ከለውጡ ሾፌሮች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ለማ መገርሳ የሽግግሩ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ ጃዋር መሐመድ አጥብቆ ሲከራረከር ነበር። አቶ ለማ የፌዴራል ፓርላማ ተወካይ ባለመሆናቸው እርሳቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር እንዳይሆኑ የሚከለክላቸው መሆኑ የታወቀ ቢሆንም በወቅቱ ግን ጃዋር ከጓደኞቹ እነ ሕዝቅኤል ገቢሣ ጋር በመሆን “ኢህአዴግ አዲስ መመሪያ/ሕግ አውጥቶም ቢሆ አቶ ለማ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊያደርጋቸው ይገባል” በማለት ሃሳብና መመሪያ ቢጤም ሲሰጥ ነበር። ጃዋር ያለውና ያሰበው ሳይሆን አቶ ለማ በለውጡ ሙቀት ውስጥ ባሉበት ወቅት “እኔና ዐቢይን ሞት ብቻ ነው የሚለየን” በማለት የድርጅት ሊቀመንበርነታቸውን ለዶ/ር አብይ አሳልፈው በመስጠት ዐቢይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆን የበኩላቸውንና ድርጅታዊ ኃላፊነታቸውን ከባልደረቦቻቸው ጋር ሆነው እውን አደረጉ። የሆሮ ጉድሩ … [Read more...] about አቶ ለማ መገርሳ – በህወሃት የማስፈራሪያ አጣብቂኝ ውስጥ
Middle Column
“የመረራን ፓርቲ የተቀላቀልኩት የሸዋን ድምጽ ለመሰብሰብ ነው”
መረራ - ሲያልቅ እጅ ሰጡ!! ኦነግን ይዞት በነበረው አቋም አማካይነት ፍጹም እንደማይነሳ አድርገው የቀጠቀጡት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ናቸው። “ኦሮሞ ግንድ እንጂ ቅርንጫፍ አይደለም ” ሲሉም የኦሮሞን አካታችነትና ታላቅ ሕዝብነት በማስረገጥ የጎጥ ፖለቲካ ረብ የለሽ መሆኑንን በጥናት አስደግፈው ኦነግን ያኮሰሱት መረራ፤ ኦነግ ውጤት እንደማያመጣም ተናግረው ነበር። ዛሬ ግን “ተመልሰው ለኦነግ እጅ ሰጡ” ሲሉ ወዳጆቻቸው ሳይቀሩ እየወቀሷቸው ነው። የአምቦ ክፋይ በሆነችው ጊንጪ የተለኮሰው የኦሮሞ ትግል አድማሱን አስፍቶ ወደ ሌሎች ክልሎችም ተስፋፍቶ በጥምረት ለውጤት ሲበቃ፣ ላለፉት ሃምሳ ዓመታት ሲንከላወስ የነበረውና ተፈረካክሶ በየአቅጣጫው የተበተነው የኦነግ አመራሮች ወደ አገር ቤት “በጀግንነት” የመግባት ዕድል ተጎናጸፉ። እናም የድል አጥቢያ አርበኛ ሆነው የጠመንጃውንና … [Read more...] about “የመረራን ፓርቲ የተቀላቀልኩት የሸዋን ድምጽ ለመሰብሰብ ነው”
የጃዋር ትልቁ የመጫወቻ ካርድ ተቃጠለ – መቀሌ ለለማ የተጋገረውን ኬክ ኦዴፓ ቆረሰው
ጃዋር የሬዲዮ ፈቃድ ተከለከለ - አበደንን እያስተዋወቀ ነው ከአጋሮቹና አቻዎቹ ጋር እኩል ረድፍ ገብቶ ወደ ብልጽግና ፓርቲ ራሱን በመቀየር ለመጪው ምርጫ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘውን የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኦዴፓን ለመሰንጠቅ በፌዴራሊስቶች ስም መቀሌ የተጋገረውን ኬክ የብልጽግና ፓርቲ እንደቆረሰው ተሰማ። ጃዋር መሃመድ አሁን ካሉት ሁለት የቴሌቪዥንና አንድ የሬዲዮ ስርጭት ጣቢያ በተጨማሪ ለመክፈት ያሰበው ሬዲዮ ፈቃድ መከለከሉ ታወቀ። ራሱን በተገንጣይ ስም እየጠራ “የኢትዮጵያ ጉዳይ ያሳስበኛል” በሚል “የፌደራሊስት ኃይሎች” ብሎ ራሱ የሰየማቸውን ለቃቅሞ መቀሌ ላይ ትህነግ የጋገረውን ኬክ ይቆርሳሉ ተብሎ የታሰበው አቶ ለማ መገርሳ ነበሩ። ለዚሁም ዝግጅት መንደረደሪያ አቶ ለማ በኦሮሚያ ይቋቋማል የተባለውን የኦሮሞ ፓርቲዎች ኅብረት እንዲመሩ ቅድመ ዝግጅቱ ተጠናቆ ነበር። … [Read more...] about የጃዋር ትልቁ የመጫወቻ ካርድ ተቃጠለ – መቀሌ ለለማ የተጋገረውን ኬክ ኦዴፓ ቆረሰው
በወታደራዊ መረጃ ምጡቅ እርምጃ
ዛሬ ታኅሣሥ 10፤2012ዓም ኢትዮጵያ በታሪኳ መጀመሪ የሆነውን ሳተላይት አምጥቃለች። ሳተላይቷ መረጃ አገልግሎት የምትሰጥ ነች የተባለ ሲሆን ይህም ባብዛኛው የመልከዓ ምድር ጥናትና የመሳሰሉትን ለማድግ የምትጠቅም መሆኗ ተነግሯል። ለወታደራዊ ግልጋሎት አትውልም የሚል ቢባም ሳተላቷ መረጃ ስትሰበስብ ይህ ቀረሽ እንደማትባል፤ “ከግዙፍ ክንውኖች እስከ ጥቃቅን እንቅስቃሴዎች” እንደምትመዘግብና እንደምታስተላልፍ ባለሙያዎቹ ይናገራሉ። በዓለማችን ወታደራዊ የበላይነት የተጎናጸፉ አገራት በርካታ ሳተላይቶች በኅዋው ላይ አላቸው። ከምስራቅ አፍሪካ እንኳን በኬኒያና በሱዳን ተቀድመናል። ከተለያየ አቅጣጫ የውጭ ጠላት ያላት አገራችን አንድ ብቻ አይደለም በርካታ ሳተላይቶች ያስፈልጓታል። በተለይ ደግሞ አገር ውስጥ ያሉ አፍራሾች የሚደርጉትን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር፣ ማባሪያ ያጣውን የወሰን … [Read more...] about በወታደራዊ መረጃ ምጡቅ እርምጃ
የኖቤል የሰላም አሻራ በኤርትራም! ባስቸኳይ!
የ2019 የዓለም የኖቤል የሰላም ሽልማት የእኛ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የእኛው ቤተሰቦች የሆኑት የኤርትራዊንም ነው ሲባል ለጎልጉል የሚገባው ሃሳቡ ወይም ንግግሩ ከመደመርም በላይ የሚታይ ስለሆነ ብቻ ነው። እንደሚታወቀው የኖቤል ተሸላሚዎች ከሚቀበሉት ዲፕሎማ በተጨማሪ ግምቱ 10ሺህ ዶላር የሚገመት 18 ካራት አረንጓዴ ወርቅ የተለበደበት 24 ካራት ወርቅ የሚሰጥ ሲሆን ወደ 950ሺህ ዶላር የሚገመት የገንዘብ ሽልማትም አብሮ ይሰጣል። ከገንዘቡና ከወርቁ ይልቅ ዓለምአቀፋዊ ዕውቅና ዝናው ከሁሉ የሚበልጥ ነው። ከዚህ በፊት በተለያዩ መስኮች የተሸለሙ በተሰጣቸው ገንዘብ ምን እንዳደረጉበት ሲናገሩ ለልጆቼ ኮሌጅ ወጪ አዋልኩት፤ አዲስ ቤት ገዛሁበት፤ በቀጥታ ወደ ቁጠባ የባንክ ሒሳቤ ነው አስገባሁት፤ ወዘተ የሚሉ መልሶችን ሰጥተዋል። የ2019 የዓለም የሰላም ሎሬት ዐቢይ … [Read more...] about የኖቤል የሰላም አሻራ በኤርትራም! ባስቸኳይ!
“ዓይኖች ሁሉ ወደ ኦስሎ ተተክለው ስለ ኢትዮጵያ ተመለከቱ”
ኦስሎ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ እስክትመስል ድረስ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማና በኢትዮጵያ ባነሮች ተውባ ሰነበተች። ሚዲያዎች ሁሉ ስለ ኢትዮጵያ በኩራት መሰከሩ። ኢትዮጵያን በድህነትና በጦርነት፣ በረሐብና በእልቂት የሚያውቋት ሁሉ አዲስ ታሪክ ሆነባቸው። በሩጫ ስናሸንፍ ነበር የሚያውቁን፤ ዛሬ ደግሞ በሰላም ሥራችን በዓለም አቀፍ መድረክ ስናሸንፍ አዩን። ከግሪን ላንድ እስከ ኒውዚላንድ፣ ከቺሊ እስከ ጃፓን ዓይኖች ሁሉ ወደ ኦስሎ ተተክለው ስለ ኢትዮጵያ ተመለከቱ። በመላው ዓለም ተበትነው የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን የዜግነት ክብራቸውን ከፍ የሚያደርግ ሥራ በታሪክ ውስጥ ሲመዘገብ አዩ። ልጆቻቸው በባዕድ ሀገር በታሪካቸው ኮሩ። ሀገራቸው በምሳሌነትና በአርአያነት ስትነሣ በዓይናቸው ብሌን ተመለከቱ፤ ሰሙ። በዓረብ ሀገር የሚኖሩ ዜጎቻችን አሠሪዎቻቸው ወደታች ሳይሆን ወደላይ እንዲዩዋቸው … [Read more...] about “ዓይኖች ሁሉ ወደ ኦስሎ ተተክለው ስለ ኢትዮጵያ ተመለከቱ”
የ2019 የኖቤል የሰላም ሎሬት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አሊ (ዶ/ር)
የ100ኛው የኖቤል የሰላም ሎሬት በመሆን ለተሸለሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አሊ ክብር በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ የኖርዌይ ንጉሣውያን ቤተሰቦች የተገኙ ሲሆን ሥነሥርዓቱ የቱንም ያህል ጥንቃቄ ቢደረግበትም የተፈጸመ አንድ አስደናቂ ክስተት ነበር። በሽልማቱ አሠጣጥ ሥነሥርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የኖቤል ኮሚቴ ሊቀ መንበር ቤሪት ራይስ አንደርሰን ንግግራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ የሽልማቱን ዲፕሎማና ሜዳሊያ ለሰላሙ ሎሬት መስጠት ሲገባቸው እርሳቸው እንዳሉት “ክቡር ጠ/ሚ/ር በንግግር ሃሳቤ ተወስዶ ሽልማቱን ሳልሰጥዎ ቀረሁ” ብለዋል። በወቅቱም አዳራሹ በሳቅ ተሞልቶ የነበረ ሲሆን ይህም ድርጊት ባልተለመደ መልኩ ብዙዎችን ያስደመመ ሆኗል። በፕሮቶኮል ባለፈም በእርግጥ ልባዊና እውነተኛ ስሜት የታየበት ሆኖ አልፏል። ሥነሥርዓቱን ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ። … [Read more...] about የ2019 የኖቤል የሰላም ሎሬት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አሊ (ዶ/ር)
“… እኛ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ነን” ቤሪት ራይስ አንደርሰን
የኖቤል ኮሚቴ ሊቀ መንበር ቤሪት ራይስ አንደርሰን ለጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድ ሽልማት ከመስጠታቸው በፊት ባደረጉት ንግግር ጠቅላይ ሚንሥትሩ ለሰላም ላበረከቱት አስተዋጽዖ ምሥጋናቸውን አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ ሰላምና ዲሞክራሲን ለማስፈን በርካታ ርምጃዎችን መውሰዳቸው እንዲሁም በካቢኔያቸው አምሳ በመቶ ሴቶችን መሾማቸዉ ተመስግኗል። በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የሰላም ሚንስትር ሙፈሪያት ካሚል፣ የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ሣኅለ-ወርቅ ዘውዴ እንዲሁም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ማአዛ አሸናፊ ሴቶች መኾናቸውን ሊቀመንበሯ አመስግነዋል። ሽልማቱም የተሰጠው፦ ሰላም እና ብልጽግና በኢትዮጵያ ለማስፈን ዓልመው መነሳታቸው ሊቀመንበሯ ገልጠዉ የኖቤል ኮሚቴዉ ዕውቅና ሰጥቶታል። በምሥራቅ አፍሪቃ ሃገራት ሰላም እንዲሰፍን ጠቅላይ ሚንስትሩ … [Read more...] about “… እኛ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ነን” ቤሪት ራይስ አንደርሰን
አሸባሪው ህወሓት በሕገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር በሕግ መታገድ፤ መሪዎቹም በኃላፊነት መጠየቅ አለባቸው
ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትህነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የወንበዴዎች ጥርቅም፤ እስካሁንም በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። አባላቱና ደጋፊዎችም በዚሁ ሁኔታ የሚታዩ መሆናቸውን ብዙዎች የሚስማሙበት ነው። በአገራችን ባለፉት ሁለት ዓመታት ያህል በእጅጉ ተንሰራፍቶ ከሚገኙት ሦስት ሕገወጥ ሥራዎች መካከል አንዱ ሕገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር ነው። ሌሎቹ ሁለቱ ደግሞ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ሐሰተኛ የዜና ዘገባዎች ናቸው። በሦስቱም ውስጥ አሸባሪው ህወሓት እጁ እንዳለበት በርካታ ጠቋሚ መረጃዎች አሉ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ድብቅ ምሥጢራትን በማውጣት የሚታወቀው ethio wiki leaks “ህወሓት እና የጦር መሳሪያ … [Read more...] about አሸባሪው ህወሓት በሕገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር በሕግ መታገድ፤ መሪዎቹም በኃላፊነት መጠየቅ አለባቸው
የመከላከያ ሚኒስትር ለማ መገርሳ መልቀቂያ አላቀረቡም!!
ዜናው የውሸት ነው ለሥራ ወደ አሜሪካ ያቀኑት የመከላከያ ሚኒስትር ለማ መገርሳ የሥልጣን መልቀቂያ ማስገባታቸውን ጠቅሶ ፋኑኤል ክንፉ ፈንታሌ በሚባለው የግል የዩቲዩብ ገጹ በድምጽ ያሰራጨው ዜና ከእውነት የራቀ መሆኑ ተጠቆመ። “የፈንታሌ ሚዲያ ምንጮች" እንደነገሩት ያስታወቀው ፋኑኤል ክንፉ ዜናው እውነት እንደሆነ አድርጎ ለማሳየት የተጠቀመው አቶ ለማ ለቪኦኤ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ነው። ለአቶ ለማም ሆነ በኦሮሚያ ጉዳይ እጅግ ቅርብ የሆኑ የሚዲያ ውጤቶች ለጊዜው ምንም ያላሉበትን ጉዳይ ፋኑኤል ምንጮቹን ጠቅሶ ይህንን አነጋጋሪ ዜና ትናትን ሌሊት (በአዲስ አበባ አቆጣጠር) ላይ መለጠፉ አነጋጋሪ ሆኗል። ዛሬ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የመከላከያ ሚኒስትርን ጠቅሶ እንዳለው ከሆነ የአቶ ለማ የስልጣን መልቀቅ ጥያቄ የሚታወቅ አይደለም። … [Read more...] about የመከላከያ ሚኒስትር ለማ መገርሳ መልቀቂያ አላቀረቡም!!