እስከ መቼ ዋይታ! መከራና ለቅሶ!
በእኛ ላይ ይደርሳል መልሶ መላልሶ!
«የትግራይ ተራሮች የዐማራ መቃብር ይሆናሉ» በሚል መፈክር፣ ለኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት ዘብ የቆሙ ኢትዮጵያውያንን ከ1967 እስከ 1983 ባሉት 17 ዓመታት ውስጥ፣ የሁሉንም ነገድ ልጆች በዐማራነት ፈርጀው በግፍ መጨፍጨፋቸውን፣ በምርኮ የያዙዋቸውን ወታሮች የወባ መድኃኒት ነው ብለው፣ የውሻ መግደያ መርዝ ግተው በምድር ውስጥ በገነቧቸው እስር ቤቶች መፍጀታቸውን እናውቃለን። ሁሉም ግን የተገደሉት በዐማራነት ስም መሆኑን ስንገነዘብ ደግሞ፣ የትግሬ ወያኔ በዐማራ ላይ ያለው ጥላቻ የቱን ያህል ከፍተኛ እንደሆነ ያሳያል። ዛሬ ይህ መፈክር፣«የኢትዮጵያ ተራሮችና ሸለቆች፣ ከተሞችና ገጠሮች የዐማራ መቀበረያ ይሆናሉ»፣ በሚል የተቀየረ እንደሆነ፣ በአገሪቱ ውስጥ በዐማራው ነገድ ላይ የሚፈጸሙት ግድያዎችና ግፎች አፍ አውጥተው እየተናገሩ ነው። «ዐማራ ካልጠፋ የትግራይ ሕዝብ ማኅበራዊ ሰላም አያገኝም» በሚለው መመሪያቸው መሠረት ለአንድነትና ለኢትዮጵያዊነት የቆሙ የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ነገድ ልጆች በግፍ መገደላቸውን ከትግሬ-ወያኔ በቀር የሌሎች ነገድ ልጆች አናውቅም ሊሉ የሚችሉ፣ አንድም መረጃ የሌላቸው፣ ሌላም በጥቅም የተገዙ ሆድ አደሮች ብቻ ናቸው። ይህ ካልሆነ አቶ ገብረመድኅን አርኣያ በተከታታይ በጠለምት፣ ወይቃይት፣ ተንቤን፣ ሽሬ፣ ደጀና፣ ዐድዋ ወዘተ በሚገኙ የባዶ ስድስት የማሰቃያ ጉድጓዶች ያለቁትን ወገኖቻችንን ያለመሰልቸት በዝርዝር ነግሮናል። የእኛ ችግር የመረጃ እጦ ሳይሆን፣ ዕውነቱ ሲነገረን፣ ነግ ለእኔ ብለን አስፈላጊውን ዝግጅት አለማድረጋችን ነው።
ይህም በመሆኑ፣ የትግሬ-ወያኔ ሥልጣንን ከተቆጣጠረ በኋላ፣ ዐማራውን በገዥ መደብነት፣ በጨቋኝነት፣ በትምክህተኝነት፣ ባለፉ ሥርዓቶች አቀንቃኝነት ስሞች ፈርጀው፣ የጎጃምንና የጎንደር ክፍለ ሀገር ነዋሪ ዐማራን «ሽፍታ ምንጠራ፣ መሬት ድልድል» የሚሉ የዘመቻ ስሞችን ሰጥተው ዐማራውን ትጥቁን ማስፈታታቸውን፣ መሬቱን መቀማታቸውን የምናስታውሰው በምሬት ነው። ድርጊቱ ትክክል አይደለም ያሉትን ልበ ሙሉ ጀግኖቻችንን በገፍ መግደላቸውና ማሰራቸው እንዲሁም ማሰደዳቸውን እናስታውሳለን። የወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ሠቲት ወረዳዎችን በመሬቱ ላይ ትግሬን ለማስፈር ከ1972 ዓም ጀምሮ በተከታታይ ዐማራዎቹን በግፍ መግደላቸው፣ ማሰራቸውና እንዲሰደዱ መደረጉ የአደባባይ ምስጢር ነው። በ1985 ጎንደር አደባባይ ኢየሱስ ለፀሎት በተሰበሰቡ የከተማው ነዋይዎች ላይ የደደቢት ሠራዊት በመትረጌስ የጨፈጨፋቸው ሰዎች ደም ዛሬም እየጨኸ ነው። በ1985 ዓም የቡትሮስ ቡትሮስን የወቅቱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊን የኢትዮጵያን ጉብኝት ዓላማ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በወጡ ተማሪዎች ላይ የአገዛዙ አፋኝ ወታደራዊ ቡድን የገደላቸውን ተማሪዎች «በኢሠፓ» አባልነት እና በዐማራነት የወነጀላቸው እንደሆነ እናስታውሳለን።
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።
Mulugeta Andargie says
Guys!!! Bene bekul ijigun yemizegnen Zena new!!!
Mulugeta Andargie says
ሰዎች!! የፖሊሶች ድርሻ ቀንሷል ባይ ነኝ!!!