• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ህወሓት ደብረጽዮንን ቀጣይ ጠ/ሚ/ር ያደርጋል!

December 3, 2012 02:48 am by Editor 7 Comments

ከአቶ መለስ መለየት በኋላ ወደ አደባባይ የወጡት ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆኑ እንደሚችሉ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ግምታቸውን ሰጡ። አገር ቤት ተቀምጠው በኢህአዴግ ላይ የሰላ ትችት በማሰማት ቀዳሚውን ስፍራ የያዙት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና መምህርና እንደ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም የአደባባይ ምሁር በመባል የሚታወቁት ዶ/ር ዳኛቸው ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ይፋ እንዳደረጉት ለግምታቸው ምክንያት ሰጥተዋል።

አቶ መለስ በህይወት እያሉ የስልጣን ክፍፍሉን በሶስት ለመመደብ መታሰቡን ሰምተው እንደነበር ያስታወሱት ዶ/ር ዳኛቸው፣ ሃሳቡ ከስምምነት ላይ ሊደረስ ባለመቻሉ ተግባራዊ ሊሆን እንዳልቻለ አመልክተዋል። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ማንም ይሁን ማን ከዚህ ቀደም እንደነበረው ስልጣኑ በአንድ ሰው ላይ ተጭኖ ሊቀጥል እንደማይችል ከስምምነት ላይ በመደረሱ አሁን የተደረገው ምደባ ተግባራዊ ሊሆን እንደቻለ በማመልከት ስለቀጣዩ ጠ/ሚኒስትር ግምታቸውን አኑረዋል።

“በእኔ ግምት” አሉ ዶ/ር ዳኛቸው የወደፊቱን ሲተነብዩ “… ህወሃት የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ለመያዝ በሁለት መንገድ እየሄደ ነው፡፡” ሕወሓት አሁንም ቢሆን ስትራቴጂካዊ ቦታ ላይ መቀመጡን ያመለከቱት ዶ/ር ዳኛቸው ህወሃት ቁልፍ ቦታዎችን መያዙን ለቀጣዩ ዋና ስልጣን መንደርደሪያ አድርጎ እንደሚጠቀምበት ጠቁመዋል።

የመጀመሪያው ህወሓት ከያዘው ቁልፍ የሚኒስቴር መ/ቤቶች ስልጣን አኳያ ከሁለት ዓመት ተኩል በኋላ ሊሆን የሚችለውን ሲገመት  አመራሩ እንደ ዱላ ቅብብል የሚተካካ እንደሆነ ተደርጎ የሚነገረው ሁሉ ጥያቄ ውስጥ እንደሚያስነሳ የተናገሩት ዶ/ር ዳኛቸው፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትርነትና ወሳኝ የሚባለው የፋይናንስና የኢኮኖሚ ዘርፎች መከላከያውን ጨምሮ ህወሃት እጅ መውደቃቸው የወደፊቱን የስልጣን ተረካቢ አመላካች መሆኑን ገልጸዋል።

ሌላው ከሁለት ዓመት በፊት የጠ/ሚኒስትርነት ስልጣኑ  የተጠናከረ በመሆኑ “ለሶስት መክፈል አለብን” የሚል ሃሳብ ተነስቶ በጊዜው ተቀባይነት ያላገኘው የጠ/ሚ ቦታ ከህወሓት እጅ ከወጣ የህወሓት የበላይነት ያከትማል የሚል ስጋት ስለነበራቸው እንደሆነ ዶ/ር ዳኛቸው ጠቁመዋል። በማያያዝም “ህወሓት ሁለት አመራሮቹን አጭቷል፤ ዶ/ር ደብረጽዮንና ዶ/ር ቴድሮስን፡፡ ከሶስት ዓመት በኋላ ስለጠ/ሚኒስትሩ ማንነት ስገምት ግምቴ ወደ ዶ/ር ደብረጽዮን ያደላል” ሲሉ የሶስቱ ጠ/ሚኒስትሮች ምደባም ሆነ የአቶ ሃይለማርያም ወንበር ይሁንታ “እስክንዘጋጅ ጠብቁን” ዓይነት መሆኑን አመላክተዋል።

መለስ በድንገት የተለዩት ህወሃትን ማን ይመራዋል? ቀጣዩ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትርስ ማን ሊሆን ይችላል? የሚለው የወቅቱ አንገብጋቢ አጀንዳ በነበረበት ወቅት ዶ/ር ደብረጽዮን ለጠቅላይ ሚኒስትርነት መታሰባቸውንና በኦህዴድ በኩል ተቀባይነት አለማግኘታቸውን ለመዘገብ ጎልጉል ቅድሚያ ነበረው። ጎልጉል በዘገባው  “ህወሓት በምርጫው ያልተገመቱና አዲስ አመራር ወደ ሃላፊነት አምጥቷል። እርሳቸውም ዶ/ር ደብረጽዮን ወልደ ሚካኤል ናቸው። በሚኒስትር ማዕረግ የኢንፎርሜሽንና ደህንነት ኤጀንሲ ዳይሬክተርና የኢትዮ ቴሌኮም ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት  ዶ/ር ደብረጽዮን በነባር ታጋዮች ዘንድ እይወደዱም” ብሎ ነበር።

ደብረጽዮን ወልደ ሚካኤል በደኅንነቱ የሚከናወኑ ከፍተኛ ጉዳዮችን የሚመሩ፣ ከፍተኛ ውሳኔዎችን የሚወስኑ፣ የአገሪቱን የደኅንነት መዋቅር ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ጎን ለጎን የሚመሩ መሆናቸውን በቅርብ የሚያውቁ ይገልጻሉ። ህወሓት የገነባውን የደህንነት መዋቅር በታማኝነት የሚቆጣጠሩት አዲሱ የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር  ህወሓት ለሁለት በተከፈለበት ወቅት አቶ መለስ በአሸናፊነት እንዲወጡ ታላቅ ሚና መጫወታቸውን በብዙዎች ይፋ ያልወጣ ግለ ታሪካቸው ነው።

ለአቶ መለስ እጅግ ቅርብ የሆኑት ደብረጽዮን ህወሓትን ወክለው የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር እንዲሆኑ በህወሓት በኩል ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለ የጎልጉል የመረጃ ምንጮች አስታውቀዋል።  በዘመነ ህንፍሽፍሽ ህወሓት ለሁለት መሰንጠቁ ይፋ ከመሆኑ በፊት ልዩነቱ ውስጥ ውስጡን በተጋጋመበት ወቅት አቶ ደብረጽዮን ከአቶ መለስ የተቀበሉትን ልዩ ተልዕኮ ለመተግበር ያስችላቸው ዘንድ የሽሬ ምክትል አስተዳዳሪ ተደርገው ተሹመው ነበር። አፈንጋጭ የተባለውን ቡድን ከሚመሩት መካከል ዋና ኃይል አላቸው ተብለው የሚፈሩት አቶ ስዬ አብርሃ በትውልድ መንደራቸው ተምቤን ውስጥ ያላቸውን ሰንሰለት ለመበጣጠስና ለማምከን ልዩ ተልዕኮ ይዘው ወደ ሽሬ ያመሩት ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ሃላፊነታቸውን በመወጣት ለመለስ አሸናፊነት ጉልህ ሚና መጫወታቸውን ምንጮቹን ጠቅሶ ጎልጉል ዘግቦ እንደ ነበር የሚታወስ ነው። የጎልጉል ምንጮች አሁንም ቢሆን ቀጣዩ ጠ/ሚኒስትር ደብረጽዮን እንደሚሆኑ ከግምት በላይ ይናገራሉ።

ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ እነሆ

ጥያቄ፡- ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ ለምክር ቤቱ አቅርበው ያፀደቁትን አዲስ የካቢኔ አደረጃጀት እንዴት ያዩታል?

ዶ/ር ዳኛቸው፡- ከዚህ በፊት ሰምቼ ነበር፤ ሶስት ቦታ እንክፈለው የሚለውን፡፡ በዚያን ጊዜ ግን ስምምነት ላይ አልተደረሰም፡፡ በአንድ ነገር ላይ ግን ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር፡፡ አዲስ የሚመጣው ጠ/ሚኒስትር ማንም ይሁን ማን ከዚህ በፊት የነበረው ጠ/ሚ የነበረውን ሃይል ክምችት ይዞ መቀጠል እንደማይችል ተነጋግረው ጨርሰዋል፡፡ ማን ጠ/ሚ ይሆናል የሚለው አይደለም ወሳኙ፤ ህወሓት አካባቢ ማን እየተሾመ ነው የሚል ነው ወሳኙ፡፡ አሁንም ቢሆን ምንም ወዲያና ወዲህ የለኝም፡፡

በእኔ ግምት ሕወሓት አሁንም ቢሆን ስትራቴጂካዊ ቦታ ላይ ተቀምጧል – ጠ/ሚ ለመሆን፡፡ በሁለት መንገድ ነው እየሄዱ ያሉት፡፡ በውጭ ጉዳይም ትክክለኛ የስልጣን ቅብብል ነው የሚባለው ጉዳይ አሁን ጥያቄ ውስጥ የገባ መሰለኝ፡፡

ህወሓት ከያዘው ቁልፍ የሚኒስቴር መ/ቤቶች ስልጣን አኳያ ከሁለት ዓመት ተኩል በኋላ ሊሆን የሚችለውን ለመገመት ስንሞክር አመራሩ እንደ ዱላ ቅብብል ነው የሚባለው ጥያቄ ውስጥ የገባ ይመስለኛል፡፡ ወሳኝ ወሳኝ ቦታዎችን ወስደዋል፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሄዷል፤ እዛው ተመልሶ ቦታው ገብቷል፡፡ ወሳኝ የሚባለው የፋይናንስና ኢኮኖሚው ሄዷል፤ ተመልሶ ቦታው ገብቷል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት የጠ/ሚኒስትርነት ስልጣኑ (ቢሮ) የተጠናከረ ነውና ለሶስት መክፈል አለብን የሚል ሃሳብ ተነስቶ ነበር፡፡

በጊዜው ያ ተቀባይነት አላገኘም፡፡ የጠ/ሚ ቦታ ከህወሓት እጅ ከወጣ የህወሓት የበላይነት ያከትማል የሚል ስጋት ነበራቸው፡፡ አሁን እንግዲህ አንድ ጠ/ሚኒስትርና ሦስት ምክትል ጠ/ሚኒስትሮች አሉን ማለት ነው፡፡ እያንዳንዳቸው ደግሞ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በክላስተር ተከፋፍለው አስተባባሪነት ተሾሞባቸዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ መተያየት ያለበት ማንኛውም ለየትኛው ክላስተር (ዘርፍ) በአስተባባሪነት እንደተመደበ ነው? ሽግሽግ ሲመጣ ሹመት ሲመጣ ህወሓት ተጠናክሮ እንደመጣ እንመለከታለን፡፡ ፋይናንስና ኢኮኖሚውን ዶ/ር ደብረጽዮን ያዘ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩን ዶ/ር ቴዎድሮስ ያዘ፤ በሶስተኛ ደረጃ መከላከያው የት ቦታ እንዳለ እናውቃለን፡፡ ይህንን ሁሉ የያዘ ፓርቲ የስልጣን ፍፁም የበላይነቱን ያዘ፣ ተቆጣጠረ ማለት ነው፡፡ ሕወሓት አካባቢ ማን ነው የበላይነት የያዘ የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡

ህወሓት ሁለት አመራሮቹን አጭቷል፤ ዶ/ር ደብረጽዮንና ዶ/ር ቴዎድሮስን፡፡ ከሶስት ዓመት በኋላ ስለጠ/ሚኒስትሩ ማንነት ስገምት ግምቴ ወደ ዶ/ር ደብረጽዮን ያደላል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ህወሓት ተደከመ፣ ሞተ የሚባለው ወሬ የተጋነነ ይመስለኛል፡፡

ታላቁ መሪያችን የፃፈውን እንተገብራለን ብለው የአሁኑን ጠ/ሚኒስትር በመሾም የመጀመሪያውን ፎርሙላ ካሳዩን በኋላ፣ በይደር ያስቀመጡት ሁለተኛው ፎርሙላ መሆኑ ነው የአሁኑ ለሶስት መካፈል – እኛ እስከምንዘጋጅ ነው ነገሩ፡፡ በዚህ ክፍፍል ለማን ምን እንደደረሰው አሁን ግልጽ የሆነ ይመስለኛል፡፡ ምክትል ጠ/ሚኒስትር ከተቀመጠ በኋላ ሌሎች ሁለት ምክትሎች ከጐኑ ማሰለፍ የሚገርም ነው፡፡ አንዳንዶቹ ሰውዬው ልምድ ስለሚያንሳቸው ነው ይላሉ፡፡ መቼ እድል ተሰጠው፡፡ እስከ አሁንስ በመለስ ምስል አይደል እንዴ ያለነው፡፡

አቶ ሃይለማርያም መከላከያው፣ ደህንነቱ፣ ዲፕሎማሲው በጠ/ሚኒስትሩ ስር እንደሆነ ተናግረዋል? ይህማ እንዳልሆነ ሊሾሙ አራት ቀን ሲቀራቸው 37 ከፍተኛ መኮንኖች መሾማቸውን ሰምተናል፡፡ እነዚህን ከፍተኛ መኮንኖች ማሾም የነበረበት ማን ነው?  ከዚህ አንፃር የህወሓት የበላይነት ተመልሷል ለሚሉት ቀድሞስ መች ጥያቄ ውስጥ ገባና እንላቸዋለን፡፡ አቶ ሃይለማርያም የካቢኔውን አደረጃጀት ሲያስረዱ፤ ከሌሎች በፓርላሜንታዊ ዲሞክራሲያዊ ሲስተም ከሚተዳደሩ ኢኮኖሚያቸው በፍጥነት እያደገ ከሚገኙት አገሮች የካቢኔ አወቃቀር የተወሰደ ልምድ እና የተካሄደ ጥናት እንዳለ ገልፀዋል … ይህ የተለመደ የኢህአዴግ ፊሊጥ (Modus Operandi) ነው፡፡ ከግሪክ አመጣነው ከግብጽ ወሰድነው ይላሉ፡፡ ሌጂቲሜሲ ለመመስረት የሚደረግ ነው፡፡

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. koster says

    December 3, 2012 12:33 pm at 12:33 pm

    As long as the oppositions are only paper tiger and fight each other instead of fighting woyane ethnic fascists, Ethiopians will suffer under successive home grown fascists.

    Reply
  2. አለም says

    December 3, 2012 04:45 pm at 4:45 pm

    ጎልጉል፡- አቀራረባችሁን ወድጃለሁ። አንድ ነገር ግን። የግለሰቦችን ማንነት ዘርዝሩልን። ለምሳሌ፣ ዶ/ር ደብረጽዮን ዶክተርነታቸው በምን ዘርፍ ነው? ዶክትሬቱን ከየት ዩኒቨርሲቲ ተቀበሉት? ጫካ ነበሩ ካላችሁ መቼ ተማሩት ወይስ ተምረው ጫካ ገቡ?

    Reply
  3. koster says

    December 3, 2012 08:44 pm at 8:44 pm

    That means the agenda of fascist Meles will be continued that is to eliminate the so-called enemies – Amharas http://vimeo.com/18242221

    Reply
  4. Tsinat says

    December 3, 2012 10:06 pm at 10:06 pm

    አለም it’s been 22 years since they have been in ጫካ. the other thing it doesn’t matter from where he got his Dr. what matter is what is his intent toward Ethiopia?

    Reply
  5. Alem says

    December 4, 2012 04:45 am at 4:45 am

    Dear Tsinat: “you are not serious when you say “it doesn’t matter where he got his PhD?” Did not Debretsion recently take over Economy, Finance, Security and Technology? How is he going to run those sectors? Are you saying he will have well-trained staff working for him? How will he be able to supervise or give instruction? Tsinat, You should know better than to say it does not matter. I hope you are not in the same league, in which case I could understand the reason for defending the indefensible. Take care.

    Reply
  6. ናታኒም says

    December 11, 2012 07:46 am at 7:46 am

    ጥሩ መረጃ ነው በርቱ ።

    Reply
  7. Maregu says

    December 17, 2012 11:38 pm at 11:38 pm

    It is funny that meles was teaching the tagays that: Amahara should vanish from the face of the earth. He must be mentally challenged. According to Aboy G/ medhin, Meles said: “amara norom aytiqmenim, motom aygodanim. Selizih amara metifat alebet”. That is the legacy of wedi zenawi. Hiwehat Beshitegna dirijit new.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule