ሦስቱ ፓርቲዎችና አጋር ድርጅቶች አቋማቸውን ግልጽ አድርገዋል ህወሃት “በሁሉም መለኪያዎች አንድ ፓርቲ ለመሆን የሚያስችል መነሻና ምክንያት በሌለበት ኢህአዴግን አፍርሶ ሌላ ፓርቲ ለማቋቋም ማሰብ አገርን የሚበትን ተግባር ነው” ሲል ጉዳዩ የሞት ሽረት መሆኑንን አስታውቋል። አሁን ግጭት እየተባባሰ የሄደውም በዚሁ ምክንያት ነው ሲል አክሏል። እስከ ዛሬ ከውህደት ተገለው የነበሩ አጋር ድርጅቶች በኢህአዴግ ሥር ተጠቃለው እንዲቀጥሉ ምኞቱን ያኖረው ህወሃት፤ አጋር ፓርቲዎች ስለምን ተገለው እንደቆዩ ቁጭቱንም ሆነ ምክንያቱን በመግለጫው አላካተተም። ሰሞኑንን አጋር ፓርቲዎች ሙሉ በሙሉ፣ ሶስቱ እህት ድርጅቶች ውህደቱን እንደሚደግፉና እንደሚቀላቀሉ ይፋ ማድረጋቸውን በድጋፍም ሆነ በነቀፌታ ያላስቀመጠው የህወሃት መግለጫ “ውህደቱ አገር ያፈራርሳል፣ ፍፁም ፀረ-ዴሞክራሲያዊ” ከማለት … [Read more...] about ህወሓት እንቅጩን ተናገረ!!