• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

መርገምተ ወያኔ

March 15, 2014 03:30 am by Editor 2 Comments

 “በረከተ መርገም” የሚያስፈልግ ቃሉ፣

ዛሬ ነው ተራገም ባለቅኔው ኃይሉ።

ቅኔህን አፍሰው እንደድሮ እንደጥንት፣

ላሁን ዘመን ገዢ ያስፈልጋል መርገምት።

አንተ በርግማንህ የጠበጠብካቸው

እነዛ ሊቃውንት በፍልስፍናቸው

ተወቃሽ በመሆን ቢያተርፉም ክፉ ስም

ለውጥ አስገኝተዋል ላለንባት ዓለም

ነገር ግን ያሁኑ ለስልጣን ለሀብቱ፣

ለስጋ ቁመናው ለሰፊው ቀፈቱ፣

አስሮ ሲያንገላታ ቆይቷል ሲገድል፣

አፍስበት በሱም ከርግማንህ ጠበል፣

ድሮ በሊቆቹ  እርግማን ከጨረስክ፣

ምን ይሰራል ብለህ ወይም መርገም ከተውክ፣

እንዳሻህ በልና  ፍቀድልኝ፣ ለኔ

የርግማን በረከት አለኝ በወያኔ

ካስፈለገም አምጣ ድርሻህን መዋጮ፣

የእኔን ግን ልጀምር ከወያኔው ቁንጮ

ከኢትዮጵያ ምድር ከአብራኳ ወጥተህ፣

አንባሻዋን ገምጠህ ወተቷን ጠጥተህ፣

ፊደል ቆጥረህባት በሜዳዋ ሮጠህ፣

በፍቅር በደስታ በኖርክባት ሀገር፣

ተንኮል ልብህ ቋጥረህ ጠንሰህ ክፉ ሸር፣

ነጻነት ሳታጣ ነጻነት ፍለጋ፣

በጫካ መሽገህ ኖረህ ስትዋጋ፣

እጅህ ስታስገባ ስልጣን ስትጨብጥ፣

አናቷን በመግመስ ህዝቡን በመበጥበጥ፣

እድሜህን በሙሉ የዳከርከው በሸፍጥ፣

የታሪክ ነቀርሳው ጨካኙ አቶ መለስ፣

ነፍስህን ገሀነብ ይቦጭቃት የሎስ።

ከድሮ ጀምሮ በአንክሮ እንዳየነው፣

ግፍ በቃኝ የማይል አበሻ ብቻ ነው።

ቴሌፎን የሰራው እውቁ ግራምቢል፣

አልታየም በጭራሽ ዓለምን ሲበድል።

ሬድዋን የሚሉህ የሁሴን ዲቃላ፣

ሬድዮና ስልክ መገናኛ ሁላ፣

ለወያኔ ውሸት ማከፋፈያ ቃል፣

መጠቀሚያ አድርገህ ህዝብን በማታለል፣

በፈጠጸምከው ጭቦ ነብዩ መሀመድ፣

አፍርጠው ይጣሉህ ያድርጉህ ዶጋ አመድ።

ከድሮ ጀምሮ በአንክሮ እንዳየነው፣

ግፍ በቃኝ የማይል አበሻ ብቻ ነው።

በረከት የሚሉህ በረከት ስምኦን፣

ህዝብ ላይ ሃያ ዓመት በፈጸምከው በደል፣

እምነት ባይኖርህም ህግ እግዜር ባትፈራ፣

አምላክ ተመልክቶ የህዝቡን መከራ፣

መዓት ያውርድብህ ያስቆጥርህ ፍዳ፣

መላ አካልህ አብጦ በመንገድ ላይ ፈንዳ።

የሕወሓት ጥንስሱ ጉምቱው አባይ ፀሐይ፣

ተንኮለኛው መዥገር አንተም ነፍሰ ገዳይ፣

ያልተፈጨ አቡክተህ፣ ያልተቀዳ አቅርበህ፣

ህዝብን እየቀለብክ ውሸት ምግብ አድርገህ፣

ከወጣትነትህ ሽምግልናህ ድረስ፣

በዘር በመለየት አገርን በማፍረስ፣

ለብዙ ዘመናት በፈጸምከው ጭቦ፣

እንደ አክርማ ሁለት ይሰንጥቁህ አቦ።

ከድሮ ጀምሮ በአንክሮ እንዳየነው፣

ግፍ በቃኝ የማይል አበሻ ብቻ ነው።

ባህል ሐይማኖትን አሳጥተህ ዋጋ፣

ሀገርን የጣልከው ለአስከፊ አደጋ፣

ወንበዴ አደራጁ አቦይ ስብሃት ነጋ፣

በሕዝብ እንደቀለድክ የማይቀልድ አምላክ፣

እጅ እግርን  ነስቶ ያስኪድህ በምብርክ።

ውጪ ሀገር ድረስ እንደሰው ተምረህ፣

ማበርከት ስትችል ያቅምህን ለሀገርህ፣

ለጋሲ፣ ራዕይ እያልክ በወያኔ ፈሊጥ፣

ስራህ ያደረከው በህዝብ ማላገጥ፣

ገፊው ኃይለማርያም ዛጎል ዓይንህ ይፍረጥ።

ከድሮ ጀምሮ በአንክሮ እንዳየነው፣

ግፍ በቃኝ የማይል አበሻ ብቻ  ነው።

የጦር አዛዥነት ሳይኖርህ ችሎታው፣

በአመራር ጉድለት ስንቱን ያስጨረስከው፣

ዝፍዝፉ መሃይም እንቅቡ አባዱላ፣

ውርደት ያሸክምህ አፈር ጠኔ ብላ።

እስራ ስትገባ የፓርላማው ሰዓት፣

ተምዘግዝጎ ወድቆ ይከመር ባንተ አናት።

በጅማት የቆምከው ቀፋፊው ሳሞራ፣

በቁም አንጠልጥሎ ይውሰድህ አሞራ።

ምድር ትጠየፍህ አንጥሮጦስ ውረድ፣

በማይታይ እሳት ተቀርቅረህ ንደድ።

ከመጥፎ አመራር ጋር አብረህ በመቆም፣

መቅሰፍት የሆንክባት ለሃገሪቷ ሰላም፣

ዲቃላው አውደልዳይ ቴዎድሮስ አድሃኖም፣

በረከቷን ነስታ ታዋርድህ ይቺ ዓለም።

ደብረጽዮን ያሉህ የማትታይ እባብ፣

ኢትዮጵያን ለማጥፋት ተንኮል ስትሸርብ፣

ህዝብን የሚጠብቅ የዓለም ፈጣሪ፣

ዓይንህን ከልሎ ጥሎህ ያለመሪ፣

ስቃይን መከራን አይተሃት በምድር፣

በቁምህ ሞት ግጦህ ገሃነብ ተቀርቀር።

ከድሮ ጀምሮ በአንክሮ እንዳየነው‹

ግፍ በቃኝ የማይል አበሻ ብቻ ነው።

የተንኮል አጋርህ የሆነው መለስን፣

ተጣብቀህ የኖርከው ክፉው ስዩም መስፍን፣

የሰው ልጆች ህይወት እጅህ ላይ ያለው ደም፣

አእምሮህን ነስቶህ አሳጥቶህ ሰላም፣

ምትይዝ ምትጨብጠው መረጋጋት ነስቶህ፣

ዲያብሎስ አጅቦ ከገደል ይክተትህ።

ህዝብ እየተራበ የናጠጥሽው በሃብት፣

አዜብ መስፍን ያሉሽ የሙስና ልዕልት፣

ድንገት አውርዶብሽ ያልታሰበ አደጋ፣

ጉሮሮሽ ይደፈን ልሳንሽ ይዘጋ።

ከድሮ ጀምሮ በአንክሮ እንዳየነው፣

ግፍ በቃኝ የማይል አበሻ ብቻ ነው።

ከዓለም ዳርቻ መሰሪ ሲጠቀስ፣

ቀድመህ ምትጠራው ጣጤው እንድርያስ፣

ረጋግጦ ጥሎህ የዳቢሎስ ፈረስ፣

ምድር ተንዳብህ ያግባህ አንጥሮጦስ።

በዘር በመፈረጅ እያፈነቃቀልክ፣

ህዝብን ከኖረበት እያነስህ የጣልክ፣

ቀልበቢሱ ፍጡር ቀልማዳው ወጠጤ፣

ቀራፎው መሃይም ሽፈራው ሽጉጤ፣

የኢትዮጵያ አምላክ እገር አሳጥቶ፣

መከራ አስቆጥሮህ የትም አንከራቶ፣

እህል እንዳማረህ ውሃ እንደናፈቀህ፣

ቸሩ መድኃኒዓለም ያውሬ እራት ያድርግህ።

ከድሮ ጀምሮ በአንክሮ እንዳየነው፣

ግፍ በቃኝ የማይል አበሻ ብቻ ነው።

ህዝብ ላይ ተጣብቀህ ደሙን እንደትኋን፣

መጠህ የጠጣኸው ደመቀ መኮንን፣

ወደፊት እማይደርስ እስካሁን ያልመጣ፣

አለም ጉድ የሚያሰኝ ያውርድብህ ቁጣ።

ህዝብ እንዲቆራመድ ሀገር እንዲጠፋ፣

ደክመህ የምትሰራው ጌታቸው አሰፋ፣

የሰራኸውን ግፍ ጌታ ተመልክቶ፣

ከተቀመጥክበት በድንገት አንስቶ፣

አስር ቦታ ሰብሮ አጣጥፎህ እንደጨርቅ፣

ጭለማ ያልብስህ ይክተትህ መቀመቅ።

ገበየሁ የሚባል ለጥፋት ያፈራህ፣

የሰይጣን ዲቃላው ወርቅነህ የሚሉህ፣

በፌደራል ፖሊስ ህዝብ እንዳስቀጠቀክ፣

በሳት ውቅያኖስ ይጨምርህ አምላክ።

ያ ገብረ ክርስቶስ አንተን የወለደ፣

አንድ ሺህ ሰይጣን ነው ጥሎብን የሄደ።

ይሄው ሀገሪቱን ከሚያጠፉ ጋራ፣

አንድ ላይ በመቆም ይዘህ ትልቅ ስፍራ፣

ህዝብ ያሰቃየኸው ጨካኙ አረመኔ፣

ጋጠወጡ ፍጡር ከይሲው ብርሃኔ፣

የተቀመጥክበት ህንጻ ተደርምሶ፣

በቁምህ ይቅበርህ አካልህን ገምሶ፣

ሲራጅ የሚሉህ ሰው ያፈራህ ፈጌሳ፣

ተሰቃይተህ ከርመህ በአእምሮ ወቀሳ፣

ምትይዝ ምትጨብጠው አሳጥቶህ ሰላም፣

ዲያቢሎስ በክንፉ ይሰውርህ ከዓለም።

ህዝብን ቆሻሻ ነው ብለህ በመፈረጅ፣

አደባባይ ቆመህ የተናገርክ አዋጅ፣

አለምነህ መኮንን የሚሉህ ግትቻ፣

አምላክ አጥመልምሎ ይጣልህ ስርቻ።

በጥፋትህ ፈርተህ ከሀገር በመበርገግ፣

መድረሻህ የጠፋው ኦባንግ ኣሞት ኦባንግ፣

በጉርጓድ ተገኝተህ ልክ እንደጋዳፊ፣

ታስረህ ተቀጥቅጠህ ቀምሰህ ደህና ጥፊ፣

እንደጨፈጨፍከው እንዳጠፋኸው ነፍስ፣

ያንተም በመንገድ ላይ ትኩስ ደምህ ይፍሰስ።

አባ መላ የሚሉህ የታሪክ አተላ፣

ለርግማን ባትበቃም ቅጹን ባታሟላ፣

ከወያኔ ጋራ አብረህ በመሰለፍ፣

ህዝብን ስለጎዳህ ጠልፈህ በማስጠለፍ፣

ከጭፍሮችህ ጋራ ሰብስቦ በአንድ ላይ፣

ለዘር ሳያስተርፍ ይጠራርግህ አባይ።

በሚንስትርነት በጦር አዛዥነት፣

በስራ አስፈጻሚ በበታች ሹምነት፣

ምክር ቤት፣ ፍርድ ቤት፣ ቀበሌ ወረዳ

ተሰግስገህ  ያለህ የዘመኑ ባንዳ፣

ኢንባሲ ደህንነት ገብተህ በመኮልኮል፣

አገር የሚጎዳ የፈጸምክ በደል፣

አላግባብ የበየንክ ይዘህ የፍርድ ወንበር፣

ህዝብ ላይ የዘመትክ የገደልክ ወታደር፣

ለባርነት ሥራ ወጣቱን በመስደድ፣

በላቡ የከበርክ በደሙ ምትነግድ፣

ለሆድህ ያደርከው አከንፋሽ አወዳሽ፣

የእናት  ሀገርህን አንጋጠህ ጡት ነካሽ፣

የገዛ ወገንክን ገድለህ በጠመንጃ፣

መንገድ የወረወርክ ዘንጥለህ በሳንጃ፣

በነጋ በጠባ ህዝብ ምትጨፈጭፍ፣

እርጉሙ ወያኔን መርቀህ ምትጽፍ፣

በድብቅ በይፋ የገደልክ ያስገደልክ፣

በደለኛ ሆነህ ንጹሃንን ያሰርክ፣

ከኖረበት ቀዬ ህዝብን ያፈናቀልክ፣

ሀሰቱን እውነት ነው ብለህ የወሸከትክ፣

በተለያየ መልክ ኢትዮጵያ ላይ ያሴርክ፣

የሚኒሊክ ፈረስ በርግጫ ዘንጥሎ፣

ጎርጊስ አካባቢ ይጣልህ ጠቅልሎ።

በጣይቱ ጥፊ መሃል ፊትህ ይንደድ፣

እንደ ክምር ድንጋይ አከላትህ ይናድ።

የካሳ ጎራዴ ተምዘግዝጎ መጥቶ፣

ቦርጭህን ያፍርሰው ሆድህን ሸርክቶ።

አሉላ ለጠላት የወረወሩት ጦር፣

ደረትህን በስቶ ሳንባህ ላይ ይቀርቀር።

የባልቻ አባ ነፍሶ የኃይለማርያም ማሞ፣

የመንፈስ ቁጣቸው ይጣልህ አጣሞ።

እነ አቡነ ጴጥሮስ የሞቱባት ሃገር፣

ማህፀኗን ዘግታ ትንፈግህ መቃብር።

መርገምተ ወያኔ ለቅጣት ሲመጣ፣

የስራህን አግኝ የጅህን አትጣ።

ንዴቴን ተወጣሁ በቃኝ ተገላገልኩ፣

እልቤ ያለውን እርግማኔን ጨረስኩ።

ዘመኑን ስንፈትሽ ጊዜውን ስናየው

 ግፍ በቃኝ ያላለ ይሄ ትውልድ ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Literature Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. MF says

    March 19, 2014 04:37 pm at 4:37 pm

    God bless u…

    Reply
  2. abudalis says

    March 20, 2014 06:22 pm at 6:22 pm

    yelben yehoden …aderesk TEBAREK ABO…

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am
  • በትግራይ የሰላም ስምምነቱን መሠረት ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደሚፈጸም ተገለጸ December 13, 2022 09:20 am
  • ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ሌብነት የተከሰሱት የደኅንነት መ/ቤት ሠራተኞች ክስ ተመሰረተ December 13, 2022 09:06 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule