• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የጎልጉል ቅምሻ

December 3, 2012 11:07 am by Editor 3 Comments

ስኳር ለስኳር በሽታ ያጋልጣል

“ጣመኝ ድገመኝ” የምንላቸው ዓይነት ብስኩቶች፣ የቸኮሌት ውጤቶች፣ አይስክሬም፣ ብርታት ሰጪ መጠጦች፣ … በከፍተኛ ሁኔታ ለስኳር በሽታ እንደሚያጋልጡ ሳይንስ ደርሼበታለሁ ይለናል፡፡ በእነዚህ የምግብ ውጤቶች ውስጥ የሚገኘው የበቆሎ ስኳር (fructose corn syrup – HFCS) ምግቦቹን ለማጣፈጥ የሚጨመር በመሆኑ ይህንን ተመጋቢ የሆኑ 20በመቶ ለስኳር በሽታ መጋለጣቸው የማይቀር ነው ይላል ውጤቱ፡፡

ከምዕራባውያን አገራት መካከል አሜሪካ በጣፋጩ አወሳሰድ ቀዳሚውን ስትይዝ በአማካይ አንድ ሰው በዓመት 24.78ኪሎ የበቆሎውን ስኳር በተለያዩ ምግቦች አማካኝነት ወደ ሆዱ ይጭናል፡፡ አንድ ካናዳዊ በዓመት 9.13ኪሎ ሲጭን አንድ ጣሊያናዊ ወይም እንግሊዛዊ ከግማሽ ኪሎ በታች እንደሆነ ጥናቱ ጠቁሟል፡፡ ግብጻዊያን 1.6ኪሎ በአማካይ እንደሚጭኑ ያስረዳው ሪፖርት የኢትዮጵያን ቁጥር አላስቀመጠም፡፡ እንዲህ ያለው አመጋገብና የበቆሎ ስኳር አወሳሰድ ለስኳር በሽታ ብቻ ሳይሆን ለውፍረትና ከዚያ ጋር ተዛማጅ ለሆኑ በሽታዎች እንደሚያልጥ የተለያዩ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ማሞና መለያው

ባለፉት ወራቶች በኒውዮርክ ከተማ ሦስት ባለሱቆችን ገድሏል የተባለው ግለሰብ ሲያዝ አስቀድሞ ፖሊስ ከበተነው ምስል ጋር ፈጽሞ ያለመመሳሰሉ ብዙዎችን አስገርሟል፡፡

ወንጀሎቹ በተፈጸሙባቸው ጊዜያት ፖሊስ ባገኘው መረጃ መሠረት ያሰራጨው ምስል የአንድ ፈርጠም ያለና መነጽር ያደረገ ወጣት ጥቁር አሜሪካዊን ነበር፡፡ በቁጥጥር ሥር የዋለው ወንጀለኛ ግን አውሮጳዊ መልክ ያለው የ64ዓመት ዕድሜ ባለጸጋና ጸጉሩ ከወደፊቱ አካባቢ የሳሳ አዛውንት ነው፡፡ የወንጀለኛውና የተጠርጣሪው አለመመሳሰል ወንጀል በተሰራ ቁጥር በጥቁሮች ላይ የማሳበብ ባህልን በግልጽ ያሳየ ነው በማለት በርካታዎች ተችተውታል፡፡

ኢኮኖሚያዊ የሞት ቅጣት

ወደ 250ሺህ ሰነዶችን ይፋ በማድረግ የዓለም መንግሥታትን በተለይም የአሜሪካንን ምስጢራትን ያጋለጠውና የሹልክዓምድ (WikiLeaks) መስራች የሆነው ጁሊያን አሳንጅ ድርጅቱ ገንዘብ መሰብሰብ እንዳይችል በምዕራባውያን የተደረገበት አፈና በድርጅቱ ላይ “ኢኮኖሚያዊ የሞት ቅጣት” እንዲደርስበት ያደረገ መሆኑን ተናገረ፡፡ በለንደን በሚገኘው የኤኳዶር ኤምባሲ ውስጥ በጥገኝነት የሚገኘው አሳንጅ በስካይፕ በሰጠው መግለጫ በተለይ ከስድስት የአሜሪካ የገንዘብ ተቋማት (ቪዛ፣ ማስተርካርድ፣ …) የደረሰበት ዕቀባ በድርጅቱ ላይ ወደ 50ሚሊዮን ዶላር ኪሣራ እንዳመጣበት ጠቁሟል፡፡ ከኤምባሲው ውጪ ከፍተኛ የፖሊስ ቁጥጥር እየተካሄደ ባለበት ወቅት በኤምባሲው ውስጥ ለተገኙትና በግምባር በዓለምዙሪያ ደግሞ በስካይፕ መልዕክቱን ሲያስተላልፍ ስለ ጤንነቱ የቀረበለትን ጥያቄ ሳይመልስ አልፎታል፡፡ ሥር በሰደደ የሳንባ በሽታ እየተጠቃ ነው የተባለውን ዜና የኤኳዶር መንግሥት አስተባብሏል፡፡

በተያያዘ ዜና ለሹልክዓምድ መረጃ በማቀበል ተባብሯል የተባለው የአሜሪካ ወታደር ብራድሊ ማኒንግ ሰሞኑን ፍርድቤት በቀረበ ወቅት ባለፉት ሁለት ዓመታት እስርቤት የደረሰበትን መከራ አጋለጠ፡፡ አንዳንዴም መናገር እያቃተው በመንተባተብ በሰጠው ቃል ራሱን ለማጥፋት በተደጋጋሚ ሙከራ እንዳደረገ የተናገረ ሲሆን ለዘጠኝ ወራት በአንዲት ትንሽ ቤት ውስጥ ብቻውን እንዲያሳልፍ መደረጉ ከፍተኛ የስነልቦና ጉዳት እንዳደረሰበት የ24ዓመቱ ወጣት አስረድቷል፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ለበርካታ ቀናት ዕርቃነሥጋውን እንዲተኛ መደረጉ ያለፍርድ ቅጣት እንዲቀበል ያደረገው በመሆኑ የደረሰበት እስካሁን የከፈለው ቅጣት ተቆጥሮለት ክሱ እንዲቆምለት ፍላጎት እንዳለው አስታውቋል፡፡

ዘመነ ብልጥስልክ ሊያበቃ ነው

ከወደ ቴክኖሎጂው መንደር ጉድ የሚያሰኝ ዜና ሰሞኑን ተሰምቶዋል፡፡ በቅልጥፍናቸው፣ በአጠቃቀም ብቃታቸው፣ … ተወዳጅ የሆኑት ብልጥስልኮች (Smartphones) ተገልግለን ሳንጠግባቸው ተፈላጊነታቸው በመነጽር ላይ በሚሰኩ ኮምፒውተሮች ይተካሉ እየተባለ ነው፡፡

የጉግል መነጽር
የማይክሮሶፍት መነጽር

ጉግል (Google Glass) የሚባል እና ማይክሮሶፍት ደግሞ ተመሳሳዩን እያሰሩ የሚገኘው ይኸው የኮምፒውተር መነጽር ይፋ ሲሆን የብልጥስልኮች ተፈላጊነትን በእጅጉ እንደሚቀንሰው እየተነገረ ነው፡፡ የኮምፒውተርን የዕድገት ለውጥ በማንሳት የሚከራከሩ “የዛሬውን አያድርገውና ኮምፒውተር ማለት በርካታ ፎቆች ካሉት ህንጻ ጋር የሚወዳደር ነበር፡፡ ቀጥሎም በመቀመጫ ዴስካችን ላይ ሆነ ከዚያም ጭናችን ላይ አሁን ደግሞ የእጃችን መዳፍ ላይ ነው፡፡ ቀጣዩ ፊታችን ላይ ይሆናል” በማለት ትንበያውን ያጠናክራሉ፡፡

በማህጸን ውስጥ የተስፋፊነት “ጦርነት”

መንትያዎች በእናታቸው ማሕጸን ውስጥ ሆነው ያችኑ ትንሽ ቦታ ለመጠቀም የእርስበርስ ትግል እንደሚያደርጉ ከወደህክምናው ዓለም ተሰምቷል፡፡ ሲኒማዊ በሆነ መልኩ የተቀረጸው የ MRI ውጤት እንደሚያሳየው ተስፋፊነትና የይገባኛል ጥያቄ የሚጀምረው ከየት እንደሆነ ለማወቅ ያስቻለ ነው ያስብላል፡፡

ይኸው በእንግሊዝ የህክምና ተመራማሪዎች የተቀዳው ምስል እንደሚያሳየው መንትዮቹ በእናታቸው ማኅጸን ውስጥ ሆነው በቀኝ በኩል ያለው ትንሹ ሰፋ ያለ ቦታ ለማግኘት ትልቁን ሲመታውና ሲገፋው ይታያል፡፡ መጀመሪያ ላይ ትልቁ ምንም ያልሆነ መስሎ ቢታይም በኋላ ግን በጉልበቱ በመማታት የመልሶ ማጥቃትና የድንበር ማስጠበቅ ተግባር ሲፈጽም ይስተዋላል፡፡ ለበርካታ ምርምሮች ፈርቀዳጅ እንደሆነ የተነገረለት ይኸው ሁኔታ ተስፋፊነት፣ ድንበር ማስጠበቅ፣ ሉዓላዊነት፣ … የመሳሰሉት ሃሳቦች የት እንደሚጀምሩ ያመላከተ ነው ሊያስብል የሚችል ነው፡፡

ፊንላንድ፡ በትምህርት ሥርዓት አንደኛ

ፒርሰን የተሰኘው ተቋም ሰሞኑን ባወጣው ዘገባ መሠረት በትምህርት ሥርዓት ፊንላንድ አንደኛ ደቡብ ኮሪያ፣ ሆንግኮንግ፣ ጃፓን እና ሲንጋፖር በተከታታይ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ጨምሮ አስታውቋል፡፡

ይኸው የሰለጠኑ በሚባሉ አገራት መካከል ያለውን የትምህርት ጥራትና ሥርዓት የገመገመው ጥናታዊ ዘገባ ለአሜሪካ የ17ኛ ደረጃ ሰጥቷታል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በቅርቡ በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የተደረገ ጥናት በላትቪያ፣ ቺሌና ብራዚል የሚገኙ ተማሪዎች በአሜሪካ ከሚገኙ ተማሪዎች በሦስት እጥፍ ፈጣንእንደሆኑ የዘገበ ሲሆን በአጠቃላይ በ11 አገራት የሚገኙ ተማሪዎች በአሜሪካ ከሚገኙቱ የሁለት ዓመታት ያህል የትምህርት ብልጫ እንዳላቸው ዘግቧል፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ከ12 ዓመታት ወደ 10 ዓመታት “እንዲሻሻል” የተደረገባት አገራችንስ የትኛው ደረጃ ላይ ትሆን?

“ለመመረጥ ብዬ ነው እንጂ …”

በቅርቡ በተጠናቀቀው የአሜሪካ ምርጫ ከቴኔሲ ጠቅላይግዛት ወረዳቸውን በመወከል ለሸንጎ የተወዳደሩት ብራድ ስታትስ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው እንደነበር የተሰማው ወሬ ግለሰቡን “ግብዝ” የሚያሰኝ ነበር፡፡

የአራት ልጆች አባት የሆኑትና የትዳርን እሴት በእጅጉ እንደሚያከብሩ በምርጫ ዘመቻ ወቅት ሲሰብኩ የነበሩት እኚሁ ግለሰብ ወግ አጥባቂ የሪፓብሊካንን አጀንዳ አራምደው በከፍተኛ ሁኔታ ከተሸነፉ በኋላ በሰጡት ንግግር ስለ ባለቤታቸው ሲናገሩ እርሷ ባትፈቅድልኝ ኖሮ ወደ ምርጫ ውድድር አልገባም ነበር በማለት አወድሰዋቸዋል፡፡ አሁን ግን ሁሉም ከተጠናቀቀና የሽንፈት ጽዋን ከተጎነጩ በኋላ ከባለቤታቸው ጋር በተነሳ ክርክር ሚስታቸውን በጥፊ ካጎኗቸው በኋላ አልጋላይ ወርውረዋቸው ቤቱን ለቅቀው ሄደዋል፡፡ ለየካቲት ወር ፍርድቤት የተቀጠሩት ስታትስ የ5ሺህ ዶላር ዋስ ተቀማጭ አድርገው ከእስርቤት ተለቅቀዋል፡፡

የሳምንቱ ምርጥ ፎቶ

የዝናብ ጉዳይ እጅግ የሚያሳስባቸው ኢንዶኔዥያውያን ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ እንዲመጣ የሚያካሂዱት ዑጁንጋን የሚባል አስደናቂ ሥርዓት አላቸው፡፡ ወንዶች ከወገባቸው በላይ ራቁታቸውን ሆነው ከዘንባባ ዛፍ በተሰራ ጅራፍ ይዠላለጣሉ፡፡ በዥለጣው ደም መፍሰስ ከጀመረ ስለ ዝናብ የተጠየቀው በተገቢው ሁኔታ ምላሽ ማግኘቱን የሚያረጋግጡበት ነው፡፡ በደንቡ መሠረት ከወገብ በታችና ከአንገት በላይ መግረፍ ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡ ዥለጣው ከተጠናቀቀ በኋላ ቂም፣ በቀል፣ ጥላቻ … ሳይኖር ሲዠላለጡ የነበሩት ተሳስቀው ዝናብ እየጠበቁ ኑሯቸውን ይቀጥላሉ፡፡

ዘገባውን ለማጠናቀር በየጽሁፉ ከጠቀስናቸው ምንጮች በተጨማሪ ሌሎችንም የሚዲያ ውጤቶች መጠቀማችንን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡ ከዜናዎቹ ማነስ አኳያ በየጸሁፉ ለመግለጽ ባለመቻላችን ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Yonas says

    December 4, 2012 01:09 am at 1:09 am

    Keep it up guys !

    Reply
  2. አ.በ. says

    December 4, 2012 04:45 am at 4:45 am

    ከኢትዮጲያ ጋር የማይገናኙ ወሬዎቸችን ለቀቅማችሁ የመታቀርቡት ለኛ ምን ይሰራልናል? ከኢትዮጲያ ውጪ ያሉ ወሬዎች ካስፈለጉን እኮ ከብዙ ምነጮች ማግኘት እንችላለን።

    Reply
  3. fisseha says

    December 4, 2012 03:24 pm at 3:24 pm

    ጎልግል እያቀረበቺው ያለው የተለያየ ነገሮች እንደኔ በጣም ጥሩ ነው ብዬ አምናለሁ :: ሁሉኑም አይነት ይዘት ያላቸው ጽሁፎች መቅረባቸው አንባቢው በጉጉት እንዲከታተል ያደርገዋል:: ሁሉም ጽሁፎች ኢትጵያ ውስጥ ስላለ ነገር ብቻ ይሁን ማለት ምን ማለት እንደሆነ አልገባኝም ከኢትዮጵያ ውጪ ያሉና የሚፈጠሩ ነገሮች እኛን አይጠቅሙንም አይመለከተንም ወይም አያዝናኑም ማለት ነው?

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ February 6, 2023 02:03 am
  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule