“ሳይወሰንልኝ” አልሳተፍም አለ
የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ/ህወሓት በቀጥታ መቃወሚያ ሳያቀርብ የኢህአዴግ እህትና አጋር ድርጅቶች እንዲዋሃዱ በሚወሰንበት የግንባሩ ጉባዔ ላይ ለመገኘት ፈቃድ አለማግኘቱን አስታወቀ። ይህንኑ የሚጠበቅ ውሳኔ ይፋ ሲያደርግ በተዘዋዋሪ ቀን እንዲሰጠው መጠየቁንና አሁንም ተጨማሪ ጊዜ እንደሚፈልግ ማብራሪያ ያላቀረበበትን የህግና የፖለቲካ ጉዳይ አስታኳል።
በህዳር 6 ቀን 2012 የግንባሩ ሥራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ላይ በውህደቱ አጀንዳ በድምጽ ተሸንፎ የወጣው ህወሃት የሶስት ቀን ተጨማሪ ጊዜ መጠየቁን ከስብሰባው ማግስት በኋላ ሲያስተባብል የቆየው ትህነግ፣ ዛሬ ባሰራጨው መግለጫ “የትህነግ ማእከላዊ ኮሚቴ በጥናቱ ላይ እንዲወያይ ተወስኖ እያለ ምንም ዓይነት ውይይት ሳይደረግ በጥድፊያ የምክር ቤት ስብሰባ ማድረግ ተገቢ አይደለም” ሲል ተጨማሪ የመወያያ ቀን ተሰጥቶት እንደነበር አምኗል። በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ቀኑን በትክክል ባያስታውቅም የትህነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ተሰብስቦ የግንባሩ ምክር ቤት የውህደቱን አጀንዳ ለማጽደቅ ህጋዊና ፖለቲካዊ ሥልጣን እንደሌለው አመልክቷል። ህጋዊና ፖለቲካዊ ያላቸውን ጉዳዮች ግን አላብራራም።
ያረጀውና ለሁለት ዐሥርት ዓመታት ሲንከባለል የኖረው የውህደት ጥያቄና ጥናት ተግባራዊ እንዲሆን በኢህአዴግ የመጨረሻው ጉባኤ ለሥራ አስፈጻሚው ውክልና ሲሰጠ በድምጽ ያጸደቀው ህወሓት/ትህነግ፣ የውህደቱ ጥያቄ ወደ ፍጻሜ ሲጠጋ “አገር ትበተናለች” በሚል ዛቻ ሳይቀር ሲያስፈራራና የራሱን የሽግግር መንግሥት ሲያደራጅ እንዳልቆየ ዛሬ “የድርጅቴ ጉባዔ ካልፈቀደ ለመዋሃድ ማንዴት የለኝም” ሲል ጉዳዩን የአሠራርና የተዓማኒነት አካሄድ ሊያስመስለው ሞክሯል።
ቀድሞ ድርጎ እየሠፈረ ያደራጃቸውን ተለጣፊና አሽከር ድርጅቶች በመሰብሰብ “አገሪቱን እንታደግ” በሚል ሽፋን የሽግግር መንግሥት ምስረታ ላይ ተጠምዶ የነበረው ህወሃት/ትህነግ፣ ሙከራው ሲከሽፍበት የውህደቱን ውሳኔ ተከትሎ በትግራይ ሠራዊትና ሚሊሺያ የጦርነት ቀስቃሽ ቃለ ምልልሶችን በማካሄድ ላይ ይገኛል።
በትግራይ ፓርቲዎችን እንደ ቀድሞ ጠፍጥፎ መንግሥት ለመገልበጥ የተሞከረው ዕቅድ ሲከሽፍ የዲፋክቶ (ጊዜያዊ) መንግሥት ማቋቋም መጀመሩን ይፋ ያደረገው ትህነግ፣ ውህደቱን የማይፈልገው ከሆነ ለምን ዝም ብሎ ለቆ በመውጣት የራሱን ሥራ እንደማይሠራ ለበርካቶች ግራ የሚያጋባ ጉዳይ ሆኗል። የትህነግ ተቃዋሚ ድርጅቶች በበኩላቸው የትግራይ ህዝብ ውሳኔ ሳይካተትበት ትህነግ “ዲፋክቶ ስቴት” እመሠርታለሁ ማለቱና ውህደቱን መቃወሙ ፍርሃት የወለደው ውሳኔ መሆኑንን በተደጋጋሚ እየገለጹ ነው።
የቁም እስረኞች ሆነው በሆቴል የመሸጉት የህወሓት/ትህነግ አንጋፋ ወንበዴዎች በሚሰጡት መመሪያ የሚንቀሳቀሰው ትህነግ አድሮ ምን እንደሚወስን ባይታወቅም በሥውር ከአክራሪ ኃይሎች ጋር በመመሳጠር አገሪቱን የማተራመስ ተግባሩን ሊገፋበት ካልሆነ ሌላ አማራጭ እንደማይኖረው አስተያየት ሰጪዎች መግለጫው ከመውጣቱ በፊት ሲናገሩ ነበር።
ህወሃት/ትህነግ በዚህ ትግራይን ይዞ የራሱን አጀንዳ እያስፈጸመ የሚሄድበት አግባብነት የሌለውን አሠራር ትግራይን መሠረት ያደረጉ ፓርቲዎች ሊቃወሙት ይገባል የሚለው አስተያየት ከበፊትም ሲባል የኖረ ነበር። ግፍን ዝም ብሎ መቀበል አይሆንለትም የሚባልለት ታላቁ የትግራይ ሕዝብ እንዲህ ዓይነቱን የትህነግ/ህወሓትን የውንብድና አሠራር በግልጽ በመቃወም ሊታገለው ይገባል። ትግራይን ከሌላው ሕዝብ በመለየት ለራሳቸው ጥቅም የሚሯሯጡትን እስከመጨረሻው ታግሎ ራሱን ከህወሃት/ትህነግ ጭቆና ነጻ ያወጣል የሚለው በቀጣይ የሚታይ ጉዳይ ሆኗል።
ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትህነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የወንበዴዎች ጥርቅም፤ እስካሁንም በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኝ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። አባላቱና ደጋፊዎችም በዚሁ ሁኔታ የሚታዩ መሆናቸውን ብዙዎች የሚስማሙበት ነው።
(ፎቶ፤ በኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ወቅት ከፊት የተቀመጡት ደብረጽዮንና ሌላኛው የበረሃ ወንበዴ ባልደረባው አዲስዓለም ባሌማ)
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።
Babylon says
TPLF is a terrorist organization secretly established by illuminati jews.The Mark on our flag is symbol of lucifer+satan http://www.antichristconspiracy.com http://www.realjewnews.com
DDOP says
No no…let all of us give respect to our lovely country for futur generation