• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢትዮጵያ በ2032

December 4, 2019 07:29 am by Editor 1 Comment

የምንፈልጋት ኢትዮጵያ በ2032 በሚል ርእስ ሀገር አቀፍ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ሀገር አቀፍ የውይይት መድረኩን በፎረም ኦፍ ፌዴሬሽን እና ዴስትኒ ኢትዮጵያ ኢኒሼቲቭ ናቸው በጋራ ያዘጋጁት።

በመድረኩ ላይም የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮ የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች እና ምክትል ርእሳነ መስተዳድሮች፣ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በተጨማሪም የበርካታ ሀገር አቀፍ እና ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና ተወካዮችም በመድረኩ ላይ ተሳትፈዋል።

መድረኩ የሀገሪቱን የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን በማቀራረብ የወደፊት የሀገሪቱ እጣ ፈንታ ላይ ለመወያየት በማለም የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

የመድረኩ ተሳታፊ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮችም፤ በመድረኩ ደስተኛ መሆናቸውን በመግለፅ፤ አሁንም ለኢትዮጵያ በርትተው እንዲሰሩ እድል የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል።

የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና ተወካዮቹ ከዚህ ቀደም በዚህ መድረክ ስር በጋራ በነበራቸው ቆይታ ስለ ሀገሪቱ ፖለቲካ በስፋት መምከራቸውን እና በሀገሪቱ የሚስተዋሉ ችግሮች በውይይት ብቻ የሚፈቱ እንደሆኑ ከመግባባት መድረሳቸውን አስታውቅዋል።

የኢዜማ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፥ መድረኩ በሀገር ጉዳይ ሁሉም በንግግር የሚፈታ መሆኑን ልምድ የተገኘበት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የአብን ሊቀ መንበር ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ፥ መድረኩ የተራራቀ አቋም ያላቸው የፖለቲካ ሀይሎችን ያቀራረበ መሆኑን ተናግረዋል።

በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ምንም አይነት የተራራቀ የአቋም ልዩነት ቢኖርም፤ በመቀራረብ እና በመወያየት የማይፈታ ነገር እንደሌለ ያስተማረ መድረክ መሆኑን ተቅሰዋል።

የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳም፥ “መድረኩ መጀመሪያ ሲጀመር ውጤቱ ላይ ጥርጣሬ ነበረኝ፤ ወደ ስራ ስገባ ግን ቀስ በቀስ በመነጋገር፣ በመወያየትና በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ መፈለግ እንደሚቻል ልምድ ያገኘሁበት ነው” ብለዋል።

የአዴፓ ተወካይ ዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል፥ “በመድረኩ በጋራ በመሆን ሀገርን፣ የዴሞክራሲ ስርዓትን፣ መንግስትን እና ኢኮኖሚን መገንባት እንደሚቻል አረጋግጫለሁ” ብለዋል።

የሀገር ሽማግሌ ተወካዮችም በመድረኩ ላይ መድረኩ ለኢትዮጵያ መፃኢ እድል በር የሚከፍት መሆኑን በመግለጽ፤ ለኢትዮጵያ ስንል ሁላችንም ዝቅ ብለን እንስራ ሲሉ መናገራቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

በመድረኩ ላይም ከ50 በላይ የተቋማት መሪዎች በኢትዮጵያ የወደፊት እጣ ፈንታ ዙሪያ ንግግር እንደሚያደርጉም ነው የተገለፀው። (ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ)

Filed Under: News, Politics Tagged With: ethiopia 2032, Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Ashebir says

    December 12, 2019 08:12 pm at 8:12 pm

    በኔ ግምት ሰው ለውይይት ሲተጋ የመጀመሪያ ጥረቱ መሆን ያለበት ለውይይት መክንያት የሆነውን ችገር አንጥሮ በማውጣት፤ የውይይቱ ተሳታፊ በሙሉ ነጥሮ በወጣው ችግር ላይ መስማማት ያስፈልጋቸዋል። ችግሮች ብዙ ሊሆኑ ይችላሉ። ሁሉም ችግሮች ባንድ ጊዜ ባንድ መንገድ ይፈታሉ ማለትም አይደለም። ነገር ገን ከችግሮቹ ውስጥ መጀመሪአ መፈታት ያለበት የቱ ነው በማለት ችግሮቹን በቅደም ተከተል ዘርዝሮ ማስቀምት ያስፈልጋል። እስካሁን ባየሁዋቸው ውይይቶች ላይ ኡሉ እንዳቸውም በጋራ የትስማሙበትን ችግር አንጥረው አውጥተው ከፊታቸው በማስቀመጥ አይደለም በእውነት እንነጋግር ካልን ውይይት የሚያልቀው ላልታውቅ ችግር መፍትሄ በማፈላለግ ጊዜው የሚያልቀው። ምሳሌ ኮሌጆ ትማሪዎችን ጉዳይ በንውሰ ካማራ አገር የመጣው ተማር ለምን ኦርሞ አገር ይገደላል? ከአኦሮሞ ኧርስ የመጣው ተማሪ ለምን አማራ አገር ይገደላል ለሚለው ጥያቄ ተስብስበው የነብሩ ሊሂቃን ምክንያቱን አንትሮ አውጥቶ ከማውጣትና ለዚያ መፍትሄ ከምውፈለግ ይልቅ፤ ወላጆች ልጆቻችሁን ምከሩ፤ ተማሪዎችም ተምራችሁ ትልቅ ስው እንድትሁኑ ትምሕርታችሁን አጠናክሩ … ውዘት ንው። ጥያቄው ታድያ በርግጥ ተማሪዎቸ ትምህርታቸውን አለማጥናከራችው ነው የግድያው ክንያት? ዝውላጆቸ ልጆቻቸው አለመምከርም ምክንያት መሆኑ እንዴት ታወቀ?

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule