መለስ የሚያቆላምጧቸው ወ/ሮ አዜብ ለመቀማጠልና ለደኅንነታቸው በመስጋት ቤተመንግሥቱን “አልለቅም” ማለታቸውን የጎልጉል ምንጮች አረጋገጡ። የአዲስ አበባ መረጃ አቀባዮቻችን እንደሚሉት ከሆነ የቀድሞዋ “ቀዳማዊት እመቤት” ሶስት ቪላዎች እንዲያማርጡ ቢለመኑም አሻፈረኝ በማለት ባነሱት የደኅንነት ጥያቄ ገፍተውበታል። ከህወሓት መከፈል በኋላ አቶ መለስ ህወሓትን በመዳፋቸው ውስጥ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ገንነው የወጡት ወ/ሮ አዜብ የተባረሩት፣ የተባረሩት ደጋፊዎችና የህወሓት ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ኢህአዴግ ውስጥ ጥርስ የነከሱባቸው ይበረክታሉ። የሥልጣን እርከን በመጣስ ከሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት በተጨማሪ ለሚያካሂዱት የንግድ ስራ ሲሉ መመሪያ በመስጠት፣ የማይፈልጉትንና አልታዘዝ የሚሉዋቸውን ባለሥልጣናት በማስገደድ፣ በተለይም ተወላጅ ሳይሆኑ በህወሓት አመራሮች ላይ ሲያሳዩ … [Read more...] about አዜብ መስፍን ፈርተዋል!!
ያልተመጣጠነ ግጥሚያ
ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ታመዋልም ሞተዋልም በሚማልበት ሰአት ሎጋው ሽቦ ተዘፈነ … የርዕሰ ብሄር መለስ ዜናዊ ሞት ይፋ በሆነበት ሰአት ደግሞ ብር አንባ ሰበርልዎ ተብሎ ሲዘፈን በሰፊው ተሰማ… ኃይለማርያም ደስ አለኝ ቦታው ተፈቅዶላቸው ሀገር ወከሉ ተብሎ ሲታወጅ አስገራሚው ዘፈን አላቆመም የቤተ ዘመዱ ይታያል ጉዱ ይባል ተገባ… ***************************************************************************************************** አጋጣሚ የፈጠረውን ፖለቲካዊ ግርግር በጥበብ ተጠቅሞ በፖለቲካው እንቅስቃሴ ውስጥ የመደራደሪያ አቅም በማበጀት ወይም አቅም በመገንባት አማራጭ ሀይል መሆንን ከማሳየት ፋንታ በቀረርቶና በሽለላ የጨዋታውን ህግ ለመቀየር መመኘት የምኞት ሁሉ መናኛ ቢባል ያስነውር ይሆን? በትግል … [Read more...] about ያልተመጣጠነ ግጥሚያ
ከሞት በፊት እውነተኛ ክብር
“… ከሁሉ አስቀድሞ ማሸነፍ የሚኖርብን በውስጣችን ያለውን ፍርሃት ነው። ለህወሃት/ኢህአዴግ ታማኝ ሊሆኑ የሚችሉት የጦርና የፀጥታ ኃይሎቹ እንዲሁም የስለላ ተቋሙ የህዝብ ድጋፍ የሌላቸው የጥቂት ዘረኞች ስብስብ በመሆኑ የሕዝብ እምቢተኝነት ሲጠናከር በቀላሉ ይመክናሉ። አመራሮቹ አስተሳሰባቸው በጣም ጠባብ፤ ብቃታቸውም እጅግ ዝቅተኛ ነው። በመሆኑም እነዚህ ኃይሎች ሁሉንም ነገር እንደተቆጣጠሩት አድርጎ ማሰብ ራስን ማዋረድ ነው። ስለዚህም መሸሽ ሳይሆን በየጊዜው ልንፈታተናቸው፣ ልንጎነትላቸውና ልንፋለማቸው ይገባል። ስለሆነም ካሁን በኋላ ሥራው ህወሃት/ኢህአዴግን ከውስጥ ሆኖ የመበታተንና የማፍረስን ሥራ ነው። የነጻነት ኃይሎችም መዋቅራቸውን በማስፋትና በርካታ ህዋሶችን በመፍጠር በትጋት እየሠሩ ይገኛሉ። የህወሃት/ኢህአዴግን የመዋቅር ስፋት በነፃነት ኃይሎች የመዋቅር ስፋት መጋፈጥ ይቻል ዘንድ … [Read more...] about ከሞት በፊት እውነተኛ ክብር
በለገጣፎ ገሃነምና ገነት አየሁ!
“የኦሮሞ እንግዴ ልጅ” በሚል ስያሜ የሚጠራው ኦህዴድ በ1997 መስቀለኛ ጥያቄ ቀርቦለት ነበር። ጥያቄውን ያቀረቡት አንድ በዕድሜ ጠና ያሉ አዛውንት ነበሩ። ጥያቄው የቀረበው አዳማ /ናዝሬት/ ቀበሌ 11 አዳራሽ ውስጥ ነበር። ተጠያቂው የወቅቱ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን ሳዶ ሲሆኑ ስብሰባው የተጠራው “ለምን አልመረጣችሁንም” በሚል ኦህዴድ ከህዝብ ጋር ያለውን ችግር ለመፍታት ታስቦ ነበር። “ኦነግ ኦሮሞ ነው። እናንተም ኦሮሞ ከሆናችሁ ለምን አንድ አትሆኑም? እናንተ አንድ ብትሆኑ ልጆቻችን አይታሰሩም፣ አይገረፉም፣ አይሰቀሉም፣ የደረሱበት እየጠፋ ሃዘን አንቀመጥም፣ ኦሮሞ እስከመቼ ይታሰራል?” የሚል ጥያቄ ያቀረቡት አባት ንግግራቸውን መጨረስ አልቻሉም ቤቱ በጭብጨባ ተናወጠ። “በኔ ዘመን የኦሮሞ ልጆች እንዳይታሰሩ አድርጌያለሁ። በድሬዳዋና በቦረና በኩል የገቡትን ኦነጎች … [Read more...] about በለገጣፎ ገሃነምና ገነት አየሁ!
ከኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል የተላከ ጥሪ
በመከለኛው ምሥራቅ ሃገሮች በቤት ውስጥ አገልጋይነት ለሚሠሩ ሴቶች ድጋፍ የሚደረግ የእግር ጉዞ በዓለምአቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያን ሴቶች መብቶች ለማስከበር የተቋቋመው ድርጅት የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል (የኢሴመማ) ለኢትዮጵያዊያት ሴቶች ድጋፍ የእግር ጉዞ አዘጋጅቷል።የጥሪው ሙሉው ቃል እዚህ ላይ ይገኛል የአማርኛ በራሪ ወረቀት እዚህ ላይ ይገኛል Click here for the English flyer … [Read more...] about ከኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል የተላከ ጥሪ
ከለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ
የለንደን ደብረጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ ስማቸው አባ ግሩም የተባሉትና አሁን ደግሞ አባ ግርማ ከበደ ተብለው የሚጠሩት ደጋፊዎቻቸውን በማስተባበርና ከኤምባሲ ሰዎች ድጋፍ በማግኘት በቤ/ክኗ ላይ እያደረሱ ያለውን በጥልቀት የሚዘረዝር ጽሁፍና የቤተ ክርስቲያኗ ጉዳይ በተመለከተ አባላትና ወዳጆች ሁሉ ባንድ ላይ ተሰብስበው ሙሉ ነጻነት ባለውና በሰለጠነ መንገድ ስለ ቤተ ክርስቲያናቸው ጉዳይ እንዲወያዩ ጥሪ ያደረጉበት ጸሁፍ ደርሶናል፡፡ ሙሉውን እዚህ ላይ ያገኙታል … [Read more...] about ከለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ
ፍትሐት!
ከሰናፍጭ ቅንጣት ባነሰችው አቅሜ በቤተ ክርስቲያናችንና በአገራችን ያለፉትን በንጽጽር ስመለከት፤ የሚሰማኝን በተደራረበ አካል እንደተፈጠረ ቀይ ሽንኩርት መሳይ ኢትዮጵያዊው ቅኔያችን ባቀረብኩት እጅግ በረካሁ ነበር:: ግን ይበልታ ማሰማት የሚችሉ የቤተ ክርስቲያኑቱ ልጆች አንገታቸውን የደፉበት ዘመን ስለሆነ ቅኔውን ትቼ ወደ አማረኛው ስነ ጽሑፍ እሻገራለሁ። የጦማሯ መነሻ በቪዲዮ የታየው የአቶ መለስ ግብአተ መሬት የተሸኘበት ፍትሐት ነው። ቤተክርስቲያችን ይህን አይነት የመሸኛ ፍትሐት የምታደርገው መመሪያዋን ፈጽመው ለሚሸኙ አማኞች ነው። በቦታው ላይ ተገኝተው ስነ ስርዓቱን የፈጸሙ ሰዎች ከኢ.ኦ.ተ. ቤተ ክርስቲያናችን መርሆ ውጭ መሆናቸውን ለመጠቆም ነው:: ሙሉውን አስነብበኝ … [Read more...] about ፍትሐት!
An Ethiopian and the Presidential debate.
By Yilma Bekele President Obama and his challenger Mitt Romney had their first debate this evening. Watching this debate for the highest office in the land was a learning moment. This is not the first debate I have viewed or the first election I am experiencing. But no matter what, for an election starved Ethiopian like me every time it happens it is a like being hit by a lightning bolt experience. It literally gives me a jolt. It is not really difficult to figure out why this is so. No one … [Read more...] about An Ethiopian and the Presidential debate.
በነፃ ገበያ ዙሪያ የሚነፍሰው የተሳሳተ አመለካከት !
በቅድሚያ ለዚህ ጽሁፌ መነሻ የሆነኝ፣ በአለፉት ሃያ ዐመታት በአገራችን ምድር የነፃ ገበያ ፖሊሲ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ ወዲህ በተሳሳተ መልክ የሚናፈሰውንና በአንዳንድ መጽሄቶች የሚወጣውን የተሳሳተ አመለካከት ለመዳሰስ ነው። በተለይም በገዢው መደብ አንዳንድ አባላት ወይም ሚኒስተሮች ስለ ነፃ ገበያ የተሳሳተ አባባል ስለሚነፍስ እንደዚህ ዐይነቱን የተዛነፈና የአንድን አገር ዕድገት የሚያዛባ አነጋገር መዋጋት ያስፈልጋል።ሙሉውን አስነብበኝ … [Read more...] about በነፃ ገበያ ዙሪያ የሚነፍሰው የተሳሳተ አመለካከት !
ኦህዴድ በ“መደብ ትግል” መተላለቅ ጀመረ!
በኦህዴድና በህወሓት መካከል የነገሰው ልዩነት ይፋ የወጣው ዛሬ አይደለም። አርሲ ላይ ማዕከል አድርጎ የተደራጀውን የጁነዲንን ኦህዴድ አባዱላ ሙሉ በሙሉ ከናዱት በኋላ ከፈጣጠሩ ጀምሮ ሰንካ ያልተለየው ራሱ ኦህዴድ ውስጥ ውስጡን ሁለት ቦታ ተገምሶ ቆይቷል። በዘመነ “ህንፍሽፍሽ” ህወሓት ለሁለት በተሰነጠቀበት ወቅት “በህወሓት የውስጥ ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ በመግባት መግለጫ አናወጣም” በማለታቸው ከድርጅትና ከሃላፊነታቸው ተባርረው በነበሩት ኩማ ደመቅሳ ጠቋሚነት ጨፌ ኦሮሚያ አዳራሽ የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ሆነው በ1997 ዓም የተመረጡት አባዱላ ገመዳ ሥልጣን በያዙ ማግስት የጁነዲንን “አርሲ ተኮር” ካቢኔ ሲንዱት ጁነዲንና ደጋፊዎቻቸው ደስተኛ እንዳልነበሩ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ይናገራሉ።ጁነዲን ስልጣን ባስረከቡ በደቂዎች ውስጥ ከጋዜጠኛ ቀርቦላቸው ለነበረ ጥያቄ “ከስልጣን እንደምወርድ ከሁለት … [Read more...] about ኦህዴድ በ“መደብ ትግል” መተላለቅ ጀመረ!