ሟቹን ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊን ለመተካት የሚደረገው የውስጥ ለውስጥ ሽኩቻ ኢህአዴግ እንደሚለው “በቀላል ሽግግር” የሚቋጭ እንዳልሆነ የሚጠቁሙ መረጃዎች እየወጡ ነው። መለስን በወኪሏ ወ/ሮ ሱዛን ራይስ አማካይነት በአስከሬን ሽኝቱ ወቅት ያቆለጳጰሰችው አሜሪካ የስልጣን ሽግግሩ ላይ ያላትን የማያወላዳ አቋም ትዕዛዙን ባለመቀበል ከሚመጣው መዘዝ ጋር ማስታወቋም ተሰምቷል። የጎልጉል የአዲስ አበባ ምንጮች ከኢህአዴግ ከፍተኛ ደጋፊዎችና የቅርብ ባለሃብቶች እንዳገኙት ገልጸው በላኩት መረጃ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲተኩ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤልን በቅድሚያ እጩነት መያዛቸውን አመልክተዋል። መረጃ አቀባዮቻችን ደብረጽዮን ለሹመቱ የታጩበትን ምክንያት ሲያስረዱ መነሻ ያደረጉት በህወሓት ክፍፍል ወቅት የነበራቸውን … [Read more...] about ህወሓት ለዳግም ሥልጣን እየሮጠ ነው

