እኔ ልሙት አንቺ፣ አንቺ ትሞች እኔ፣ ሳያውቅብን ቀኑ፣ ሳናውቅበት ቀኑን፣
በቁም ያለን መስሎን፣ እናቴ እኔና አንቺ፣ ተለያይተን ቀረን።
ሞትን መቀበር ነው፣ በጉድጓድ መከተት፣ ከምድር በታች መዋል፣
ብለህ አትናገር፣ ሌላ ሞትም አለ፣ አታውራ ዝም በል።
በእኔና በእናቴ፣ በልጅና በእናት፣ ደርሷል ቆሞ መሞት፣
ቀኑ ወር ተክቷል፣ ወራት ብዙ ዓመታት፣ ሳታየኝ ሳላያት።
አዎን! አለች አለሁ፣ አለን እንላለን፣ በስጋ ቆመናል፣
ነገር ግን ውሸት ነው፣ የለሁም የለችም፣ መለየት ገድሎናል።
እንዴት ነው፣ ያለችው?፣ እንዴት ነው፣ ያለሁት?
እሷ ልጄ እንዳለች፣ እኔ እናቴ እንዳልኳት፣
ተስፋችን ሞቶብን፣ ላታየኝ ላላያት፣
ቆመናል አልልም፣ የለሁም የለችም፣ እናቴ የእኔ እናት…
Gedion Adenew says
yemin maguremrem new- mindinew Bisotu
yesew lij endiley – ke enat kabatu
bilom enditabek- ke wuditua mistu
sale tegeltsolih- tetsifo bekalu?