ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ ተጠርጥሮ በእስር ላይ የሚገኘው ጃዋር ሲራጅ መሃመድ የተከሰሰበት ጉዳይ “ፖለቲካዊ ነው፤ ይህ ችግር የሚፈታው ቁጭ ብሎ በመወያየት ነው” በማለት ለፍርድ ቤቱ ተናገረ። የወንጀል ተጠርጣሪው ጃዋር በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን ፖሊስ የጀመረውን ምርመራ ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ቀናት እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል። ከጃዋር ጋር አብሮ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎችም ተጠርጣሪዎች ሐሙስ ዕለት ነው ልደታ ምድብ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት እና አራዳ ምድብ ተረኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት። ይህንንም ተከትሎ የጃዋር ጠበቃ ደንበኛቸው በዋስ ከእስር ቤት ውጪ ሆኖ ጉዳዩን መከታተል እንዲችል እንዲፈቀድለት ጠይቀው የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ያቀረበውን የተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጥያቄ ተቀብሎታል። በዚህ … [Read more...] about በወንጀል ተጠርጣሪው ጃዋር ለፍርድ ቤቱ፤ “ጉዳዩ ፖለቲካዊ ነው፤ የሚበጀው ቁጭ ብሎ መነጋገር ነው” አለ
bekele gerba
የሃጫሉ ተኳሽ፣ አስተኳሾችና የአስከሬን ድራማ ጸሐፊ ተውኔቶች የግፍ ሥራ
የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ጸጋ ቅዳሜ ሐምሌ 5፤ 2012 ከፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጋር በሰጡት ዝርዝር ማብራሪያ የሃጫሉ ሁንዴሣ ግድያን አስመልክቶ የተቀናበረውን ድራማ አስረድተዋል። የድራማውን ጸሐፍትና የድራማ ትወናቸውንም በዝርዝር ተናግረዋል። ቃታ ሳቢው ጥላሁን (ተኳሽ) “የአርቲስቱ ግድያ ግብ ነበረው” ያሉት አቶ ፍቃዱ ጸጋ “አርቲስቱ የግድያ ዛቻ ይደርስበት እንደነበር ለጓደኞቹ ተናግሯል” ብለዋል። ወደ ግድያው አፈጻጸም ዝርዝር ትንታኔ በመግባትም ገዳዩ ጥላሁን ያሚ በሚኖርበት የገላን ኮንዶሚኒየም አካባቢ ሁለት የማያቃቸው ሰዎች ስሙን ጠርተው እንዳናገሩት ራሱ በሰጠው የእምነት ክህደት ቃል አስረድቷል። ይህንን የእምነት ክህደት ቃል የሰጠውም ሕገመንግሥታዊና የወንጀል ሕግ በሚፈቅደው መሠረት መብትና ግዴታው … [Read more...] about የሃጫሉ ተኳሽ፣ አስተኳሾችና የአስከሬን ድራማ ጸሐፊ ተውኔቶች የግፍ ሥራ
ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ
አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ በፌዴራል የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ ዘገበ። ኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ ከደቂቃዎች በፊት በሰራው ዘገባ እንዳለው ጀዋርን በቁጥጥር ሥር ለማዋል በተደረገው ጥረት የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ከፌዴራል የጸጥታ ኃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ ገብተው ነበር። በሁለቱ ኃይሎች መካከል በተፈጠረው ፍጥጫ ጉዳት ስለመድረሱ የዘገበው ኦኤምኤን ተጨማሪ ማብራሪያ ግን አልሰጠም። የፌዴራል የጸጥታ አስከባሪዎች ኃይል ጨምረው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አመራሮችን በቁጥጥር ሥር እንዳዋሉ የቴሌቭዥን ጣቢው ዘግቧል። ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ «ለጊዜው የታሰሩበት ቦታ አልታወቀም» ብሏል። በውጭ አገር የተመሠረተው እና አቶ ጀዋር መሐመድ በኃላፊነት ሲመሩት የነበሩት … [Read more...] about ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ
Tank Man 1989
የዛሬ 29 ዓመት በቻይና የታይናንመን አደባባይ የሆነውን ታሪክ ስናስብ “ታንክ ማን” ወይም በግልቡ የአማርኛ ትርጉም “ታንክ ሰው”ን እናስባለን። እናያለን። የወቅቱን ገድሉን እናስባለን። ወደ አገራችን ስንመለስ ምንም እንኳን ምንም ያልተባለላቸው ጀግኖች ያለመታወሳቸው ሊያሳዝነን ሲገባ፣ አሉ የሚባሉት ላይ መማማል መመረጡ በቃላት ሊገለጽ የማይችል የሃዘን አዙሪት ውስጥ ይከተናል። ከሁሉም በላይ ደም ሰፍረን ትርፍ እንሻለን። ለአገር ክብርና ልዕልና ያለፉትን የማይተኩ ዜጎች የግብር ማወራረጃ ለማድረግ ይዳዳናል። ህወሓት “በሞተብኝ መጠን ልዝረፍ” በሚል ቀረርቶ ል27 ዓመታት ያደነቆረንና ለዚሁ ግልብ ዓላማው የጨፈጨፈን፣ የደገንብን ታንክና አፈሙዝ፣ ያሰረን፣ ያቆሰለን፣ የገረፈን ሳያንስ ዛሬም በተመሳሳይ “የእኛ ደም” በሚል ክፍያ ሲጠየቅ ሰምተናል። ከሁሉም በላይ ደግሞ አሳዛኙና … [Read more...] about Tank Man 1989