“ግድያ ከተፈጸመ በኋላ አስከሬኖችን ለመቀጣጫ ተጠቅመዋል” አሉ ፕሮፌሰር ጌታቸው። ሲያስረዱም “ገድለው የሰውነትን ክፍል በመበጣጠስ ሜዳ ላይ ጥለዋል። ይህ የሆነው አንተም እንዲህ ትሆናለህ፣ ለቀህ ጥፋ፣ ሂድ፣ የሚል የመቀጣጫ ማሳያ ለመጠቀም ሲባል ነው። ይህንን ያዩ፣ የፈሩ ቤተክርስቲያን ተሸሸጉ፣ ጫካ ውስጥ ተጠለሉ። ወደ ማይታወቅ ቦታ አመለጡ”።
ይህ የተባለው ትግሉን አጠናቆ ወደ ቤቱ የገባውና አደረጃጀት የሌለው መስዋዕትነት የከፈለውን ቄሮ ሳይሆን በጃዋር መሃመድ የሚመራ፣ ከፍተኛ ገንዘብ የሚያዘዋውር፣ የተደራጀ፣ ትዕዛዝ አመንጪ ያለው፣ አዛዥና የዕዝ ሠንሠለት ያለው፣ የማዘዣ ኮማንድ የተበጀለት … የጥፋት ኃይል በአሸባሪነት እንዲፈረጅ ጥያቄ በቀረበበት ወቅት ነው።
በማስረጃ ተደግፎ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ክስ የቀረበበት ይህ ኃይል በአሸባሪነት እንዲፈረጅና ዓለም ይህ ድርጅት ምስራቅ አፍሪቃን ሳያተራምስ እንዲከስም አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥበት፣ ጉዳዩ አሳሳቢና ጊዜ የማይሰጥ መሆኑንን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ለተመድ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ተጠሪዎች ማብራራቱን ይፋ አድርጓል።
ከመረጃ ቲቪ ባልደረባ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌና እስክንድር ነጋ እንዳሉት የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለቀረበለት ጥያቄ ቀና የሚባል መልስ ሰጥቷል። ከቀረበለት ማስረጃ በተጨማሪ ጉዳዩን በራሳቸው አግባብ እንደሚያጣሩና አስቸኳይ ምላሽ እንደሚሰጥ ማስታወቁን ገልጠዋል።
በኢትዮጵያ ተመድ ያስቀመጣቸው የጄኖሳይድ ጥቃት ስለመኖሩ ማስረጃ፣ ሰለባዎች በማንና እንዴት እንደተጠቁ በሰነድና በመረጃ መቅረቡን ያመለከተው እስክንድር የአልሸባብ፣ የሙጃሂድና የአልቃይዳን አፈጣጠር ለምሳሌነት መነሳቱን ጠቁሟል።
የተመድ ባለሥልጣናት ስማቸው እንዳይጠቀስ በማስገንዘብ ጉዳዩን በውል እንደሚያዩት ፕሮፌሰር ጌታቸው ተናግረዋል።
ከተመድ ጋር የተደረገው ውይይት ኢትዮጵያውያን በዋሽንግቶን ዲሲ ተወያተው ያሳለፉት ውሳኔ አካል እንደሆነ ያስታወሰው እስክንድር፣ ጃዋር የሚመራው ቄሮ የፈጸመውን የዘር ማጽዳት ወንጀል የሚያጣራ ግብረኃይል መቋቋሙንና ይህም ግብረኃይል ተጨማሪ መረጃዎችን በማሰባሰብ ለባለሥልጣናቱ ተጨማሪ ግብዓት እንደሚያቀርብ ጠቁሟል።
“ጤናማ ቄሮ አለ፣ ጽንፈኛ ቄሮ አለ። ጤማዎቹ ትግላቸውን ጨርሰው ወደ ቤታቸው ገብተዋል” ሲል ማብራሪያውን የሰጠው እስክንድር፣ አሁን በጽንፈኛነት የተሰማራው ኃይል ድርጊቱን ሲፈጽም “ቄሮ ነኝ” እያለ ራሱን በመግለጽ በመሆኑ በሌላ ስም ሊጠራ እንደማይችል አመልክቷል። መሪውም ጃዋር መሆኑንና ከመንግሥት እና (ከፓርቲ) መዋቅር ውስጥም ተባባሪ እንዳላቸው አክሏል።
ፕሮፌስር ጌታቸው እንዳሉት ይህ ኃይል የራሱ ሚዲያ ያለውና የጥፋት ጥሪውን በዚሁ ሚዲያው እንደሚያሰራጭ፣ ባለቤቱም የዚሁ ኃይል መሪ እንደሆነ ጠቁመዋል። ይህንንም በማስረጃ ማቅረባቸውን ይፋ አድርገዋል። ይህንን የገለጹት ከተመድ ባለሥልጣናት ለቀረበ ጥያቄ ሲመለሱ እንደሆነም አመልክተዋል።
ጃዋር መሀመድ “ያ – ቄሮ” በማለት መመሪያ እንደሚሰጥ ሕዝብ በተደጋጋሚ ያየው ሃቅ ሲሆን፣ በሲዳማ የደረሰው ቀውስ እየተፋፋመ በተለይ ቡና ጃዋር መመሪያ ይሰጥ እንደነበር ጎልጉል ምንጮቹን ጠቅሶ መዘገቡ የሚታወስ ነው። ጃዋር ራሱን ሰላማዊ ታጋይ አድርጎ ያቅርብ እንጂ ሬዲዮ፣ ሁለት የቴሌቪዥን ጣቢያ፣ ጋዜጦች፣ መጽሄቶችና በርካታ የማኅበራዊ ሚዲያ ሠራዊት ያለው አካል መሆኑ ይታወቃል። መንግሥትን በአንድ ቀን የመገልበጥ አቅም ያለው እንደሆንም በአደባባይ የሚናገር ከመሆኑ በላይ ከመከላከያ ሚኒስትር ለማ መገርሳ ጋር በጥምረት እንደሚሠራ መረጃዎች አሉ።
ከጽንፈኛው ቄሮ ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ስማቸው የማይነሳው አቶ በቀለ ገርባ በቄሮ አደረጃጀት ውስጥ (መሪም ናቸው ይባላል) ወሳኝ ቦታ እንዳላቸው የመረጃ ሰዎች ለውጡ በተጋጋለበት ወቅት ምስክርነት ሲሰጡ እንደነበር፣ ከለውጡም በኋላ ከጃዋር ጋር ይፋዊ አጋር መሆናቸውና በቅጽበት፣ በሚታይ ሁኔታ ወደ ጽንፈኛነት መቀየራቸው ደግሞ የዚሁ የጽንፈኛ ቡድን ቁንጮ መሆናቸውን የሚያመሳክር እንደሆነ ለጉዳዩ የሚቀርቡ የሚናገሩት የአደባባይ ምሥጢር ነው።
ይህንን ጽሁፍ እስከምናትተምናበት ድረስ ከተከሳሾቹ ወገን የተባለ ነገር የለም። ዜናውን የሰሙ አካላት ግን የተለያይ ስሜት እያንጸባረቁ ነው። ተመድ አምኖ ጊዜያዊ እርምጃ ከወሰደ በእነ ጃዋር ዙሪያ ባሉ አካላት ላይ የጉዞ ገደብ ሊጥል ይችላል፤ ገንዘባቸውም እንዲታገድ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።
Engdasew says
It’s right
Alem says
Professor Getachew Haile has a history of
changing facts to fit his personal agenda.
Information he says he got is from a phone
Conversation with his friends in Addis.
We need to remember he resides in New York.
Remember also he wants us to believe him
that he talked with UN officials and the officials
don’t want any one to know their identity.
You believe that? That is dishonest and a wicked lie.
Tesfa says
በዘመነው ዓለም በብሄር ህሳቤ ልባቸው ተነድፎ ልክ እንደ ጫካ አውሬ ለእኔ ብቻ የሚሉት እነዚህ የኦሮሞ የእብድ ስብስቦችን ሴራ ማቆም የሚቻለው እሳትን በእሳት በመመከት ብቻ ነው። በምንም ሂሳብ ይህ የጥፋት ስብስብ ልብ ኑሮት ድርጊቱን የሚያቆም አይደለም። ለምሳሌ በአሜሪካን ሃገር በፕሮፌሰርነት ማእረግ በመምህርነት ደሞዝ የሚከፈለው የጫቱ ምሁር በሩቅና በቅርብ በህዝባችን ላይ የሚጨረውን እሳት በመረጃ ለትምህርት ተቋሙ በማቅረብ ከሥራው እንዲባረር ማድረግ ሌላው ተግባር ሊሆን ይገባል። ሰው እያጋደሉ መደንፋት የለም። የወያኔን ከሥልጣን ወደ ጎን መሆን ተጠቅመው ጊዜው የእኛ ነው የሚሉን እነዚህ የጠባብ – ጠባብ ብሄርተኞች ከወያኔ ቢከፉ እንጂ አይሻሉም። በሙታን አስከሬን የሚጫወቱ። ፎቶ አንስተው በሶሻል ሚዲያዎች ላይ የሚለጥፉ ግሞች ናቸው። በአንድ ስፍራ ሰውን ተሰብስበው ከእየቤቱ እየደበደቡና እየገደሉ ከቤታቸው ካወጡ በህዋላ መኖሪያቸው ላይ እሳት ይለቃሉ። የታሰሩ የቀንድ ከብቶችም ይጮሃሉ። ከውጭ የቆሙት የሞት ጭፍሮች በላሞችና በበጎች የድረሱልኝ ጥሪ ይሳሳቃሉ። በጎናቸው አንድ ሰው እረ እባካችሁ እንስሳትን እንኳን አትግደሉ ቢላቸው በቢለዋ እንደወጉት በሥፍራው የነበሩ የአይን ምስርክሮች ተናግረዋል። ይህ ትውልድ ነው የኦሮሞን ህዝብ ነጻነት የሚያስጠብቀው። የተኩላዎች ጥርቅም።
የሃበሻው ፓለቲካ ከመሰረቱ የተናጋ በአሽዋ ላይ የተመሰረተ ነው። አዕላፎችን በልቷል፤ ገናም ይበላል። የዛሬ 60 ዓመት የተነሱ የፓለቲካ ጥያቄዎች ዛሬም እንደ አዲስ ተነስተው ሰው ሲናቆርባቸው ማየትና መስማት ምን ያህል ፓለቲካው በአለህበት ሂድ እንደሆነ አመላካች ነው። በዚህ ላይ ወያኔና ሻቢያ በፈጠሩት የብሄር ፓለቲካ ሰው ሁሉ እየገባ ሲማገድ ማየት ተስፋ ያስቆርጣል። የምድሪቱ ችግር ፈጣሪዎች እኛውና እኛው ነን። የውጭ ጠላቶች የእኛን መከፋፈል ተመልክተው ነው የእነርሱ ጉዳይ አስፈጻሚዎች የሚያደርጉን። በፔትሮ ዶላር የሰከሩት አረቦች በሁለት ካምፕ ተከፍለው ምሥራቁን የአፍሪቃ ክፍል እያተራመሱት ይገኛሉ። ሳውዲአረቢያ ለዚህ ቀዳሚዋ ናት። ሁሉም ባይሆኑ አንዳንዶቹ የጥቃቱ ተሳታፊዎች ክርስቲያኖችን መርጠው የሚገሉትና የአምልኮ ሥፍራቸውን የሚያጋዪት በዚህ ተልእኮ ነው። ግብጽ ሌላዋ የሃገራችን በሽታ ናት። አሁን ደግሞ ቱርክም በሶማሊያና ሱዳን በኩል ስራዋን ጀምራለች። የኦሮሞ ህዝብ የወስላታ ፓለቲከኞችን ጥሪ ችላ በማለት ከሃገሩ ህዝብ ጋር በፊትም እንደኖረ ዛሬም በሰላም ለመኖር የሙታን ፓለቲከኞችን ጥሪ ችላ ካላለ የወደፊት እድሉ የጨለመ ነው የሚሆነው። በመሰረቱ የዘርና የጎሳ ፓለቲካ ለማንም አይጠቅምም። ወያኔ ለራሱ የሥልጣን ማቆያ ያመቻቸው የክልል ፓለቲካ አፓርታይድ ነው። ለእኔ ቄሮ ማለት አራጅ፤ የወገኑ አስከሬን ወድቆ እያየ በደስታ የሚፈነጥዝ፤ ኦሮሚያ ለኦሮሞ ብቻ የሚል የእብድ ስብስብ ነው። የጃዋርን የፓለቲካ አስተሳሰብ የሚከተል ሁሉ እንቁራሪት ነው። እሱ ሲጮህ አብሮ የሚጮህ። የራስ እይታና አስተሳሰብ የሌለው ኦና ጭንቅላት። ገና በምድሪቱ ላይ ሊመጣ ያለውን ገመና ሰዎች አሁን ማየት ቢችሉ እጃቸውን በአፋቸው ላይ ይጭኑ ነበር። ግን ቀኑ እስኪ ገልጠው የነብይ ጋጋታ ውስልትና ነው የሚሆነው። ዝም ብሎ ማየት ለኖረ መልካም ነው። ይብቃኝ።
Solomon says
One of the risks in going to the UN is
that the agency will investigate the validity
of the complaint by sifting through all
available material. That means speeches
Eskinder made will be looked into.
If you think Eskinder is a peaceful person
then you are in for a big surprise.
Remember also Jawar has a chance
to defend himself. Another risk is that
Professor Getachew and Eskinder are
Amharas. Their collaboration along with
their U.N. contact (whose identity they are
keeping secret) will damn their effort
as ethnically biased thus degrading
their credibility.