አገራችን ከህወሓት አፋኝ የግፍ አገዛዝ ወጥታ በለውጥ ሒደት ውስጥ ትገኛለች። ሆኖም በአፋኙ ዘመነ ወያኔ እንኳን ሆኖ በማያውቅ መልኩ በአሁኑ ጊዜ አገራችንን እያፈረሰ የሚገኘው በማኅበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው የሃሰትና የፈጠራ ዜና ነው። ለዚህ ደግሞ በርካታ መዋዕለ ንዋይ እየፈሰሰ ቀንተሌት ተግተው የሚሠሩ “የሳይበር ወታደሮች” ተመድበዋል። እነዚህ በተለይ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በትጋት የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ዓላማቸው መረጃ ማዛባት፤ የሃሰት መረጃ መበተን፤ የሚወጡ መረጃዎችን ማወዛገብ (ሕዝብ እውነቱንና ሐሰቱን እንዳይለይ ማድረግ)፤ ወዘተ ናቸው። ይህ በዕዝና ቁጥጥር የሚመራ ኃይል ዋና ትኩረት የሚያደርገው በለውጡ ዙሪያ ያሉትን አመራሮች ማጠልሸት፤ የሕዝብ ድጋፋቸውን ማምከን፤ ከተቻለም ሕዝብ እንዲነሳባቸው ማድረግ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በልዩ ልዩ ረቂቅ ስልት በሚበትኑት መረጃ … [Read more...] about ዲጂታል “ወያኔ”፤ “እረኛውን ግደል፣ መንጋው ይበተናል”
Politics
አዴፓ ህወሓትን በልኩ በሚገባው ስም በመጥራት አዋርዶ ቀበረው
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት ሰባት ዓመታት የኢትዮጵያ ብቸኛ ጠላት የሆነውን ህወሓት በሚገባው ስም መጠራት አለበት በማለት በተደጋጋሚ ሲወተውት ለመኖሩ ያለፉትን ጽሁፎች መመልከቱ በቂ ግንዛቤ ይሰጣል። በመሆኑም ህወሓት (የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር) በሚለው የተገንጣይ ስሙ አገር በግፍ እየገዛ ያለ የወንበዴዎች ስብስብ ነው በማለት በዚሁ ስሙ እንዲጠራ ብዙ ብለናል። ይህ የአሸባሪዎችና በሞራል ዝቅጠት የመጨረሻው ደረጃ ላይ ባሉ ርካሾች የሚመራ የወሮበሎች ድርጅት በነጻ አውጪ ስም ኢትዮጵያን ያከለ ታላቅ አገር በንቀት እየገዛ ያለ ነው በማለት አትተናል። በመሆኑም ይህ በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች ቋት ውስጥ እስካሁን ድረስ ተመዝግቦ የሚገኝ ድርጅት መታደስ ሳይሆን መታገድና መክሰም ያለበት መሆኑንም አበክረን አሳስበናል። ይህ የእኛ ብቻ ሳይሆን የበርካቶች … [Read more...] about አዴፓ ህወሓትን በልኩ በሚገባው ስም በመጥራት አዋርዶ ቀበረው
የጄ/ል አበባው “ከፈለገ ይፈንዳ” ንግግር በትግራይ ሌላ ችግር እያፈነዳ ነው
ትግራይን የተቆጣጠሩ የቀድሞ አገዛዝ ርዝራዦች አሁንም ለዐቢይ ችግር ናቸው በባህርዳርና አዲስ አበባ በተቀናጀ መልኩ በተካሄደው የመፈንቅለ መስተዳድር/መንግሥት ህይወታቸውን ባጡት ጄ/ል ሰዓረ መኮንን አስከሬን ሽኝት ላይ በጄ/ል አበባው ታደሰ የተነገረው በትግራይ ሌላ ችግር እያፈነዳ መሆኑ ተሰማ። በአዲስ አበባ በቅድስት ሥላሴ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው የጄ/ል ሰዓረ ቀብር ትግራይ መደረጉ ይህንኑ ተከትሎ ለተነሳው “እሣት” ማዳፈኛ ይሆን ዘንድ ለፖለቲካ ፍጆታ የዋለ መሆኑ ተገለፀ። በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር መ/ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ኃላፊው ቲቦር ኒጌይ ትግራይ የመሸጉ የህወሓት ርዝራዦች አሁንም ለጠ/ሚ/ር ዐቢይ ችግር ፈጣሪዎች እንደሆኑ ተናገሩ። ህወሓትን በአደባባይ እንደሚያገለግል እየተናገረ መከላከያውን በኤታማዦር ሥልጣን ለረጅም ዓመታት ሲመራ የነበረው ሳሞራ የኑስን … [Read more...] about የጄ/ል አበባው “ከፈለገ ይፈንዳ” ንግግር በትግራይ ሌላ ችግር እያፈነዳ ነው
ኦነግ በአማርኛ መግለጫ ባወጣ ጥቂት ቀን “ትጥቃችንን ለኦሮሞ ሕዝብና ለአባ ገዳዎቻችን አስረክበናል” አለ
ኢትዮጵያን “አቢሲኒያ ኢምፓዬር” በማለት ሲጠራ የኖረውና ራሱን የኦሮሞ ነጻአውጪ ግምባር ብሎ የሰየመው “ኦነግ” አቢሲኒያ ከሚላት ኢትዮጵያ ለመገንጠል ብቻ ሳይሆን አማርኛንም እንደ ጨቋኝ ቋንቋ በመቁጠር በዚያ ከመጠቀም ተቆጥቦ መኖሩ የሚታወቅ ነው። ለአብነት ያህል በቅርቡ ወዳገር ቤት የገቡት ገላሳ ዲልቦ እነ መለስ በጠሩት የሽግግር መንግሥት ምሥረታ ወቅት በእንግሊዝኛ ሲናገሩ ሌንጮ ለታ ከጎናቸው በመሆን በኦሮሚኛ ያስተረጉሙ ነበር። አሁን ደግሞ እኚሁ ገላሳ ዲልቦ በየሚዲያው በአማርና ቃለምልልስ ብቻ ሳይሆን ቅኔም ሲዘርፉ ሰምተናል። በግሩም የአማርኛ ብሒል የታጀበውና “ግመል ሰርቆ ኣጎምብሶ” ኣይደበቅ ነገር በሚል ርዕስ የወጣው የኦነግ መግለጫ ያተኮረው መንግሥት ምዕራብ ወለጋን በአየር ስለመደብደቡ የጠ/ሚ/ሩ ፕሬስ ክፍል (እንግሊዝኛ) ቢልለኔ ስዩም ማስተባበላቸውን ተከትሎ … [Read more...] about ኦነግ በአማርኛ መግለጫ ባወጣ ጥቂት ቀን “ትጥቃችንን ለኦሮሞ ሕዝብና ለአባ ገዳዎቻችን አስረክበናል” አለ
ከቅዳሜው የህወሓት ሰልፍ በፊት በትግራይ “ከዓቅም በታች የሰረቁ” ተፈረደባቸው
ቅዳሜ በህወሓት አስገዳጅነትና ተለማማጭነት አሁን በመላው ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ለውጥ የመቃወም እንደምታ ያለው ሰልፍ ተጠርቷል። እስካሁን ድረስ በርካታ መረን የወጣ ሌብነት የፈጸሙ፣ እጅግ አሰቃቂ የሰብዓዊ መብቶችን የጣሱና ሌሎች ተፈላጊ ወንጀለኞችን በትግራይ ደብቆ የያዘው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) በኤፈርት አልባሽነት ቅዳሜ "ሰላማዊ" ያለውን ሰልፍ በመቀሌ፣ ትግራይ ጠርቷል። ሌብነትን እንቃወማለን ለማለትም በአንዳንዶች ዘንድ “ከዓቅም በታች የሰረቁ” የተባሉ አነስተኛና ጥቃቅን ሌቦች ላይ ፍርድ አስተላልፏል። የመቀሌ ከተማ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ዘመንፈስቅዱስ ፍሰሃን ጠቅሶ ኢዜአ እንደዘገበው የሰልፉ አንዱ ዓላማ “ህገመንግሥቱ ይከበር” የሚል ነው ብሏል። ይህ በህወሓት አነጋገር ከአንቀጽ 39 ጀምሮ በርካታ ነገሮችን ሊያስብል የሚችል አገላለጽ፤ ህወሓት ከሁለት ዐሥርተ … [Read more...] about ከቅዳሜው የህወሓት ሰልፍ በፊት በትግራይ “ከዓቅም በታች የሰረቁ” ተፈረደባቸው
የትግራይ ህዝብ ሆይ፦ “ሀገርና ህዝብ ከህወሓት በፊት ነበሩ፣ ከውድቀቱም በኋላ ይኖራሉ!”
በመጀመሪያ ደረጃ “የትግራይ ህዝብ” ስል ከኢትዮጵያ ህዝብ በተዘረፈ ሃብት የቅንጦት ህይወት የሚኖሩትን፣ በስርቆት ሃብት አጉል የሚቀብጡትን የካድሬ ልጆችና ወዳጆች አይመለከትም። “የትግራይ ህዝብ” ስል በህወሓት ድጋፍና ድጎማ የሚኖሩ የድርጅቱን አባላትና ፅንፈኛ ደጋፊዎች አይመለከትም። የእነዚህ ሰዎች ስኬት እና ውድቀት፣ ድህነት እና ሃብት፣… በአጠቃላይ ሁሉ ነገራቸው ከህወሓት ጋር የተቆራኘ ስለሆነ የድርጅቱ አመራሮች የደገፉትን ይደግፋሉ፣ የተቃወሙትን ይቃወማሉ። የእነሱ ዕለት-ከእለት ኑሮ ከህወሓት መኖርና አለመኖር ጋር የተቆራኘ ስለሆነ ህወሓት የህልውናቸው መሰረት ነው። በእርግጥ እነዚህ ሰዎች የትግራይ ተወላጆች ናቸው። ነገር ግን እነዚህ ሰዎች “የህወሓት አፈ-ቀላጤዎች” እንጂ “የትግራይ ህዝብ” ሊሆኑ አይችሉም፤ እነሱ የህወሓት ካድሬዎች እንጂ የትግራይ ህዝብ አይደሉም! ከዚያ … [Read more...] about የትግራይ ህዝብ ሆይ፦ “ሀገርና ህዝብ ከህወሓት በፊት ነበሩ፣ ከውድቀቱም በኋላ ይኖራሉ!”
በኮሞሮስ ባንዲራ የሚቀዝፉት የሜቴክ መርከቦች እና በካሪቢያን ስም የምትቀዝፈው የኢትዮጵያ መርከብ
የፌደራል ዋና አቃቢ ህግ ሜቴክ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጪ በገዛቸው ሁለት መርከቦች አማካኝነት በህግወጥ የንግድ እንቅስቃሴ መሰማራቱን ገልፆ እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም ግን በሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜ/ጄ ክንፈ ዳኘው ላይ የቀረበው ክስ ድርጅቱ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጪ አባይ እና ህዳሴ የተባሉትን ሁለት መርከቦች በመግዛት ከፍተኛ የገንዘብ ብክነት የሀገርና ህዝብን ሃብት ያለ አግባብ አባክኗል የሚል ነው። ሆኖም ግን ለድረገፃች አዘጋጅ በደረሰው መረጃ መሠረት ሜቴክ የገዛቸው ሁለት መርከቦች እ.አ.አ. እስከ 02 – 07/-01-2016 በምስራቅ አፍሪካዊቷ የኮሞሮስ (Comoros) ደሴት ሰንደቅ ዓላማ አያውለበልቡ በህገወጥ ንግድ ተሰማርተው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ በቀረበው የቴሌቪዥን ዶክመንተሪ ሜቴክ እ.አ.አ. በ2014 ዓ.ም አባይ እና ህዳሴ የተባሉን መርከቦች … [Read more...] about በኮሞሮስ ባንዲራ የሚቀዝፉት የሜቴክ መርከቦች እና በካሪቢያን ስም የምትቀዝፈው የኢትዮጵያ መርከብ
አማራና ትግራይ ክልሎች ከቃላት ጦርነት ወደ መሣሪያ መማዘዝ?
ሰሞኑን በአማራና በትግራይ ክልል መካከል የተፈጠረው የመግለጫ እሰጥ አገባ ከቃላት ጦርነት ወደ መሣሪያ መማዘዝ እንዳይቀየር ፍርሃቻ አለ። የኤርትራው መሪ ኢሳያስ አፈወርቅ ወደ አማራ ክልል ለጉብኝት መምጣታቸው በህወሓት አቀንቃኞች ዘንድ በፍርሃቻ እየታየ ነው፤ ሌሎች የዘር ፖለቲካ አራማጆች ደግሞ ጉብኝቱን ስህተት ነው ብለውታል። የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅና የሱማሌው ፕሬዚዳንት ሙሐመድ አብዱላሂ ፎርማጆ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ግብዣ ዛሬ በአማራ ክልል ጉብኝት ለማድረግ ጎንደር ገብተዋል። ይህ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ጉብኝት የጎንደርና አካባቢውን ታሪካዊ ቦታዎች ለመመልከትና በባህር ዳር ውበት ለለመሰጥ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። በተለይ ኢሳያስ በተደጋጋሚ በትግራይ አመራር ላይ ካሉት የህወሓት ሰዎች የቀረበላቸውን የወዳጅነት ጥያቄ ችላ በማለት ከህወሓት ጋር … [Read more...] about አማራና ትግራይ ክልሎች ከቃላት ጦርነት ወደ መሣሪያ መማዘዝ?
“ጋትሉዋክና ተባባሪዎቻቸው በሙሉ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው” የክልሉ ነዋሪዎች
ላለፉት ሰባት ዓመታት የጋምቤላ ሕዝብ አንድነት ዴሞክራሲዊ ንቅናቄ (ጋሕአዴን) ሊቀመንበርና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት ጋትሉዋክ ቱት ከፓርቲው ሊቀመንበርነታቸው “በፈቃዳቸው” ለቅቀዋል። ከእርሳቸው ጋር አብረው ምክትላቸው ሰናይ አክዎርም ከፓርቲው ምክትል ኃላፊነታቸው እንደዚሁ በፈቃዳቸው ለቅቀዋል። በምትካቸው የክልሉ የሥነምግባርና ጸረ-ሙስና ኃላፊ ዑመድ ዑጁሉ ሊቀመንበር፤ የጋትሉዋክ ሚስት ወንድም የሆኑትና የክልሉ የንግድ ቢሮ ኃላፊ ታንኩዌይ ጆክ ሮምን ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል። የክልሉ ነዋሪዎች ምርጫውን “የቀድሞ ደጃዝማቾች ካባቸውን አውልቀው ለሚፈልጉት በመስጠት እንደሚሾሙት ጋትሉዋክም ለዘመዱ የስልጣኑን ካባ ያጎናጸፈበት ቀልድ ነው” ሲሉ አውግዘውታል፤ ይልቁኑም ጋትሉዋክ ቱት በበርካታ ወንጀሎች የሚጠረጠሩ ስለሆነ ሌሎቹንም አመራሮች ጨምሮ ሁሉም “ለፍርድ መቅረብ … [Read more...] about “ጋትሉዋክና ተባባሪዎቻቸው በሙሉ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው” የክልሉ ነዋሪዎች
ኮ/ል ጎሹ ወልዴ አዲስ አበባ ገቡ
በደርግ ዘመነ መንግሥት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የትምህርት ሚኒስትር የነበሩት ኮ/ል ጎሹ ወልዴ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂሩት ዘመንና እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ነብያት ጌታቸውን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርግውላቸዋል። የቀድሞው ሚኒስትር በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የደርግን አገዛዝ በመቃወም ሃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው ከለቀቁና ኑሯቸውን በአሜሪካ ካደረጉ ጀምሮ ላለፉት 32 አመታት የአገራቸውን መሬት ሲረግጡ የመጀመሪያቸው መሆኑን ገልፀዋል። ኮ/ል ጎሹ ወልዴ አመጣጣቸው የአገሪቱን አጠቃላይ የለውጥ ሂደት ለማየት፣ ለረጅም ጊዜ የናፈቋቸውን ዘመድ ወዳጆች ለማግኘትና የተጀመረውን የሰላም፣ የፍቅርና የመደመር ሂደት በሚችሉት መጠን … [Read more...] about ኮ/ል ጎሹ ወልዴ አዲስ አበባ ገቡ










