ለቅሶ ሳቅ – ሳቅ ለቅሶ February 12, 2013 06:35 am by Editor 1 Comment አቅቶን መለወጥ ለቅሶን በደስታ፤ ሃዘን ጠል አልብሶን ሳቅ ደርቦ ኩታ፤ ያንዱን ቤት ገንብቶ የሌላውን ሲያፈርስ፤ አንዱን ሳቅ አጅቦት ሌላው ከፍቶት ሲያለቅስ፤ ለቅሶ ሳቅ – ሳቅ ለቅሶ – እየደባለቀ፤ ግማሽ ጎኑ ሲያለቅስ – ግማሽ ጎኑ ሳቀ:: (ሙሉውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) Share on FacebookTweetFollow us
በለው ! says February 12, 2013 07:41 pm at 7:41 pm ^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^ ሕዝብ ተነሳ አሉ የሚያርፍበትን ሳያሳውቁት አንዳንዱ ታፍኖ ሌላው ከፍቶት ሳቅና ለቅሶ ከቶ መች ለየለት ? የድብልቅልቅ ያለህ ዘመነ ልቅ እያነቡ – እስክስታ አለቅሶ- መሳቅ የደላውም ጠገበ እራበውም ጠማው እዩ.. አስተላለፉን ለቅሶን ሳቅ ሲያጅበው:: በመልካሙ ዘመን ያለው ለሌለው ደረቅ ቡና ይቀርባል ቁርጥ ነው ችግሩን ተናግሮ መፍትሔ መክሮበት እንደ የሥጋ-ዘመድ ለችግር ደራሽ ነው ጎረቤት የልቡን ሚስጥር አውጥቶ አልቅሶ ተጫውቶ የተቸገረ ተረዳድቶ የከፋው ተፅናንቶ ሀሳቡን ያቀላል እንቅልፍ ይወስደዋል ተኝቶ ። ዛሬማ የክልል አጥር የጥርጣሬ መስመር የማፍረስ የማጥፋት አባዜ በሀገር ሲዘወር በቆመበት እንቅልፍ ፣ተቀምጦ ደንዝዞ ዕንባው ቅርር ለመቻል ለመሸፈን አልቅሶ እንደገና ስቆ ማፈር ሳቅና ለቅሶ የአንድ እናት ልጆች ሆነው ሕዝቤን ግራ አጋቡት እየሳቀ እያለቀሰ አሳ’ቀው ትርጉማቸው ተቃራኒ በአገላለጽ ተለያይተው ለምን? እንዴት? ሕዝቤ አጣ የሚረ’ዳው ? እባካችሁ ድረሱለት ህዝብ ከልቡ ነው የሚያለቅሰው!! ። —————————————- በለው!ከሀገረ ካናዳ ከምስጋና ጋር በቸር ይግጠመን>> Reply
በለው ! says
^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^^
ሕዝብ ተነሳ አሉ የሚያርፍበትን ሳያሳውቁት
አንዳንዱ ታፍኖ ሌላው ከፍቶት
ሳቅና ለቅሶ ከቶ መች ለየለት ?
የድብልቅልቅ ያለህ ዘመነ ልቅ
እያነቡ – እስክስታ አለቅሶ- መሳቅ
የደላውም ጠገበ እራበውም ጠማው
እዩ.. አስተላለፉን ለቅሶን ሳቅ ሲያጅበው::
በመልካሙ ዘመን ያለው ለሌለው
ደረቅ ቡና ይቀርባል ቁርጥ ነው
ችግሩን ተናግሮ መፍትሔ መክሮበት
እንደ የሥጋ-ዘመድ ለችግር ደራሽ ነው ጎረቤት
የልቡን ሚስጥር አውጥቶ አልቅሶ ተጫውቶ
የተቸገረ ተረዳድቶ የከፋው ተፅናንቶ
ሀሳቡን ያቀላል እንቅልፍ ይወስደዋል ተኝቶ ።
ዛሬማ የክልል አጥር የጥርጣሬ መስመር
የማፍረስ የማጥፋት አባዜ በሀገር ሲዘወር
በቆመበት እንቅልፍ ፣ተቀምጦ ደንዝዞ ዕንባው ቅርር
ለመቻል ለመሸፈን አልቅሶ እንደገና ስቆ ማፈር
ሳቅና ለቅሶ የአንድ እናት ልጆች ሆነው
ሕዝቤን ግራ አጋቡት እየሳቀ እያለቀሰ አሳ’ቀው
ትርጉማቸው ተቃራኒ በአገላለጽ ተለያይተው
ለምን? እንዴት? ሕዝቤ አጣ የሚረ’ዳው ?
እባካችሁ ድረሱለት ህዝብ ከልቡ ነው የሚያለቅሰው!! ።
—————————————-
በለው!ከሀገረ ካናዳ ከምስጋና ጋር በቸር ይግጠመን>>