የህወሓት ዘመን ማብቂያው አካባቢ ኃይለማርያም ደሳለኝ “ከሥልጣኔ ለቅቄአለሁ” ካለ በኋላ ለጠ/ሚ/ር ቦታ በተደረገው ሽኩቻ ዶ/ር ዐቢይ (የለማ ቡድን) አሸንፎ በወጣ ጊዜ የህወሓት ቡድን ወደ መቀሌ ሄዶ ሲመሽግ ስብሃት ነጋ በተፈጠረው ተናድዶ የሚከተለውን መናገሩ ታማጭ የመረጃ ምንጫችን አስታውቆናል። ስብሃት ነጋ በትግሪኛ የተናገረውና በአማርኛ ተተርጎመው የስብሃት ንግግር እንዲህ ይነበባል፤ “(ደመቀ) ለትህነግ ታማኝና ታዛዥ ነበር። ፈፅም! የተባለውን ነገር ለመፈፀም 'ለምን?' ብሎ እንኳን አያውቅም። አንድ ቀን ግን የሱዳን ግዛት የሆነውን አዋሳኝ መሬት ለመስጠት ‘ፈርም’ ሲባል ‘አይሆንም አልፈርምም!’ ብሎ አሻፈረኝ ሲል ያኔ ይህ ሰው አንድ ቀን እንደሚሸውደን እርግጠኛ ሁኜ ለጓዶቼ ነግሬያቸው ነበር። ሁሉም የእኔን እይታ ሳያቅማሙ ሲቀበሉኝ ጌታቸው (አሰፋ)ግን ‘አታስብ እሱ … [Read more...] about ስብሃት ነጋ ስለ ደመቀ መኮንን፤ “ደመቀ የሸወደንን ያክል መሰሪው ጀበሃ (ሻእቢያ) እንኳን አልሸወደንም!”
Politics
ህወሓት/ትህነግ በአጥር ላይ
ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትህነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የተገንጣዮች ጥርቅም፤ አዲስ የተመሠረተውን ብልጽግና ፓርቲ አልቀላቀልም ብሎ ካፈነገጠ ወዲህ ሁኔታዎች መስመር እየለቀቁበት ነው። ላሁኑ አጥር ላይ መንጠልጠሉን አማራጭ አድርጓል። እስካሁን በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኘው ትህነግ/ህወሓት መሪ የነበረው መለስ በሥልጣን በቆየበት ዘመን ሲዘልፋቸው የኖረውን ተቃዋሚዎች ባንድ ወቅት እንዲህ ብሏቸው ነበር፤ አጥር ላይ መሆንና አንድ እግር ከግቢ ውስጥ ሌላኛውን ከውጭ ማድረግ አይቻልም። በአሁኑ ወቅት ህወሓት ያለችበት ወቅታዊ ሁኔታ የመለስን አጽም ካላበት ቦታ እንዲላወስ ያደረገ ሆኗል። አንድ እግሯ መቀሌ፤ ሌላው እግሯ አዲስ አበባ … [Read more...] about ህወሓት/ትህነግ በአጥር ላይ
ህወሓት/ትህነግ ጊዜ እንዲሰጠው የሚጠይቅ “ስልታዊ” ውሳኔ አሳለፈ
"ሳይወሰንልኝ" አልሳተፍም አለ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ/ህወሓት በቀጥታ መቃወሚያ ሳያቀርብ የኢህአዴግ እህትና አጋር ድርጅቶች እንዲዋሃዱ በሚወሰንበት የግንባሩ ጉባዔ ላይ ለመገኘት ፈቃድ አለማግኘቱን አስታወቀ። ይህንኑ የሚጠበቅ ውሳኔ ይፋ ሲያደርግ በተዘዋዋሪ ቀን እንዲሰጠው መጠየቁንና አሁንም ተጨማሪ ጊዜ እንደሚፈልግ ማብራሪያ ያላቀረበበትን የህግና የፖለቲካ ጉዳይ አስታኳል። በህዳር 6 ቀን 2012 የግንባሩ ሥራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ላይ በውህደቱ አጀንዳ በድምጽ ተሸንፎ የወጣው ህወሃት የሶስት ቀን ተጨማሪ ጊዜ መጠየቁን ከስብሰባው ማግስት በኋላ ሲያስተባብል የቆየው ትህነግ፣ ዛሬ ባሰራጨው መግለጫ “የትህነግ ማእከላዊ ኮሚቴ በጥናቱ ላይ እንዲወያይ ተወስኖ እያለ ምንም ዓይነት ውይይት ሳይደረግ በጥድፊያ የምክር ቤት ስብሰባ ማድረግ ተገቢ … [Read more...] about ህወሓት/ትህነግ ጊዜ እንዲሰጠው የሚጠይቅ “ስልታዊ” ውሳኔ አሳለፈ
ህወሓት እንቅጩን ተናገረ!!
ሦስቱ ፓርቲዎችና አጋር ድርጅቶች አቋማቸውን ግልጽ አድርገዋል ህወሃት “በሁሉም መለኪያዎች አንድ ፓርቲ ለመሆን የሚያስችል መነሻና ምክንያት በሌለበት ኢህአዴግን አፍርሶ ሌላ ፓርቲ ለማቋቋም ማሰብ አገርን የሚበትን ተግባር ነው” ሲል ጉዳዩ የሞት ሽረት መሆኑንን አስታውቋል። አሁን ግጭት እየተባባሰ የሄደውም በዚሁ ምክንያት ነው ሲል አክሏል። እስከ ዛሬ ከውህደት ተገለው የነበሩ አጋር ድርጅቶች በኢህአዴግ ሥር ተጠቃለው እንዲቀጥሉ ምኞቱን ያኖረው ህወሃት፤ አጋር ፓርቲዎች ስለምን ተገለው እንደቆዩ ቁጭቱንም ሆነ ምክንያቱን በመግለጫው አላካተተም። ሰሞኑንን አጋር ፓርቲዎች ሙሉ በሙሉ፣ ሶስቱ እህት ድርጅቶች ውህደቱን እንደሚደግፉና እንደሚቀላቀሉ ይፋ ማድረጋቸውን በድጋፍም ሆነ በነቀፌታ ያላስቀመጠው የህወሃት መግለጫ “ውህደቱ አገር ያፈራርሳል፣ ፍፁም ፀረ-ዴሞክራሲያዊ” ከማለት … [Read more...] about ህወሓት እንቅጩን ተናገረ!!
ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ከአፍሪኮም ዕዝ አዛዥ በተነጋገሩ ማግስት አሸባሪው ህወሓት አሸባሪዎችን እያሠለጠነ መሆኑ ተሰማ
የኢትዮጵያ መንግሥት ባፋጣኝ እርምጃ ሊወስድ ይገባል ተብሏል ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትሕነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የወንበዴዎች ጥርቅም፤ እስካሁንም በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኘው አሸባሪው ህወሓት አሸባሪዎችን እያሠለጠነ መሆኑ ተሰማ። መረጃው የአፍሪኮም አዛዥ ከጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ጋር ከተመካከሩ በኋላ መውጣቱ የጉዳዩን አሳሳቢነት ብቻ ሳይሆን አቅጣጫ ጠቋሚም ነው ተብሏል። “ከባድ ሚስጥራዊ መረጃ፡- ጄ/ል ሳሞራ ዬኑስ በሱዳን 8ሺህ ወታደር እያሰለጠኑ ነው!” በማለት Ethiopian Think Thank Group የተሰኘው ድረገጽ ዛሬ ባስነበበው መሠረት መረጃው የተገኘው ከደኅንነት ሠራተኛ መሆኑን ተናግሯል። … [Read more...] about ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ከአፍሪኮም ዕዝ አዛዥ በተነጋገሩ ማግስት አሸባሪው ህወሓት አሸባሪዎችን እያሠለጠነ መሆኑ ተሰማ
የኢትዮጵያን የ6 ½ ዓመት በጀት የሚሸፍን ገንዘብ በህወሓት ዘመን ተዘርፏል
ኢትዮጵያ ባለፉት 30 ዓመታት 30 ቢሊዮን ዶላር ተዘርፋለች! ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን ከመጣ ጀምሮ 30 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከኢትዮጵያ በሕገ ወጥ መንገድ መሸሸቱንና ገንዘቡንም ለማስመለስ መንግሥት ከባድ ሥራ ከፊቱ እንደሚጠብቀው ምሁራን ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ከሀገር የሸሸውን ገንዘብ ለማስመለስ ከፍተኛ ጥረት ቢጠይቅም መንግሥት ጉዳዩን እንደሚከታተለው አሳውቀው የነበረ ቢሆንም ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዳልታዬ ምሁራኑ ገልጸዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት ምሁሩ ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገዳ እንደገለጹት በኢህአዴግ ዘመነ አገዛዝ ከኢትዮጵያ ወደተለያዩ ሀገራት በሙስና እና ማጭበርበር የሸሸው ገንዘብ 30 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደሚደርስ በጥናት ተረጋግጧል፤ ገንዘቡም በወቅቱ የኢትዮጵያን የስድስት ዓመት ተኩል በጀት መሸፈን የሚችል … [Read more...] about የኢትዮጵያን የ6 ½ ዓመት በጀት የሚሸፍን ገንዘብ በህወሓት ዘመን ተዘርፏል
የጃዋር ሰለባዎች በሱ መመሪያ የተጨፈጨፉት ብቻ ሳይሆኑ ሚዲያውም ጭምር ነው
የሚዲያ አውታሮች ከውስጥም ከውጭም፣ የመንግሥትም ሆኑ የግል፣ የተገዙም ሆኑ በሊዝ የተያዙ፣ በደመ ነፍስ የሚጓዙትን ጨምሮ ሆን ብለው አስበውበትም ሆነ ሳያውቁት የጃዋር ሰለባና አንደበት ሆነዋል። አንዳንዶቹ በሳል የሚባሉት የሚዲያ አውታሮች ተቆጣጣሪ ኤዲቶር ያላቸውም አይመስሉም። “በድንገት በጃዋር ላይ በለሊት ከበባ መደረጉን ተከትሎ” እያሉ እሳቱ ላይ ነዳጅ ያርከፈክፋሉ። የዘገቡ መስሏቸው የጃዋር አፈቀላጤ በመሆን በትጋት ያገለግላሉ። ጃዋር “ተከበበ ” የተባለው በማን ነው? ማን ከበበው? እንዴት ተከበበ? ስንት ሠራዊት ከበበው? ለምን ተከበበ? በሚል ማጣራቱ ቢቀር እሱ ያለውን ጠቅሶ መዘገብ እንዴት ለአንድ ሚዲያ ይከብዳል? ከደረሰው ዘግናኝ ጭፍጨፋና ቁሳዊ ጥፋት ለማምለጥ እየዋለ ሲያድር ከሚባለው ውጪ “በሌሊት ጠባቂዎቼ እንዲነሱ ታዘዘ” የሚለውን ጠቅሶ ለመዘገብ ያልተቻለበት … [Read more...] about የጃዋር ሰለባዎች በሱ መመሪያ የተጨፈጨፉት ብቻ ሳይሆኑ ሚዲያውም ጭምር ነው
ጃዋር፤ ለኦሮሚያ የተጠመደ ፈንጂ!
“… ስሙን መጥቀስ ባያስፈልግም አንድ ጎረምሳ ልንለው እንችላለን። ጃዋር ዜግነቱ አሜሪካዊ በመሆኑ የጃዋር ሚዲያ የተመዘገበው በዚህ ጎረምሳ ስም ነው። ከየአቅጣጫው የሚሰበሰበው ገንዘብ የሚቀመጠው በዚሁ ልጅ ስም ነው። መኪኖችና አንዳንድ ንብረቶች የሚገዙትም በዚሁ ስም ነው። ይህ ጎረምሳ አዲስ አበባ እጅግ መንዛሪና በከፍተኛ ቅንጦት እንደሚኖር የሚያውቁት ነገረውኛል። የቄሮ አካልም አልነበረም። ቄሮ ከድል በኋላ ቤቱ ሲመለስ የጠበቀው ማሳውና መደቡ ሲሆን እነ ጃዋርና ስማቸውን የሚጠቀሙባቸው ጎረምሶች በሚሊዮኖች እየረጩ ዘመናዊ ተሽከርካሪ ይሸምታሉ፤ ንብረት ያከማቻሉ፤ ሰዎች ሰላም ሰፍኖ በተረጋጋ መልኩ እንዳያስቡ ቀውስ ይመረትላቸዋል። ልክ ከዚህ በፊት ተደርጎ እንደማይታወቅ በዓሉንም፣ ልደቱንም፣ በሚዲያ እያስጮሁ ያሳብዱታል። ይህ ወጣት የሰከነ ዕለት ለጃዋር የሚቀርብለት ጥያቄ ስለሚታወቅ … [Read more...] about ጃዋር፤ ለኦሮሚያ የተጠመደ ፈንጂ!
“ድንቁርና እና ዘረኝነት ሲደባለቅ እሳት ነው፤ አገር ያፈርሳል”
“ኢትዮጵያ የሚለው መጠሪያ እንዲያስፈራ ተደርጎ ተሰርቷል” በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የሚገኙት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ሐምሌ 26/2011ዓም ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋዜጠኛ ምህረት ሞገስ ጋር ቃለምልልስ አድርገዋል። “ድንቁርና እና ድህነት እሳት ነው፤ አገር ያቃጥላል” በሚል ርዕስ የወጣውን ቃለምልልስ ከዚህ በታች አስፍረነዋል። በዚህ ጥያቄና መልስ አቶ ኦባንግ ወሳኝ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መልሶችን ሰጥተዋል፤ ጎሰኝነትን፣ ብሔረተኝነትን፣ ኢትዮጵያዊነት፣ ወዘተ በመሳሰሉ ርዕሶች ላይ ሊነበብ የሚገባው መልሶችንና ዕምነታቸውን ተናግረዋል። አዲስ ዘመን፡– የካናዳ የትምህርት ህይወት እንዴት … [Read more...] about “ድንቁርና እና ዘረኝነት ሲደባለቅ እሳት ነው፤ አገር ያፈርሳል”
የወቅቱ የአገራችን ችግር፤ የሐሰት ዜና ወረርሽኝ!
በኢትዮጵያ ደረጃ የሚታየው መድረሻውን ያስቀመጠ የሀሰተኛ መረጃ ሻሞ ወይም እርባታ ሕዝብን እንደ ዋዛ እያሳከረ፣ አገርን ለአደጋ የሚዳርግ፣ ታስቦበት፣ በዕቅድ፣ በባለሙያ፣ በበጀት፣ በድርጅት፣ በመሪ፣ በሥልጠና የሚከናወን የዘመኑ የዲጂታል ጦርነት ነው። ሰሞኑን የፓሪስ ከተማ ክፉኛ ተንጣ ነበር። የናጣት በማኅበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ አንድ ሐሰተኛ መረጃ ሲሆን፣ መረጃው “የፓሪስ ውሃ ተመርዟልና አትጠጡ” የሚል የጅምላ ጥሪ ነበር። መረጃው የነፍስ ጉዳይ በመሆኑ የከተማዋን ነዋሪዎች ክፉኛ ናጣቸው። ይህንን አሸባሪ መረጃ ለመከላከል የፓሪስ አካባቢ ኃላፊዎች መግለጫ እንዲሰጡ አስገደዳቸው። በመሆኑም አርብ ሐምሌ 12፤ 2011 (ጁላይ 19) ተመረዘ የተባለው ውሃው እንደተባለው እንዳልተመረዘና ለመጠጥም ቢሆን ምንም የማያሰጋ መሆኑን አስረግጠው ተናገሩ። ይህ የሐሰት መረጃ ፓሪስን … [Read more...] about የወቅቱ የአገራችን ችግር፤ የሐሰት ዜና ወረርሽኝ!










