* ዳያስፖራው ራሱን ከትግሉ እያገለለ ነው ከሚያዚያ 6 ቀን 2018 ዓም ጀምሮ በተደረገ ተከታታይ ስምሪት የፋኖ ኃይል እጅግ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ተገለጸ። በተለይ በራያ ቆቦ ወረዳ የተደረገው ሥምሪት ባካባቢው በሚገኘው የፋኖ ኃይል የደረሰው ጉዳት መጠነ ሰፊ እንደሆነ ተመልክቷል። በፋኖ ተስፋ የቆረጠው ዳያስፖራ ከሚኖርበት ሀገር የገጠመው ችግር ተጨምሮ ለፋኖ የሚሰጠውን ድጋፍ እየቀነሰ ነው። እስከ ዛሬ ድረስ በራያ ቆቦ ወረዳ በአማያ፣ በባይባዋ፣ በፀበለት እና አካባቢው በተደረገው ተከታታይ ስምሪት የመከላከያ ሠራዊት በፋኖ ላይ ባደረሰው ከፍተኛ ምት ንብረቱን፣ ትጥቁን እና ተተኳሹን በመተው ከአካባቢው ሲለቅቅ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 802ኛ ኮር አካል የሆነው 48ኛ ክፍለ ጦር በተጠቀሱት ቦታዎች እና ልዩ ሥፍራው "አካምባ" በሚባል ቦታ ፈጥኖ በመድረስ የፋኖው ኃይል ጥሎት … [Read more...] about የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ
Archives for April 2026
አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?!
* ለመሆኑ የቴዲ ኢትዮጵያ የት ትሆን ያለችው? ታዋቂው አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) አዲሱን አልበሙን በስምንተኛው ወር፣ በስምንተኛው ቀን፣ በስምንተኛዋ ሰዓት ለመልቀቅ መወሰኑ በቁጥር ስሌት (Gematria) ዙሪያ መነጋጋሪያ አጀንዳ ፈጥሯል። ይህ "888" የተሰኘው ቁጥር በአጋጣሚ የተመረጠ እንዳልሆነና አርቲስቱ ሆን ብሎ መልዕክት ለማስተላለፍ የተጠቀመበት ነው የሚሉ ወገኖችም አሉ። በክርስትና እምነት 777 የመለኮት ቁጥር ሲሆን፣ 666 ደግሞ የባቢሎን፣ የአውሬው ወይም የክርስቶስ ተቃዋሚ ቁጥር ተደርጎ እንደሚወሰድ ሁሉ፣ 888 ምንን ሊወክል ይችላል የሚለው ጥያቄ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል። ከመንፈሳዊ ትርጓሜ አንፃር፣ 888 በግሪክ ቋንቋ የኢየሱስ (Ιησούς) ስም መጠሪያ ሆኖ የሚያገለግልና ከፍጽምና በላይ የሆነን መለኮታዊ ኃይል ወይም አዲስ ጅማሮን … [Read more...] about አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?!
ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ?
ሰዎች ተጠርጣሪ ወንጀለኛ ናችሁ ተብለው ሲያዙ ይደነግጣሉ፤ ከሁሉ በላይ የሚያስደነግጠው ደግሞ ፖሊስ ጣቢያ ሄደው የሚነሱት ፎቶ ነው። ሕይወታቸውን ሁሉ የሚያበላሽ፤ ዕድሜ ልካቸውን ሲከተላቸው የሚኖር ፎቶ ነው። ብዙዎች ሲነሱ ይበሳጫሉ፤ ሌላ ሰው ለመምሰል ይሞክራሉ፤ ንዴትና ቁጭር ይታይባቸዋል፤ ዓይነቱ እጅግ ብዙ ነው። ዱሮ ላይ ፎቶ ቤት ሄዶ መነሳት ብርቅ ነበር። ፎቶ አንሺ ማለት ከሐኪም በላይ ነው የሚከበረው፤ ሁኑ ያለውን ሁሉ ሆኖ መነሳት የግድ ነው። የማይሆኑ ትዕዛዞችን ሊሰጥ ይችላል፤ "የተናደደ ሳቅ ፊትህ ላይ አሳይ"፤ "ተመስጠህ ተበሳጭ"፤ ወዘተ የሚሉ። ፊንቴክን በተመለከተ ተጠርጥረው የተያዙት የተነሱት ፎቶ ትንሽ ለየት ያለ ነው። ዱሮ "ፎቶ ቤት ሄደህ ፎቶ ትነሳለህ" እንደተባለ ልጅ ፍልቅልቅ ብለው መነሳታቸው ግራ ያጋባል። አንድ ሰው ለብቻው በሺዎች የሚቆጠር ፎቶ … [Read more...] about ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ?
የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ
የውጭ የደህንነት ተቋማት በአንድ ሀገር ውስጥ ወደፊት ስልጣን ወይም ተፅዕኖ ሊኖራቸው የሚችሉ ወጣቶችን ገና በለጋ እድሜያቸው የመመልመልና የራሳቸውን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ግብ በሚያሳካ መልኩ ኮትኩቶ የማሳደግ ስልትን በስፋት ይተገብራሉ። ይህ ተግባር በዘርፉ "የልሂቃን ቀረጻ" (Elite Capture or Cultivation) ተብሎ የሚጠራ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም የተመረጡ ወጣቶችን የዓለም እይታ (Worldview) ከሀገራዊ ጥቅም ይልቅ የውጭ ሃገር ፍላጎትና ጥቅምን በሚያሳካ መልኩ አድርጎ መቅረጽ ነው። እነዚህ ተቋማት የአንድን ወጣት የወደፊት የመሪነት ዝንባሌ ቀድመው በመረዳት፣ በትምህርት እና በተለያዩ ስልጠናዎች ስም ከሀገሩ በማውጣት የአስተሳሰብ አድማሱን በእነሱ የፍላጎት ልክ ይቀርፁታል። ይህ "Formative age" ወይም የማንነት ቀረጻ ምቹ እድሜ የአንድ ሰው ስብዕና እና … [Read more...] about የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ




