
የኢትዮጵያ አትሌቶች በ14ኛው የዓለም አትሌክቲክስ ሻምፒዮን ውድድር አስደናቂ ውጤት አስመዘገበዋል ! አትሌቶቻችን 1 ወርቅ፣ 2 ብር፤ እና 1 ነሃስ ያገኙ ሲሆን እውነትም አረንጓዴው ጎርፍ የሚለውን ስማቸውን አድሰዋል። በውጤቱም በወንዶች ማራቶን ኢትዮጵያውያን፤ 2ኛ ለሌሳ ደሲሳ, 3ኛ ታደሰ ቶላ, 4ኛ ጸጋዬ ከበደ እና 8ኛ የማነ ጸጋዬ የወጡ ሲሆን፤ በሴቶች 5000 ሜትር ሩጫ ደግሞ፤ 1ኛ መሰረት ደፋር፣ 3ኛ አልማዝ አያና 5ኛ ብዙ ድሪባ አሸናፊ ሆነዋል፡፡ በአጠቃላይ በዛሬው እለት ብቻ 1 ወርቅ ፣ 2 ብር እና 1 ነሀስ በድምሩ 4 ሜዳሊያዎችን በመጨመር ኢትዮጵያ ከራሺያ፤ ከአሜሪካ፤ ከጃማይካ እና ከኬንያ በመቀጠል በ6ኛነት በ3 ወርቅ፣ 3 ብር እና 4 ነሀስ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን በማግኝት የኢትዮጵያ ባንዲራ በሞስኮ ስታዲዮም ከፍ ብሎ እንዲወለበለብ ላደርጉት ብርቅዬ አትሌቶቻችን ከፍተኛ ምስጋና ክብርየወገባቸዋል ! እነሆ ባለዎርቅ አትሌቶቻቸን በዘከርኩበት የስንኝ ቋጠሮ መሲ ባንችም ኮራን ያልኩትን ተጋበዙ! (ግጥሙን ለማንበብ እዚያው ግጥሙ ላይ ይጫኑ)
የኢትዮጵያ ሕዝብ እና አትሌቶቻችን እንኳን ደስ አላችሁ!! እንኳን ደስ አለን !!!
Leave a Reply