና
እንደ እበት ሳትለድፍ
እንደ ጭቃ ሳትለጥፍ
ልክ ልኬን ንገረኝ
ደስ ይበልህ…ስደበኝ
ባንተ መለኪያ ተለክቸ
ባንተ መነፀር ታይቸ
ሙሉ እንደማልሆን አውቃለሁ
ባልተገራ ምላስህ
ባዶ በሆነው ራስህ
ማንነቴን ስትናገር፤ ማንነትህን አያለሁ
እና…አንተን ደስ እንዲልህ
የተጫንከው እንዲቀልህ
……………..ስደበኝ
ለአቶ ዓልምነው መኮነን
የአማራ ክልል ም/ፕሬዘዳንትና የብአዴን ፅ/ቤት ኃላፊ
Gize Lekulu says
Tell Him !!Lezih CHIKA
zeynu says
wey zendro drom ke zenbe mar antbkem egna amharawch