በቀዳሚው ጹሁፌ “የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች በድረ-መለስ ኢትዮጵያ፣ አይዲዮሎጂካል እና ስትራተጂካዊ ሁኔታዎች” እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ05/01/2013 በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ላይ በወጣው ላይ ተመስርተው አቶ አንዱ አለም ተፈራ በፈረንጆቹ አቆጣጠር 10/01/2013 በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ላይ “የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች የተግባር ድክመት ወይንስ የግብና የእቅድ ልዩነት” ብለው ባወጡት ጹሁፍ ላይ ገንቢና አስተማሪ ሃሳቦችን ስላቀረቡ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሰዎት እላለው::
የዚህ ጹሁፍ አላማ በዋናነት በመጀመሪያ ጹሁፌ ላይ ያቀረብኩትን ሃሳብ በበለጠ የሚያብራራ ሲሆን፣ በተጨማሪም በአቶ አንዱ አለም ከተነሱት ገንቢ ሃሳቦች መካከል በበለጠ መብራራት አለባቸው ብዬ ያሰብኳቸውን ጉዳዮች ለመዳሰስ ነው:: (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል)
በለው ! says
የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች ተቋማዊ ድክመት ወይስ የራዕይና ስትራተጂ ልዩነት? (ይቺ ጽሑፍ እንደ ምስሏ “አንድ ዓይን ሁለት ፊት” አላት በለው!)
፩) በኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎች መካከል የሚታየው ችግር የሰለጠነ የፖለቲካ ባህል እጦት ነው::(፣ የጋራ አጀንዳዎችን መንደፍ፣ በሚያስማሙ ጉዳዮች ላይ በጋራ መምከር፤ልዩነቶችን ማቻቻል፣ ሁሉንም ተሳታፊ ማድረግ)
*የጋራ አጃንዳ መቼም ከወያኔ/ኢህዴግ የተሻለ ሁሉም ዜጋ በሀገሩ እኩል የሚያደርግ, ሕጋዊ, ሰላማዊ,የባህልንና የኢኮኖሚያዊ የጋራ የኅበረተሰብ ግንኑነት የሚፈጥር እንጂ የሚለያይ መሆን የለበት።!ይህንን የማይቀበል ግን ከዚሁ በከፋ መልኩ ብጥብጥን፣ መገንጠልን፣ ማጋጨትን፣ ማተራመስን፣ ማሸበርን፣ ከወያኔ የተማረ አብሮ ሲዶልት የኖረ፣የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ፣ አስመሳይ ሆድአደር, ሠርጎ ገብ, ዋጋ ቢስ በመሆኑ ጥሎ ማለፍ ይቀጥላል… የግድ መቻቻል አያስፈልግም!አብሮ መንጋጋትት እና መጠላለፍ የሰለጠነ ፖለቲካ ሳይሆን የተለጠጠ የተሟጠጠ የትግል ማነቆ ይሆናል።አራት ነጥብ።
፪)”በኢትዮጵያ በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፸ በትግል እንቅስቃሴና በስደት ላይ የሚገኙ ፓርቲዎች ፴፭ ናቸው:: ሁሉም
ከሚያስማማቸው ጉዳዮች ይልቅ የሚያለያያቸው ይበዛል:: እነዚህ ልዩነቶች ምንጫቸው ግን ተቋማዊ አቅምና ውስጣዊ ዴሞክራሲ እጦት ነው እንጂ የግብና የዕቅድ ልዩነቶች አይደሉም::”
*የሀሳብ ልዩነት ባይኖራቸው ምርጫ ቦርድም ተለያየ አርማ ባልሠጣቸው ለነጉሩስ ኢህአዴግ ትውልደ ኢትዮጳያዊ ኤርትራውያንን አማራ(ብአዴን) አድርጓቸው የለምን? መሬት ቢከለል ወደብ ቢቋረጥስ ሥልጣንና ጥቅማጥቅሙ መች ቀረ? ። ኢህአዴግ ‘ሹምባሽ’ ተከታይ ክልልና ብሔር እንዲወክል ማድረጉ ልዩ ተቋማዊ አቅም ያለው… የውስጣዊ ዲሞክራሲ ስኬት አለው ። ብለን እዚህ ባናንቆለጳጵስ ሌሎችንም አናንቋሽ ! አንውቀስ!!።
፫)”በተፎካካሪው ጎራ ስንት ቅንጅቶች፣ ግንባሮችና ህብረቶች ተቋቋሙ? ስንቱስ የተቋቋሙበትን አላማ አሳኩ? ስንቶቹስ ተጨባጭ ተግባራትን ሳያከናውኑ ከሰሙ?–ሁሉም ውስጣዊና ተቋማዊ ድክመቶቻቸውን ሳያርሙ፣ በሃሳቦች ዙሪያ ከሚደረገው መቀራረብ ይልቅ በግለሰቦች ዙሪያ ለመሰባሰብ መሞከራቸውና ካለፈው ስህተት እንኳን ለመማርና ለማስተካከል ሳይችሉ በመቅረታቸው ነው::”
*ወያኔ በረሃ ሲገባ ፯ ነበርን ነው ያለው መጀመሪያም በግለሰብ ዙሪያ ተሰባሰበ(ብሔር ላመስገኝጠል ለመገንጠል) ይህን ዓላማ ሚደግፉም ሆነ ለመራዳት ሆድአደሮችን አሰለፈ። ንብረት አወደመ፣ ዘረፈ፣ ሰረቀ ፣አሠረ፣ገረፈ፣ ገደለ…በዋናውም ነፍሰ ገዳይ አመለከ…እሱም ሁሉን አንደጠቀለለ በጠላው ሰንደቅ ተጠቀለለ…ዓላማና ራዕይ ያላቸው ለግል ንብረትና ገንዘብ ሀብታቸው ሲሉ “ዘለማዊ ክብርና ሞገስ ለእሳቸው “ብለው ፀለዩ “ደረታቸውን ደቁ፣ ከል ለበሱ፣የዕርዳታ ስንዴ ንፍሮ በድንኳን ውስጥ ነፉ፣በስማቸው ካኒቴራ ባርኔጣ ፎቶግራፍ ሸጡ፣እንባ ጠፍቶ በካሜራ ፊት ዓይናቸውን በለጠጡ!!ካለፈው ፲፱፺፯ ስሕተት በመማር ህዝብ ሌላ ተፎካካሪ እንዳይመርጥ በገንዘብ በአነስተኛና ጥቃቅን ጥቅማጥቅም አስተቃቀፉት፣የመናገር የመጻፍ የማንበብ እና የመሰብሰብ መብቱን ዘጉበት።(ኢህአዴግ ከስሕተቱ ይማራል ሱሉም ዛቱ አደረጉትም)ታዲያ ለጥቅሙና ለሆዱ የቆመና ለሀገር የቆመ አንድ ናቸውን?።
፬) የኢትዮጵያ ዘመናዊ የሃገር ግንባታ ታሪክ እንደማንኛውም የሃገር ግንባታ ታሪክ ያለፈባቸው መሰረታዊ ሂደቶች አንድም የተወሰነን ቡድን ወይም ብሔር ልሂቃንን ማዕከል (ለምሳሌ፣ በኢትዮጵያ የአማራንና ትግራይን፤)
*ጣዲያ ምን ይጠበስ ? አሁን የኦሮሞ የአደሬ, የአፋር, ሊሂቃን አደለም “የከንባታ” በጠ/ሚ ማዕረግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አለን አደለምን? የመንግስት ኮምንኬሽን ሚ/ር በጠ/ሚኒስትርነት ማዕረግ ”የአማራ ኤርትራ” ፤ፋይናንስና መገናኛ ኢንፎርሜሽን በጠ/ሚ ማዕረግ “የትግራይ ኤርትራ” አለን ስለዚህ አሁን የተገፋ ሳይሆን የተነፋ ናቸውና ተፎካካሪ አያስፈልግም! ዝም በሉ ነው ጥያቄው ወይንስ ምሁር የፖለቲካ አብጠልጣይነትን ለማጉፈር?፭)”ያለፈውን ታሪክ ለታሪክ ሙሁራን ትቶ የተሻለ ነገን የመፍጠር ሂደት ላይ ማተኮሩ እግጅ አስፈላጊ ነው”
*”ታሪክ ሠሪው ሠፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው!!” ሲሉ ሠምተዋልን? ለመሆኑ የታሪክ ምሁሮቹ የፃአፉት ሲሉን… ስብሃት ነጋ? አባይ ፀሐዬ? ለገሠ መለሠ?በረከት ስምዖን? ተስፋዬ ገ/እባብ? ወይስ ኢዚህ በእየ ቡና ቤቱ(ማሲንቆ ቤቱ) የሚሞላፈጠው ዲያስፖራ ወይንስ ይህ በእየ ቤተክርስቲያኑ ምድር ቤት ለሳንቡሳና ለሻይ የሚጋፋው? ወይንስ በክርስትና ቤቱና በልደት ቤቱ ቢራውን እየለጋ ቱልቱላውን የሚነፋው ?በሞቅታ ጠረጴዛ የሚመታው? ( ወይንስ በጉልበታቸው በእውቀታቸው በገንዘባቸው በደማቸው ሌት ተቀን የሚደክሙ በሀገርም ውስጥ ሆነ በውጭው ዕለም በፀሐይ ብብርድ በዝናብ በበረዶ በሕዝብ ፊት ኃያላን መንግስታት ቢሮ ቆመው የሚጮሁላት ታሪክን ሠርተው አሠርተው ያለፉም የሚፅፉም የሚዘግቡም ማለትዎ ነው? ፮) የግዛት አንድነት? የመንፈስ አንድነት? የህዘቦች አንድነት?…በኢህአዴግ ነው?ድንቄም አልቀረብንም ድሮ ሲባል ተሰምቷል ቆሉብን! ፈጩብን!አለ..
*ይቺ “ከግሎባላይዜሽን “ጠቆንጥራ የመጣች ነገር ናት! ግሎባላይዘየሽን፡ (ሀ) ጉልቤ-አይዜሽን(በስው ሀገር ሃያል መሆን) ያንድን ሀገር መውረር በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በዳርድንበር ሉዓላዊነትን ለመስበር ወረርሽኝ ማድረግና አንድን ሕዝብ ማፈናቀል፣ ማሰደድ፣ እራሱንም፣ ልጆቹንም ፣መሬቱንም፣ ዕምነትና ባሕሉን እንዲተው እንዲበረዝ እንዲከለስ ብሎም ጨርሶ እንዲጠፋ ማዳቀል የሀገርን ዳር ድንበር እና የሀገርን ጥሬ ሀብት በቅድሚያ ለጎረቤት ሀገር መስጠት ገዚውን ፓርቲ ከውጭ ተቀኛቃኝ እነዲጠብቁ መገበሪያ የምርት ውጤትና መብራት በገፍ በማቅረብ በመሳሪያ በወታደር መክበብ (…)
(ለ) ግልቤ-አይዜሽን (መግለብ) የሚያስተሳስሩ እሴቶቹን መበተን የሀገርን ውስጠ ሚስጥር ከሕዝቡ በበለጠ መመራመር ባሕልና አብሮ መኖርን ማናናቅ በእአንዳንዱ ዘርፍ ተሳታፊ ሆኖ ያለውን ሥርዓት በማሞካሸት ህዝብን በሥነልቦና ጫና ማዳከም የትምህርት ጤና የሥራ ዕድልን ለሥርዓቱ ደራፊዎች በማመቻቸውት ሌላውን እያቁለጨለጩ የበይ ተመልካች ወይንም ተንበርካኪ ሁለተኛ ዜጋ ማድረግ (ዕድር፣ዕቁብ፣ጋብቻ፣መተዛዘን ፣አብሮ መብላት፣ የቀብር ቦታን፣የቤት ይዞታ ውረስን መግታት፣ የሙታንን ሀውልት የታሪክ መዘክሮችን ማቃጥል መሸጥ መለውጥ (…)ይሆናል።
በሀይማኖት ነፃነት ሥም የፓርቲ ደጋፎዎችን በመከፋፈል ተቀናቃኞችን የብጥብጥ እስትራቴጂ መቀየስ ናቸው።
፯) “ዶ/ር ፍሰሃ እሸቱ በቅርቡ ባወጣው ጹሁፉ ላይ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን እንደአሰባሳቢና መሪ እንዲሆን ያቀረበው ፕሮፖዛል…እንደ እኔ እስካሁን ድረስ ከገመገምኳቸው ፲፫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፕሮግራም አንጻር ስመለከተው…መሰባሰብ ያለብን በሃሳብ ዙሪያ ነው ባይ ነኝ::ባጠናኋቸው ፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ያገኘሁት መሰረታዊ ልዩነቶች የግለሰቦች ቅራኔና ማን መሪ ሊሆን የሚል የስልጣን ስኩቻዎች ናቸው:
*”በቆሎ አምርቶ እራሱን መመገብ ያልቻለ ህዝብ እንዴት ለሥልጣን ይጣላል” ?”ይቺን መቀመጫ የሚቀመጥባት አንድ ሰው ብቻ ነው!” ሀራሬ የጠፉት የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ኮነሬል መንግስቱ ኃይለማርያም። “ከሺህ ዓመት እድሜ በላይ ያስቆጠረ የአክሱም የላሊበላ ቅርሶችን ያነፀ የፋሲለደስ ግንብን የገነባ ሕዝብ ነበር… ዛሬ ያለው ትውልድ እንኳን ያንን የመሠለ ነገር ሊሠራ ቀርቶ ቅርሱን ጠብቆ ለማቆየት ቀለም መቀባት እንኳን አልቻለም” የተቀበሩት ጠ/ሚ አቶ ለገሠ (መለሠ) ዜናዊ …ታዲያ መሪዎቹ ይህንን ያህል ከተመረሩ ፲፫ የፖለቲካ ፓርቲ ፲፫ ጠ/ሚኒስትር ማምረት አለበት ማለት ነውን? ወይንስ ግለሰቦች ሥም እዚህ ስለተጠቀሰ ከወዲሁ እንቅልፍ ማጣት የመሠሪ መርዝ የተቀባ ከረሜላ?? የግለሰቦችንም ሥምና ንግግር እየጠቀሱም ማብጠልጠልም የራስን አተረጋጎም እየሰጡ ልሁቅ መሆንም ጥሩ አደለም!!
፰) “አንድ በሚያደርጉን ሃሳቦች ዙሪያ ተደራጅተን በሂደት ልዩነታችንን በማጥበብ፣ የተቃውሞ ሂደቱን ተቋማዊ አድርገን፣ ጠንካራ፣ግልጽና ተጠያቂነት
የሰፈነበትን አደረጃጀትና አሰራር ዘርግተን ተቃውሞውን መምራት መቻል አለበን:፡” ቁም ነገሩ የት ለመሔድ ?
*የትኛውን ሕዝብ ለመምራት? ወዴት?”በጥናት ከደረሱበት ፻፭ ተፎካካሪዎች ሌላ ፺፮ኛ ፓርቲ ካላቋቋሙ በቀር ሁሉን አናንቀውና አንቋሸው በዚህ ጥናት መስማማት ላይ ይደረሳል የሚለው በመሠርቱ እኔ ግለሰቡ የምከተለው ፓርቲና ብሔር የለኝም እንደ አንድ ኢትዮጵዊ ዜጋ ግን ታዝቤ ፈግግ ማለት ሙሉ መብት አለኝ!ትግል ያለ መሪ አልሰማሁም። በእርግጥ ፈላጊና ተፈላጊው አለመገጣጠሙ እንጂ ኢትዮጵያ የመሪ ችግር የለባትም ያለ መሪ የሚሄድ መንጋም አመሳሹም ላይ ይበላል! ይጠፋል! ለነገሩ ጠቅላያችን ተጠቅልለው ምክንያቱን ቀንና ቦታውን ሳናውቀው “ሳናያቸው እንዳሉ አምነን እራሳችንን አሰተዳደርን ኩሩ ሕዝቦች ማለት እና ኢትዮጵያውያን ትናንትም ዛሬም ነገም ነን በለው!!” መናጋር መጻፍ ወንጀል ሆኖ “አለም በቃኝን” አፍርሰው “ኢትዮጵያ በቃችኝን” ገንብተው ህዘብ ከሚያሸብሩ አድነን እዚህ ጉልጉል አድርገን እንድንናገር እንድንፅፍ ዕድሉን ስላገኝን እናመሰግናለን!!