ኢትዮጵያዊነት ከአጭበርባሪነት፣ ከሸፍጥ፣ ከሴራ፣ ከኩርፊያ፣ ከበቀል፣ ከተንኮል፣ ከደባ፣ ከድብቅ ዓላማ፣ ከአድማ፣ ከባንዳነት፣ ከአቃጣሪነት፣ ከከሃዲነት፣ ከተቀጣሪነት፣ ከማወናበድ፣ በተለይም ከማስመሰለና ከተራ የፖለቲካ ንግድ በላይ መሆኑንና ማንም ሊበርዘው ቢደክምም ሊሸረሽረው የማይችለው የልብ ማህተም መሆኑን ሰሞኑን አየን። ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግርኳስ ቡድን ድል እውን ይሆን ዘንድ ሠንደቅ ዓላማቸውን ለብሰው ሌሊቱን ሙሉ ላገራቸው ያዜሙ፣ በየቤታቸው ሆነው በጸሎት የማለዱ፣ በመላው ዓለም በየድረገጹ የመልካም የደስታ ምኞታቸውን ሲገልጹ የነበሩ፣ በዋናው የትግል ሜዳ የአገራቸውን መለያ ለብሰው ታሪኩን ያከወኑና የትግሉን ስትራቴጂ በመንደፍ ታሪክ የሰሩ ድርና ማግ ሆነው አገራቸውን አብርተዋታል። ብንዘገይም ለመላው የኢትዮጵያ እግርኳስ ቡድን አባላት፣ ለመላው የኢትዮጵያ … [Read more...] about እባካችሁ ይህንን “ኢትዮጵያዊነት” አክብሩት!!
ሥራ አስፈጻሚ ወይስ ጉዳይ አስፈጻሚ?
“ከአያያዝ ይቀደዳል ከአነጋገር ይፈረዳል” እንዲሉ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ፓርላማ ተራ ቁጥር አንድ መቀመጫ ላይ ተሰይመው ንግግር ማድረጋቸውን ተከትሎ አዲስ ክስተት ተስተውሏል። የቅናት፣ የተንኮል፣ የንቀት፣ ያለመታዘዝ፣ ተቃውሞን የማሳየት… ይሁን የሌላ እስካሁን በውል አልታወቀም። በመጀመሪያ ንግግራቸው መዛለፋቸውን ግን ብዙዎች ከእርሳቸው የጠበቁት ባለመሆኑ ተገርመውባቸዋል። በሌላ በኩል ግን ገና ከጅምሩ አክርረው የመጡት “ተለሳላሽ” ናቸው የሚባለውን ለመስበር እንደሆነም አስተያየት ተሰጥቷል። የህወሃት፣ የብአዴን፣ የኦህዴድ፣ የደኢህዴን ሰዎችና ወ/ሮ አዜብ አቶ መለስ ንግግር ካላቸው ማታ እንኳን አያመሹም። ሲያንቀላፉ እንዳይታዩ በጊዜ ተኝተው ጠዋት ፓርላማ ናቸው። ሚኒስትሮችና ከፍተኛ ባለስልጣናት አንዳቸውም አይቀሩም። በሽተኛ እንኳን ቢሆኑ እንደ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ወሳኝ … [Read more...] about ሥራ አስፈጻሚ ወይስ ጉዳይ አስፈጻሚ?
“የጥቁርም የነጭም ደም ቀይ ነው” የመለስ ድራማ!!
የኦጋዴን ጉዳይ ሲነሳ ኢህአዴግ ይደነግጣል። ስለ ኦጋዴን አንዳችም ጉዳይ እንዲነሳበት አይፈልግም። የቢቢሲ የምርመራ ዘገባ በኦጋዴን ተፈጽሟል ያለውን ይፋ ሲያደርግ ኢህአዴግ በተለዩት መሪው፣ በህዝብ ግንኙነቱና እንግሊዝ አገር ባሉት አምባሳደሩ በኩል የማስተባበያ ዘመቻ ከፍቶ ነበር። በኬንያ ስደት ጣቢያ የሚገኙትን የክልሉ ነዋሪዎችን ያነጋገረው የቢቢሲው መርማሪ ጋዜጠኛ ሪፖርት ብቻ ሳይሆን ሂውማን ራይትስ ዎችም የከረረ መግለጫ አውጥቶ ነበር። ከአገር በቀል የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች መካከል የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄም በተመሳሳይ የኦጋዴንን አጀንዳ በማንሳት ጥሪ በማስተላለፍ ቅድሚያ እንደነበረው መረጃዎች ያመለክታሉ። ኢህአዴግ በሃሰት ላይ የተመረኮዘ መረጃ በማዘጋጀት የሚመራውን ህዝብና የዓለም ህብረተሰብን እንደሚያወናብድ የሚያጋልጡ መረጃዎች በየጊዜው ይፋ ይሆናሉ። … [Read more...] about “የጥቁርም የነጭም ደም ቀይ ነው” የመለስ ድራማ!!
ኦብነግና ኢህአዴግ ንግግር አቆሙ!
የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አወጪ ግንባር /ኦብነግ/ እና ኢህአዴግ ጀምረው የነበሩት ድርድር መጨናገፉ ታወቀ። ድርድሩ የተጨናገፈው በኢህአዴግ በኩል በቀረበ ቅድመ ሁኔታ መሆኑ ተገልጿል። መግለጫው ለሁለት ተከታታይ ቀናት ስለተደረገው ንግግር በዝርዝር ሳያብራራ ህዝበ ውሳኔን በመፍትሄነት አስቀምጧል። 74 ንጹሃንን የገደሉት የኦብነግ ሰዎች ጉዳይ በድርድሩ ስለመካተቱ እስካሁን የተገለጸ ነገር የለም። ኦብነግ በድረገጹ ኦክቶበር 17 ቀን 2012 በይፋ እንዳስታወቀው የሰላም ድርድሩ የተጀመረው የኢትዮጵያ መንግሥት ለኬኒያ መንግስት ባቀረበው የአሸማግሉኝ ጥያቄ መሰረት ነበር። በዚሁ ጥያቄ መሰረት የኬንያ መንግስት አሸማጋዮች ለግንባሩ አመራሮች ጥያቄውን አቅርቦ ቀና ምላሽ በማግኘቱ የመጀመሪያ ደረጃ ንግግር ተደርጎ ነበር። የግንባሩ አመራሮች በቀናነት የድርድር ሃሳቡን ተቀብለው እንደነበር … [Read more...] about ኦብነግና ኢህአዴግ ንግግር አቆሙ!
ካለበት የተጋባበት
የአማርኛው ብሂል ‹ካለበት የተጋባበት› ይለዋል፡፡ ፈረንጅኛውም ለዚህ ዓይነቱ አባባል ከአማርኛው አይሰንፍም፤ More catholic than the Pope በማለት ያሳምረዋል፡፡ እንዲህ ዓይነት አባባሎች ከአፎታቸው ተመዝዘው ወደ ደንበኛቸው እንደጃርት ወለባ እየተወረወሩ እሚሰኩት ኃይለማርያም ደሳለኝን የመሰለ ራሱን መሆን የማይችል በጥቅም ወይም በዓላማ ወይም በአእምሮ ዘገምተኝነት ወይም ምናልባትም በነዚህ በሦስቱምና በሌሎችም ተዛማጅ ምክንያቶች የተነሣ ሰውነቱን ለባዕድ ስብዕና ያስገዛ አስገራሚ ፍጡር ሲያጋጥም ነው፡፡ ለነገሩ ዘመኑ የአስገራሚ ፍጡራን መናኸሪያ ስሇሆነ አሁን አሁን የሚያስገርመን ይልቁናም ደህና ሰው ያገኘን እንደሆነ ነው፡፡ (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ይገኛል) … [Read more...] about ካለበት የተጋባበት
ዓዲስ ሰው
ተወዳጁ ገጣሚና ባለቅኔ ጋሽ አሰፋ ገ/ማርያም ረቡዕ ጥቅምት 7 ቀን 2005 ዓም (October 17,2012) የታላቁ ኢትዮጵያዊ ደራሲ የክቡር አቶ ሃዲስ አለማየሁ (ዶ/ር) 103ኛ ቀነ-ልደት (BIRTHDAY) በማስመልከት የጻፉትን ግጥም ልከውልናል፡፡ ግጥሙ ዘመን የማይሽረው በመሆኑ በዚህ ወቅት በድጋሚ አውጥተነዋል (በፎቶ የተከሸነውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) በተጨማሪ በአንድ ወቅት የተቀኙላቸውን በቃላቸው የሚስታውሱትን የአማርኛ መወድስ ቅኔ መርቀውልናል፡፡ ጋሽ አሰፋን ከልብ እናመሰግናለን፡፡ መወድሱ እንዲህ ይነበባል፡- መውደድ ካልቀረ ማፍቀር፤ ወገንና ሃገር፤ እንደ ደራሲው አዲስ ነገር፤ ፍቅር !...እስከ መቃብር! በመጨረሻም “ለወጣቱ ትውልድ መልካም አርአያ የሚሆን ኢትዮጵያዊ እምብዛም በሌለበት በዚህ ጉደኛ ዘመን እንደነ ሃዲስ አለማየሁ የመሳሰሉትንና በየወቅቱ … [Read more...] about ዓዲስ ሰው
ዳምጠው አየለ “ችግሬ እየተቃለለ ነው” አለ
አርቲስት ዳምጠው አየለ አጋጥሞት የነበረው ችግር በኖርዌይ መንግስት ጉዳዩ የሚመለከታቸው ክፍሎች በኩል እየታየና ወደ መፍትሔ እየቀረበ መሆኑን አስታወቀ። በደረሰበት ያልታሰበ እንግልትና በቤተሰብ ናፍቆት የተነሳ ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ቃለ ምልልስ ከሰጠ በኋላ በርካታ ወዳጆቹና አድናቂዎቹ መጨነቃቸውን ያስታወቀው ዳምጠው አየለ፣ "ያጋጠመኝ ችግር መስመር እየያዘ ነው፤ በጥሩ ሁኔታ ላይ እገኛለሁ። ስሜታችሁን ለገለጻችሁልኝ በሙሉ ምስጋናዬ ታላቅ ነው" ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል። በወቅቱ ከቤተሰብ የቆየ ፍቅር ጋር ተዳምሮ፣ አጋጣሚው ስላበሳጨው ስሜቱን መቆጣጠር ተስኖት በሰጠው ቃለምልልስ አድናቂዎቹና ወዳጆቹ አዝነው በስልክና በተለያዩ መንገዶች ስለላኩለት ማበረታቻ ምስጋና ያቀረበው ዳምጠው፣ በቅርቡ ለወዳጅ ዘመድና አድናቂዎቹ ሰፊ መልዕክት እንደሚኖረው አመልክቷል። ከቃለ ምልልሱ ዋና … [Read more...] about ዳምጠው አየለ “ችግሬ እየተቃለለ ነው” አለ
ቱጃሯ ሱራና ኦህዴድ
በማናቸውም የአገሪቱ ባለስልጣናትና ተቋማት ብሔራዊ ባንክን ጨምሮ ይፋ የማያደርጉት የአገር ውስጥ የጫት ፍጆታና ገቢ በውስጡ ከፍተኛ ዝርፊያ ይከናወንበታል። ከዝርፊያው ጋር በተያያዘ አቶ መለስን ጨምሮ ከፍተኛ ሹማምንትና ባለቤታቸው ወ/ሮ አዜብ መስፍን በቅድሚያ ስማቸው ከሚጠቀሱት መካከል ናቸው። የጎልጉል የኦህዴድ ምንጮች የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትርና የንግድና ኢንዱስትሪ ምክትል ሚኒስትሩ በጫት ንግድ ዙሪያ የሚጫወቱትን ሚና አጋልጠዋል። ያገኘነውን መረጃ ለንባብ ያመች ዘንድ እንደሚከተለው አቅርበነዋል። የጫት ንግድ ዝምድና - ወ/ሮ ሱራ በደርግ የአገዛዝ ዘመን ወደ ጅቡቲ ኤክስፖርት መደረግ የጀመረው ጫት ኢህአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር የወያኔ አባላትን ቀልብ አልሳበም ነበር። ባለስልጣናቱና የቀድሞው ታጋዮች ጫት ተጠቃሚ ስላልነበሩ ስለ ጫት ንግድና ከፍተኛ ፍጆታ እንዳለው መረጃው … [Read more...] about ቱጃሯ ሱራና ኦህዴድ
እኔ ምን አገባኝ?
እኔ ምን አገባኝ እኔ ምን አገባኝ የምትሉት ሐረግ እሱ ነው ሀገሬን ያረዳት እንደ በግ የሚል ግጥም ልጽፍ ስሜት አንዘርዝሮኝ ብድግ አልኩኝና ምን አገባኝ ብየ ቁጭ አልኩ እንደገና:: ግጥሙ የተወሰደው ከኑረዲን ዒሳ ፌስቡክ ነው:: ባለፈው ሌባዬ በሚል ርዕስ ላወጣነው የግጥም ጨዋታ የተሳተፋችሁትን ሁሉ በተለይ ደግሞ Tsinat ፣ Gedion Adenew እና አበበ አዲስ ከልብ እናመሰግናለን:: እስቲ ለዚህኛውም አንድ ሁለት ሁላችንም እንበል!! እንደበፊቱ ሁሉ ምላሹ በግጥም ቢሆን ጨዋታዋን ሞቅ ያደርገዋል:: … [Read more...] about እኔ ምን አገባኝ?
ALERT!!
Ambassador Tiruneh Zena's fake Human Rights Council is seeking legitimacy from the United Nations for his excellent job of turning blind eye on the atrocities committed right under his nose. The need to be accredited by the United Nations gives the Commissioner and his bosses two advantages. From one angle, he may seek funding to keep his inactive office alive and may even share the money with his bosses. On the other hand he would try to claim recognition for silence on human rights abuse in … [Read more...] about ALERT!!