ፍርሃትን እያሰረጸና እያነገሰ የኖረው ፖለቲካችን ነጻነታችንን፣ ክብራችንን፣ ታሪካችንን፣ ስብዕናችን እና አብሮነታችንንም ጭምር ሲያኮስስና ሲያረክስ፤ እንዲሁም የወደፊት ተስፋችንም ላይ ጥላውን ሲያጠላ እያየን ነው። የማንኛውም አንባገነናዊ ሥርዓት ሥነ-ልቦናዊ መሰረቱ ፍርሃት ነው። አንባገነኖች ያላቸውን ኃይል ሁሉ የሚያሟጥጡት ሕዝብን በማሸበር የፍርሃት ቆፈን ውስጥ እንዲቆይ በማድረግ ነው። ለዚህም አራት ነገሮችን በዋነኝነት ይጠቀማሉ። የመጀመሪያው የጡንቻቸውን ልክ ለማሳየት ዱላና ጠመንጃን በመጠቀም የጭካኔ በትራቸውን በሕዝብ ላይ ማሳረፍ ነው። ለመቀጣጫም ከማህበረሰቡ ውስጥ የነቁና ሥርዓቱን በአደባባይ የሚተቹ እና የሚያሳጡ ሰዎችን ዒላማ በማድረግ ያስራሉ፣ ይገርፋሉ፣ ያሰቃያሉ፣ አልፎም ይገድላሉ። ሁለተኛው ፍርሃት የሚያሰርጹበት መንገድ ደግሞ የመገናኛ ብዙሃንን በቀጥታና በተዘዋዋሪ … [Read more...] about ሕዝብ ፍርሃትን እያሸነፈ፤ የወያኔም ጀንበር እየጠለቀች ነው!