ያልተገራ ፈረስ ደርጉ እያላችሁ ፈርጥጦ ፈርጥጦ ገደል ገባላችሁ ........... የሚለው የ1966ቱ የለውጥ ማግስት የወቅቱ ወጣቶች ዜማወግ ሰሞኑን ትዝ ትዝ እያለኝ ነው፤ መንግሥት ግራ እንደገባው የተረዳው የያኔው ተማሪዎች መካከል እርስዎም የወቅቱ ወጣት ነበሩና መዝሙሯን በደንብ እንደሚያስታውሷት አልጠራጠርም፡፡ ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ mintuye1984@gmail.com “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ … [Read more...] about ይድረስ ለኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ
tplf
ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወድያ
ሰሞኑን አየሩን የሞላው “የበላይነት” የሚለውን ጽንሰሃሳብ በመለጠጥና በማጥበብ ዙርያ ሆኗል። የህወሃት የበላይነት፣ የትግራይ የበላይነት፣ የትግራይ ህዝብ የበላይነት በሚሉ ብዙም በማይራራቁ ጽንሰ ሃሳቦች ዙርያ ከዝንብ መላላጫ የማውጣት ያህል ከየአቅጣጫው እየተሰነዘሩ ነው። እነዚህ እሰጥ አገባዎች አብዛኛውን ጊዜ ስሜታዊነትና ጥላቻም ተቀላቀሎባቸው ሶሻል ሚድያውን፣ የርስ በርስ ውይይቱንና መገናኛ አውታሮችን ያጣበቡ ሲሆን በጣም ጥቂቶች በአጋጣሚው የጠለቀ ትንተና በመስጠት በነገሮች ላይ ያለንን እይታ እንዳሰፉት እሙን ነው። ወያኔም ህብረተሰቡ በዚህ ስሜታዊ እንካስላንትያ ሲጠመድ ሊያገኝ የሚችለውን እፎይታና የተቃውሞው ጎራ መከፋፈል ሊያተርፍበት ሲንደፋደፍ ይታያል። ለእኔ ደግሞ “የበላይነት” አለ፣ የለም የሚለው ጉንጭ አልፋ ውይይት ላይ ጊዜና ጉልበታችን ሲጠፋ አግባብ ሆኖ አይታየኝም። … [Read more...] about ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወድያ
“ቄሮ አልሸባብ” ነው – ህወሓት!
“ስድስት ሚሊዮን ወጣት በጠላትነት ፈርጀህ ማንን ልታስተዳድር ነው?” ለማ መገርሳ ህወሓት/ኢህአዴግ በኢትዮጵ የተለያዩ ክፍሎች በተለይም በምሥራቅ ሐረርጌ “ቄሮ” በመባል የሚታወቅ ሕገወጥ እንቅስቃሴ እመረምራለሁ፤ ለፍርድ አቀርባለሁ ብሎ ዝቷል። “አመራሩ ብቃት የለውም” በማለት ራሱን የገመገመው ህወሓት/ኢህአዴግ ብቃት አልባነቱን ተገንዝቦ ራሱን ከሥልጣን ማግለል ሲገባው አሁንም የማሰርና የማሰቃየት ግፉን በስፋት ለመቀጠል በዕቅድ ለመቀንቀሳቀስ ማሰቡን ነው በዚህ ዜና የገለጸው። የኢትዮጵያ ወጣቶችን በሥራ በማሰማራት ለአገር እንዲጠቅሙ ከማድረግ ይልቅ “አደገኛ ቦዘኔ” በማለት ሲፈርጅና ሲስር የነበረው ህወሓት አሁን ደግሞ በኦሮሞ ወጣቶች “ቄሮ” ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ለመሰንዘር ጎራዴውን እየሳለ ነው። ግፉ የበዛባቸው ወጣቶች ታላቁ ሩጫ በተካሄደበት ባንድ ወቅት ላይ “አደገኛ ቦዘኔ … [Read more...] about “ቄሮ አልሸባብ” ነው – ህወሓት!
ስለ ለማ መገርሣ ጥቂት ምልከታዎች
ማሳሰቢያ፤ ከዚህ በታች የሰፈሩት ጽሁፎች በቀጥታ ከተለያዩ ጸሐፍት (በተለይ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከሚሳተፉ) የተወሰዱ አስተያየቶችና ምልከታዎች ናቸው እንጂ የጎልጉል አቋም አይደሉም። ዮሐንስ ሞላ እንዲህ ይላል፤ አቶ ለማ መገርሳ የመንግስት ባለስልጣን ሆኖ በቆየበት ጊዜ ሁሉ ሲያስገድል፣ በሀሰት ሲያስወነጅል፣ ሕዝብን ከሕዝብ ሲያባላ እና በድህነት እንድንሰቃይ ለሙስና ሲያጋፍር ነው የኖረው። ሌላውን የኢህአዴግ ባለስልጣን አስኮንኖ፣ አቶ ለማ እና ዶ/ር ዐብይን ነጻ የሚያስወጣ ምንም ዓይነት ምክንያት የለንም። ማሽሞንሞን ሳያስፈልግ፥ አቶ ለማ መገርሳ የኢህአዴግ ሽንት ጨርቅ ነው። የአምባገነን ስርዓት ሽንት እንዳይታይ በማድረግ ረገድ የሚጫወተው የዳይፐርነት ሚና ከደረሱብን ጉዳቶችም የሚልቅ እና፣ ለዚህ ግብሩ መጨፈር እና መቀኘታችን ወደፊት ብዙ የሞራል ዋጋ የሚያስከፍለን … [Read more...] about ስለ ለማ መገርሣ ጥቂት ምልከታዎች
Abebe Kassie, a Brave Ethiopian and a Victim of a TPLF Terror House
(Note: Ethiopia is a current member of Human Rights Council of the United Nations) Below is a translation based on a letter obtained from one brave Ethiopian among many victims who have fallen into the hands of the terrorist regime of the Tigrayan People’s Liberation Front (TPLF) currently ruling Ethiopia. My name is Abebe Kassie, I am a forty-one-year-old from Armachoho Woereda in Northern Gonder. I am currently in Kilinto prison in the Akaki area. I was imprisoned by the TPLF on the 20th of … [Read more...] about Abebe Kassie, a Brave Ethiopian and a Victim of a TPLF Terror House
“አመራሩ ከሽፏል” ለማ
ታዲያ ሁላችሁም ለምን ከሥልጣን አትወርዱም? "ለአመጽ የግብረ መልስ የሚሰጥ አመራር እንጂ ለችግሮች ቀድሞ መፍትሄ የሚሰጥ አመራር አይደለም"፤ "አመራሩ ህዝቡ ከሚጠብቀው በታች ነው"፤ "አመራሩ ከሽፏል"፤ የማሸማቀቅና የማስፈራራት ተግባር ነው በፓርቲው ውስጥ ያለው፤ ተመሳሳይ ዓይነት ነገር ወደ ሕዝቡ ሰርጾዋል፤ ወዘተ በማለት "በድፍረት" የተናገረው የኦህዴዱ ለማ መገርሳ እንደዚህ ብቃት የሌለውን አመራር ቢያንስ "ሥልጣኑን መልቀቅ ይገባዋል" ሳይል ወይም ራሱ ሁኔታው የማይስተካከል ከሆነ ሥልጣኑን እንደሚለቅ ምንም ፍንጭ ሳይሰጥ ንግግሩን አብቅቷል። ህወሓት/ኢህ አዴግ እንደ ድርጅት ከሽፏል! ይህ የተመሰከረው ደግሞ በራሱ በአመራሩ ነው። እስካሁን በሥልጣን ለምን እንደቆዩ እና ወደፊትም ለመቆየት ለምን እንዳሰቡ ግልጽ ቢያደርጉ የተሻለ ነው። መለስም "እስከ እንጥላችን ገምተናል" እያለ … [Read more...] about “አመራሩ ከሽፏል” ለማ
ፎቶና ታሪኩ – እስረኞች [የህወሓት ግፍ ሰለባ ስለሆኑት ወገኖቻችን ሲባል ሊነበብ የሚገባው]
{ፈላስፋ በወህኒ ቤት በራፍ ላይ እንዲህ የሚል ፅሁፍ አነበብኩ አለ፤ ይህች ቦታ የመከራና የጭንቅ ናት፤ ያልሞቱ (በሕይወት ያሉ) ሰዎች የሚቀበሩባት መቃብርም ናት። የወዳጆች መፈተኛ፤ የጠላቶች መደሰቻ የሆነች ቦታ ናትና።} አንጋረ ፈላስፋ (የፈላስፎች አነጋገር)፤ በሊቀ መዘምራን ሞገስ ዕቁበ ጊዮርጊስ በ1953 ዓ/ም ከግዕዝ ወደ አማርኛ ተተረጎመ። ************************************************************* በወያኔ አገዛዝ፤ በወያኔ ቀንበር የካቴናው ስርስር የኮረንቲው ንዝር የመቀመቅ ፍዳው የጨለማው እስር የሰቆቃው ንረት የአውሬዎቹ ምንዝር እንዴት እንደ ሆነ እንዴት እንደነበር ፍትህ በሌለበት ለዳኛ ከመንገር ጠበቃ ከማቆም ዕማኝ ከመደርደር ይኸው የኛ ፎቶ ታሪኩን ይናገር። ፎቶ፤ ሴፕቴምበር 14 2011 (እአአ) የወያኔ ፀጥታ … [Read more...] about ፎቶና ታሪኩ – እስረኞች [የህወሓት ግፍ ሰለባ ስለሆኑት ወገኖቻችን ሲባል ሊነበብ የሚገባው]
የወያኔ “መርህ-አልባ” ክስ ስረ-መሰረትና አፀያፊ “ውነትነት”
ሰሞነኛ መነጋገሪያ የሆነው "ለፖለቲካ እስረኞች ይቅርታ ልሰጥ ነው?” የሚለው ድንገተኛየወያኔ ዛባር (ቅዠት) መሰል ወግ ከመንገዳችን እንዳያወጣን መነጋገሩ አስፈላጊ ሆኖ ስለተሰማኝ የዚህ ጽሁፍ ማጠንጠኛ ላደርገው ፈቀድኩ። “የእስረኛ መልቀቅ” ጩኸት ከአፋኞቹ አፍ አምልጦ እንዲወጣ ያስገደደው ዋነኛ ሀቅ የህዝብ እምቢተኛነትና አልገዛም ባይነት አመጽ ለመሆኑ አንዳች ብዥታ እንደሌለን እየታወቀ ወያኔ “ምህረትና-ይቅርታ” በሚሉ ቃላቶች ዙሪያ፤ በማፈራረቅ ሲዋዥቅ አውቆም ሆነ ሳያውቅ በፈጠረልን “አጀንዳ” የተነጠቀውን ኳስ አስመልሶ ዋናውን የነጻነት ጥያቄበብርሃን ፍጥነት ወደ እስረኛ የማስፈታት ባህሪ እንዳይወርደው ልብ ማለት የተገባ ነው። ለመሆኑ አሁንም አሁንም አጥፍቻለሁ፤ በስብሻለሁ፤ ተግማምቸ -አግምቻችኋለሁ እያለ ሲወሻከት የነበረው የወሮበላ ቡድን “ይቅርታ አስጠይቄ … [Read more...] about የወያኔ “መርህ-አልባ” ክስ ስረ-መሰረትና አፀያፊ “ውነትነት”
መልስ ለዶ/ር በያን አሶባ ቃለ መጠይቅ
የተከበራችሁ አንባቢያን፤ ይህችን መጣጥፍ ለመከተብ የተነሳሁት የዶ/ር በያን አሶባን (የኦሮሞ ዴሞክራሲ ግንባር ቃል አቀባይ) ቃለ መጠይቅ ካደመጥኩ በኋላ ነው፤ አመለካከታቸው ብዙ መልካም አስተሳሰቦችን በውስጡ ያካትታል፤ መልካም የምላቸው አመለካክቶች የኢትዮጵያ ችግር መፈታት ያለበት እዛው ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑ፤ መሰረታዊ ለውጥ ማስፈለጉ፣ በሙሉ እከሌ ከእከሌ ሳይባል የፖለቲካ እስረኞች የመፈታትን ሃሳብ፣ የውጭው ትግል አጋዥነት እንጂ መሪ ቦታ መያዝ እንደማይገባው፤ የሚሉትን ሲሆን ትልቁ ተቃውሞዬ ወያኔን የሽግግሩ አካል ማድረጉ ላይ ነው፤ (በሰላምና እርቅ ሰበብ) ፍራቻቸው ወያኔ አጓጉል አወዳደቅ ከወደቀ አገሪቱ የማትወጣበት ችግር ውስጥ ትገባለች ነው፤ {አገሪቱ የማትወጣበት ችግር ውስጥ ከገባች ሰንብታለች}። ወደ በያን አሶባ ማንነት ስመለስ ለዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ በመለሱት ደብዳቤ … [Read more...] about መልስ ለዶ/ር በያን አሶባ ቃለ መጠይቅ
IS THE EPRDF OFFER FOR REAL?
IS THE RELEASE OF POLITICAL PRISONERS AN HONEST FIRST STEP TO PRODUCTIVE DIALOGUE LEADING TO RECONCILIATION, MEANINGFUL REFORMS AND RESTORATIVE JUSTICE OR IS IT A MANIPULATIVE SURVIVAL TECHNIQUE FOR THE EPRDF? Washington, DC-- On January 3, 2018, Prime Minister Hailemariam Desalegn publicly declared the EPRDF’S (Ethiopian Peoples Revolutionary Democratic Front) decision to release all political prisoners and to close down the infamous Maekelawi detention center as a confidence-building measure … [Read more...] about IS THE EPRDF OFFER FOR REAL?