• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የኢትዮጵያን የ6 ½ ዓመት በጀት የሚሸፍን ገንዘብ በህወሓት ዘመን ተዘርፏል

November 5, 2019 07:01 pm by Editor 1 Comment

ኢትዮጵያ ባለፉት 30 ዓመታት 30 ቢሊዮን ዶላር ተዘርፋለች!

ኢህአዴግ ወደ ሥልጣን ከመጣ ጀምሮ 30 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከኢትዮጵያ በሕገ ወጥ መንገድ መሸሸቱንና ገንዘቡንም ለማስመለስ መንግሥት ከባድ ሥራ ከፊቱ እንደሚጠብቀው ምሁራን ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ከሀገር የሸሸውን ገንዘብ ለማስመለስ ከፍተኛ ጥረት ቢጠይቅም መንግሥት ጉዳዩን እንደሚከታተለው አሳውቀው የነበረ ቢሆንም ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዳልታዬ ምሁራኑ ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት ምሁሩ ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገዳ እንደገለጹት በኢህአዴግ ዘመነ አገዛዝ ከኢትዮጵያ ወደተለያዩ ሀገራት በሙስና እና ማጭበርበር የሸሸው ገንዘብ 30 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደሚደርስ በጥናት ተረጋግጧል፤ ገንዘቡም በወቅቱ የኢትዮጵያን የስድስት ዓመት ተኩል በጀት መሸፈን የሚችል ወይም አሁን ያለውን የውጭ አገር የመንግሥት ብድር በአንድ ቀን ከፍሎ መጨረስ የሚያስችል ነው።

ጥናቱ ሲሰራ በሀሰት ደረሰኝ የወጪ ንግዱ ላይ በማጭበርበር፣ ከዕርዳታ የተገኘውን እና ጥቅም ላይ የዋለውን ልዩነት በመመርመር እንዲሁም በቀጥታ በሙስና የወጡ ገንዘቦችን ተመርኩዞ መሆኑን የገለጹት ፕሮፌሰር ዓለማየሁ በተለይ በዕርዳታ የሚገባው ገንዘብና ተግባር ላይ የሚውለው መጠን ከፍተኛ ልዩነት እንደነበረውና ለሌብነት የተጋለጠ እንደነበር አስረድተዋል።

“የሸሸው ገንዘብም በግለሰቦች ሒሳብ (አካውንት) እና በባለሥልጣናት የባንክ አድራሻ ነው ወደ ውጭ የወጣው” ያሉት ፕሮፌሰር ዓለማየሁ በዓለምአቀፍ ሕግ መሠረት ደግሞ የግለሰቦችን አካውንት የመመርመር ሥልጣን ስለሌለ የማስመለሱ ጉዳይ ከባድ መሆኑን አመልክተዋል፤ ቢሆንም ግን በመርህ ደረጃ መብት ባይኖርም በፖለቲካ ጥያቄ ተጽእኖ ማድረግ እንደሚቻል መክረዋል።

እንደ ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ማብራሪያ ሕጉ ባይፈቅድም አሜሪካ፣ ዐረብ አገራትና አውሮፓውያን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን በጥሩ መልኩ ስለሚቀበሉ የመንግሥትን የመርምሩልኝ ጥያቄ ሊቀበሉ ይችላሉ። በመሆኑም ጉዳዩ የፖለቲካ ጥያቄ ነው የሚሆነው። አሜሪካና የተለያዩ ሀገራትን ስለሸሸው ገንዘብ መገኛና መረጃ አጣሩልኝ በማለት ጥያቄ ማቅረብ ይቻላል።

ይሁንና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ “የሸሸውን ገንዘብ የማስመለስ ጥረት ይደረጋል” ቢሉም እስካሁን ግን ተጨባጭና ተግባራዊ ጉዳይ አለመታዬቱን ፕሮፌሰር ዓለማየሁ አስታውቀዋል። አሁንም በርካታ ገንዘብ ከሀገር እየሸሸ በመሆኑ በእጅ ያለውንም መቆጣጠር እንደሚያስፈልግ መክረዋል።

የፋይናንስ አሠራር ቁጥጥርና ምርመራን በማጠናከር በማጭበርበርም ሆነ በሙስና ግለሰቦች ወደ አካውንት እንዳይገባ ካልተሠሰራ ትርፉ ድካም ነው የሚሆነው።

በፋይናንስ እና ታክስ ጉዳዮች ለ50 ዓመታት የሰሩት ፕሮፌሰር ፍሰሐጽዮን መንግሥቱ እንደተናገሩት ደግሞ በአፍሪካ በየዓመቱ ካደጉ አገራት ከሚደርሰው ዕርዳታ ይልቅ በሕገ ወጥ መንገድ የሚወጣው ገንዘብ በቢሊዮኖች የአሜሪካ ዶላር ብልጫ አለው። በኢትዮጵያም ተመሳሳይ ሁኔታ ነው ያለው።

ሀገር ወዳድነት በመቀነሱ እና በታማኝነት የሚያገለግሉ ባለሥልጣናት ጥቂት በመሆናቸው በርካታ ገንዘብ ከሀገር ሸሽቷል፤ አሁንም እየሸሸ ነው። በመሆኑም ገንዘቡ እንዳይወጣ ከፍተኛ ቁጥጥር ከማድረግ በተጨማሪ የእስካሁኑ የት ደረሰ፣ በማን ስም እና እንዴት ወጣ የሚለው በመረጃ ላይ የተመሠረተ ሰነድ ያስፈልገዋል።

ፕሮፌሰር ፍሰሐጽዮንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ገንዘቡን የማስመለስ ጥረት እንደሚደረግ ቢገልጹም የታየ ግልጽ ነገር አለመኖሩን ተናግረዋል። በሌላ በኩል የውጭ ባንኮች ገንዘቡ ከየትም ይምጣ ከየትም ተቀብለው ለብድር እና ለተለያዩ ሥራዎች እየተጠቀሙበት ነው። የባንኮች የሕግ፣ አሠራር እና መብት የማንንም ገንዘብ ማንኛውም መንግሥታት እንዲወስድ አይፈቅድም። በመሆኑም ገንዘቡን ለማስመለስ የሚደረገው ጥረት ቀላል አይሆንም። ይሁንና በቅድሚያ ጠንካራ የፋይናንስ ደኅንነት ተቋማትን በማጠናከር እና ሀገር ወዳድነቱን በማሳደግ ገንዘቡ እንዳይወጣ ከወጣም አካሄዱን በመረጃ ብቻ ሳይሆን በማስረጃ ጭምር አስደግፎ መከታተል ያስፈልጋል። መንግሥት የወጣውን ገንዘብ ለማስመለስ ከመሞከር ባሻገር ማን፣ ምን ያህል፣ መቼ እና እንዴት ባለ መንገድ ገንዘብ ከሀገር አሸሸ የሚለውን በዝርዝር አጥንቶ ለቀጣዩ እርምጃ መዘጋጀት እንዳለበትም አሳስበዋል።

የፋይናንስ ደኅንነት መረጃ ማዕከል የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ እንዳለ አሰፋ እንደተናገሩት ደግሞ ኢትዮጵያ የዓለምአቀፉ የፋይናንስ ደኅንነት መረጃ ግሩፕ (ኤግሞንት) አባል ከሆነች ሦስት ወራት በመቆጠሩ በዚህ ወቅት በየሀገራቱ ከሚገኙ 164 የፋይናንስ ደኅንነት ተቋማት ያለምንም ክልከላ መረጃ የማግኘት መብት ይኖራታል።

በመሆኑም በአገር ደረጃ የሸሹ ገንዘቦችን መገኛና ተጨባጭ መረጃ የሚያሰባብስ ጥናት ተጀምሯል። ከሀገር የሸሸ ተብሎ በየመገናኛ ብዙኃኑ የሚገለጸው የተለያየ ቢሆንም ማጣራቱ ሲደረግ መጠኑን በተጨባጭ ማወቅ ይቻላል። በጉዳዩ ተጠርጥረው መረጃ እየተሰበሰበባቸው የሚገኙ ሰዎችንም በተመለከተ ምርመራ እየተካሄደ በመሆኑ ጊዜው ሲደርስ ይፋ እንደሚሆን መግለጻቸውንም አዲስ ዘመን ጋዜጣ በጥቅምት 15፤ 2012 ዓም ዕትሙ አስነብቧል።

እንደ አቶ እንዳለ ገለጻ ተጨባጭ ምንጭና መረጃ ላይ ሲደረስ የትኛውንም ሀገር ስለሸሸው ገንዘብ መገኛ እና በማን ስም እንዳለ ያለከልካይ መረጃ ማግኘት ይቻላል። የግል ዓለምአቀፍ ባንኮች ውስጥ ገንዘቡ ቢኖር እንኳን በዚያው አገር ያለው የፋይናንስ ደኅንነት መረጃ ማዕከል መረጃ የመስጠት ግዴታ ስላለበት መተባበሩ አይቀርም። በጉዳዩ ላይም በመንግሥት ደረጃ የሠላም ሚኒስቴር የሚሳተፍበት ሥራ በስፋት እየተከናወነ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

ምንጭ፤ አብመድ

Filed Under: Opinions, Politics Tagged With: 30 billion, Right Column - Primary Sidebar, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. አለም says

    November 12, 2019 09:23 pm at 9:23 pm

    የተባለው ጥናት ጥሩ መረጃ ካለው የተዘረፈውን ማስመለስ ይቻላል። ዶ/ር ዐቢይ ሁሉን ነገር በራሳቸው ማስፈጸም አይችሉም። በየሙያ ዘርፉ የተሠማሩ ኢትዮጵያውያን አሉ እኮ። በዓለም አቀፍ ህግ እና ፋይናንስ የሠለጠኑ ለአገራቸው የሚቆረቆሩ አሁንም አሉ። ከእነርሱ የተውጣጣ አጣሪ ኮሚቴ በህግ አደራጅቶ ማሠማራት ነው። የተዘረፈው አብዛኛው በእርዳታ ከመጣ ገንዘብ ነው፤ ይህም ክትትል በእርዳታ ሰጭ አገሮች ተቀባይነት ይኖረዋል። ህወሓት አካውንት ከፍቶ ያስቀመጠባቸው ባንኮች የሌባ መነኻርያ እንዳይባሉ ትልቅ ሥጋት ስላለባቸው ይተባበራሉ። ኤፍቢአይ እና ኢንተርፖል አንዱ ሥራቸው ይህንኑ ዓይነት የገንዘብ ዝርፍያ መከታተል ነው። በነገራችን ላይ እነዚሁ ተቋማት ህወሓት ሲሠራ የነበረውን የማያውቁ እንዳይመስለን። በነገራችን ላይ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ ቀንደኛ ነው።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule