• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ዓይኖች ሁሉ ወደ ኦስሎ ተተክለው ስለ ኢትዮጵያ ተመለከቱ”

December 11, 2019 07:53 pm by Editor 1 Comment

ኦስሎ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ እስክትመስል ድረስ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማና በኢትዮጵያ ባነሮች ተውባ ሰነበተች። ሚዲያዎች ሁሉ ስለ ኢትዮጵያ በኩራት መሰከሩ። ኢትዮጵያን በድህነትና በጦርነት፣ በረሐብና በእልቂት የሚያውቋት ሁሉ አዲስ ታሪክ ሆነባቸው። በሩጫ ስናሸንፍ ነበር የሚያውቁን፤ ዛሬ ደግሞ በሰላም ሥራችን በዓለም አቀፍ መድረክ ስናሸንፍ አዩን። ከግሪን ላንድ እስከ ኒውዚላንድ፣ ከቺሊ እስከ ጃፓን ዓይኖች ሁሉ ወደ ኦስሎ ተተክለው ስለ ኢትዮጵያ ተመለከቱ።

በመላው ዓለም ተበትነው የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን የዜግነት ክብራቸውን ከፍ የሚያደርግ ሥራ በታሪክ ውስጥ ሲመዘገብ አዩ። ልጆቻቸው በባዕድ ሀገር በታሪካቸው ኮሩ። ሀገራቸው በምሳሌነትና በአርአያነት ስትነሣ በዓይናቸው ብሌን ተመለከቱ፤ ሰሙ። በዓረብ ሀገር የሚኖሩ ዜጎቻችን አሠሪዎቻቸው ወደታች ሳይሆን ወደላይ እንዲዩዋቸው የሚያደርግ ታሪክ በዓለም አደባባይ ሲከወን ዕንባ በተሞሉ ዓይኖቻቸው አደነቁ።

ሁለት ዓይነት ታሪክ ሲሠራ የዓለም ዓይኖች ታዘቡ። በጦርነት የምትታወቅ ሀገር የሰላም ሽልማት ተሸለመች። የሰላምን ዋጋ የሚያውቀው ዓለም፤ የሰላም ሽልማት በቀላሉ እንደማይገኝ የሚያውቁ የዓለም ዜጎች በደስታና በክብር አብረውን ከረሙ። ለሕዝቦች መቀራረብ፣ ለሕዝቦች መገናኘት፣ ለሕዝቦች ዕርቅና ሰላም መሥራት የሚያሸልም ተግባር መሆኑን የሚያውቁ ሁሉ፤ የቻሉ በኦስሎ ጎዳናዎች ተገኝተው፤ ያልቻሉ በየቴሌቭዥን መስኮቶች አፍጥጠው ክብር ሰጡን።

በኦስሎ ያገኘነው ክብር የሀገራችን ጉዞ ከትናንት የዛሬው፣ ከዛሬውም የነገው እጅግ የተሻለ መሆኑን አመላክቶናል። ይህ ለኢትዮጵያውያን የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ አይሆንም። በሰላም፣ በሳይንስ፣ በሥነ ጽሑፍ ገና ብዙ ኢትዮጵያውያን ወደ ኖቤል ሀገር ወደ ኖርዌይ ይመጣሉ።

ዛሬ ያገኘነውን አክብረን አያሌ ኢትዮጵያውያን በዓለም አቀፍ መድረኮች ሀገራቸውን እንዲያስጠሩ እንሠራለን። ለዚህ ደግሞ ሁላችንም ሀገር የሚያስጠራ ጥረት እንድናደርግ ጥሪ አቀርባለሁ።

Abiy Ahmed Ali

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column, Nobel Peace Prize Laureate Abiy Ahmed Ali

Reader Interactions

Comments

  1. መታሰቢያ says

    December 12, 2019 10:52 am at 10:52 am

    በመላው አለም በታሪክ ውስጥ ያለውን ጦርነቱንም ሰላሙንም ሽልማቱንም የሚፈጥሩት በአብዛኛው እራሳቸው ግሎባሊስት ኦሊጋርኬዎቹ ናቸው።የአንድን ሀገር መሪ ሲያወድሱም ሲሸልሙም ያ ግለሰብ ለሀገሩ ህዝብ ብሄራዊ ጥቅም ምን መልካም ነገር ሰራ ወይንም ለወደፊት ምን መልካም ነገር ይሰራል ብለው ሳይሆን ዋና መመዘኛቸው ለግሎባሊስት ኦሊጋርኬው አለም አቀፍ ጥቅም ምን ሰርቷል ወይንም ወደፊት ምን ሊሰራ ይችላል ተብሎ ታቅዶና ተሰልቶ ነው። በተቃራኒው የአንድን ሀገር መሪ ሲያወግዙና ጫና ሲያደርጉም ከራሳቸው ዘላቂ ጥቅም አንፃር አስልተው ነው።ሌላው በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል ለተፈጠረው ሰላም መሸለም የነበረባቸው የሁለቱም ሀገር መሪዎች መሆን ነበረባቸው።ለምን ዶክተር አቢይ ብቻ ተለይተው ተሸለሙ?
    እርግጥ ነው ለሰላም የሚገባውን ዋጋ ያህል መከፈል አለበት።ከዚህ አንፃር ኤርትራና ኢትዮጵያ ለዘላቂ ሰላም መስፈን በየፊናቸው ምን ያህል ዋጋ እየከፈሉ ነው?ከዚህ አንፃር ኢትዮጵያስ ዘላቂ ብሄራዊ ጥቅሟን ምን ያህል እያስጠበቀች ነው?ነው ወይንስ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሟ የሚጠበቀው በኖቤል ሽልማቱ ብቻ ነው ማለት ነው?ኢሳያስ ቀርተው አብይ ተለይተው ሲሸለሙ ኢትዮጵያ እስከዛሬ ለሰላም አብልጣ የከፈለችው እና ወደፊትም በቀጣይ የምትከፍለው የበለጠ ብዙ ዋጋ አለ ማለት ነው?
    የሀገራችን መሪ በአለም አደባባይ መሸለሙ የኢትዮጵያ ስም በመልካም መጠራቱ ጥሩ ስሜት ይፈጥራል ደስ ይላል።
    ነገር ግን በእውነት እና በምክንያትነት ላይ ያልተመሰረተ ሆያ ሆዬ እና ጊዚያዊ የደስታ ስሜት አላፊ ነው።የኖቤል ሽልማቱ ጊዚያዊ ስኬት መሬት ላይ ያለውን ያፈጠጠ ያገጠጠ ነባራዊ ሁኔታ ያን ያህል አይቀይረውም።
    አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ እንዳይሆን አርቆ ማሰቡ ይጠቅማል።
    የአንድን ሀገር እና ህዝብ አጠቃላይ መፃኢ
    እና ነባራዊ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ከአንድ ግለሰብ ጋር አቆራኝቶ ማስተሳሰርም ወደ ሌላ ተጨማሪ ፈተና እንዳይወስደን መጠንቀቅና አርቆ ማሰብ ይጠቅማል።የአንድ ሀገር ዋናው የኖቤል ሽልማቱ በቅድሚያ የራሱን ሀገር ብሄራዊ ጥቅም ማስጠበቅ ነው።ፈረንጆቹ ብልጦች ስለሆኑ በየተቋሞቻቸው ለሚያቀርቡልን ግለሰባዊም ሆነ ቡድናዊ ጊዚያዊ ውዳሴ ከንቱ ሁሉ እንደ ህፃን ልጅ በቀላሉ የምንሸነፍ ወይንም የምንሸወድ ከሆነ ብዙ ጥፋቶችን ልንሰራ እንችላለን።ጥሩ የሰራን እየሸለሙ ማበረታታት ያለና ወደፊትም የሚኖር መልካም ነገር ነው።ነገር ግን አንድ ሽልማት ሲሰጥ ለሽልማቱ ከበስተጀርባው ያለው ገፊ ምክንያት ምንድን ነው ብሎ መጠየቅና መመርመር ይገባል።የውጪ ሃይሎች ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ውዳሴ ከንቱ እያቀረቡ ወደፊትም እንደ ህፃን ልጅ በጊዚያዊ ብልጭልጭ ነገር እንዳይሸውዱን እና ብሄራዊ ጥቅማችንን ለጊዚያዊ ጥቅም እያሳለፍን እንዳንሰጥ ቆም ተብሎ ቢታሰብበት ጥሩ ነው።ይሄ አካሄድ በኢትዮጵያ እንደ ልምድ እየተስፋፋ ነው።ለመልካም ስራ ሽልማት እየሰጡ እውቅና መስጠቱ ጥሩ ነው።ነገር ግን ምንጊዜም ቢሆን የተሰራው ስራ መልካም ከሆነ እራሱ ተግባሩ ሌላ መስካሪ ሳይፈልግ አፍ አውጦቶ ይመሰክራል።ከኖቤል የሰላም ሽልማቱም ይልቅ መሬት ያለው ነባራዊ እውነታ አፍ አውጥቶ ይመሰክራል።በሌላው ፅንፍ ያለውን ስናይ አብይ ለምን ተሸለሙ ብሎ ለተቃውሞ ሰልፍ መውጣት መብት ቢሆንም እንኳን ተገቢ አይደለም።ይሄን ማድረግ ዶ/ር አብይ ለሀገራቸው ዜጋ መጦፎ ስሜትን እንዲያሳድሩ በር ይከፍታል።ከሀገራቸው ብሄራዊ ጥቅም ይልቅ ጭራሽ የአለም አቀፍ ኦሊጋርኬውን አለም አቀፍ ጥቅም እንዲያስጠብቁ እድል ይፈጥራል።የውጪ ሃይሎች እንደ እኛ አይነት የታዳጊ ሀገራት መሪዎችን ከሚመሩት ህዝባቸው ነጥለው ወደራሳቸው አለም አቀፍ ኦሊጋርኬ ጎራ የሚስቡበት የተለያዩ የስነልቦናና የስሜት መቀየሪያ ታክቲኮች አሏቸው።አንዱ ዘዴ ያ መሪ ከህዝቡ የተለየ ማንነት እንዳለው አድርጎ እንዲያስብ አድርገው እየካቡ ሰማይ ያወጡታል።የራሱን እና የቤተሰቡን የህይወት ዘይቤውን እና አመለካከቱን ሁሉ ከሀገሩ ብሄራዊ ማንነት ይነጥሉና የራሳቸው አለም አቀፍ ጎራ ውስጥ ይከቱታል።ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ያ መሪ በሀገሩና በህዝቡ ላይ እንደ ባእድ የውጪ ሰው ጨካኝ ዲክታተር ይሆናል።ዶክተር አቢይ ለምን ተሸለሙ ብሎ መቃወም እሳቸውን ወደዚያ አቅጣጫ መግፋት ይሆናል።ሆኖም ግን ሽልማቱ ዶክተር አብይን የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ከማስጠበቅ ከቶውንም እንደማያዘናጋቸው ተስፋ አደርጋለሁ።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule