እኤአ በፌብሩዋሪ 2014 በ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ወደ ሥልጣን የመጣውንና ምርጫው “ደህንነትና ትብብር ድርጅት” (OSCE Organization for Security and Cooperation) በተሰኘው ዓለምአቀፋዊ ድርጅት የጸደቀው የዩክሬን መንግሥት በመፈንቅለ መንግሥት ተወገደ። ፕሬዚዳንቱ ቪክቶር ያኑኮቪች ሕይወታቸውን ለማዳን ከአገር ለቅቀው ወጡ። መፈንቅለ መንግሥቱ የተቀነባበረው በተለይ በአሜሪካ ባልሥልጣናት ነው። ትውልደ ዩክሬን የሆነችውና በወቅቱ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአውሮጳና ዩሬዢያ ረዳት ጸሐፊ የነበረችው ቪክቶሪያ ኑላንድ የሤራው ዋና አቀናባሪ ነበረች። አብሯት ሟቹ ሴናተር ጆን ማኬይን ሠርቷል። ፕሬዚዳንት ያኑኮቪችን ከሥልጣን ለማስወገድ ቪክቶሪያ ራሷ ከማስተባበር ባለፈ ሰላማዊ ሰልፍ የሚወጡትን ዩክሬናውያንን ከመደገፍ አልፋ ለሰልፈኞች ብስኩት ስታድል በወቅቱ … [Read more...] about “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች
Archives for March 2022
የምግብ ዘይት በመፀዳጃ ቤት ውስጥ ተከማችቶ ተገኘ
በአዲስ አበባ ከተማ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ በወረዳ 03 ያለአግባብ የተከማቸ የምግብ ዘይት በህዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል። ክ/ከተማው በ11 ሱቆች ላይ ተደረገ ባለው ፍተሻ 442 ሊትር ዘይት በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን አሳውቋል። ፍተሻ የተደረገው በወቅታዊ የዋጋ ንረት ምክንያት ካሉ 6 ቀጠናዎች በ3ቱ ቀጠናዎች ላይ ብቻ መሆኑ ተጠቁሟል። ክ/ከተማው በቁጥጥር ስር የዋለው የምግብ ዘይት ባልተገባ ቦታ መፀዳጃ ቤት ውስጥ ተደብቆ መገኘቱን የገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡ እንደዚህ አይነት ድርጊት የሚፈፅሙትን "ሌባን ሌባ " ሲል እንዲያጋልጥ ጥሪ አቀርቧል። በአግባቡ ስራቸው ላይ የሚገኙ ነጋዴዎች አሁን በያዙት ልክ ዘይትን ወደ ፊት በማምጣት መሸጥ ይኖረባቸዋል የተባለ ሲሆን ህገወጥ ስራዎችን በሚሰሩ ነጋዴዎች ላይ ንግድ ፍቃድ መሰረዝ ጨምሮ ጠበቅ ያሉ እርምጃዎች … [Read more...] about የምግብ ዘይት በመፀዳጃ ቤት ውስጥ ተከማችቶ ተገኘ
166, 800 የአሜሪካን ዶላር፤ 19,850 ዩሮና ለሸኔ ሊተላለፍ የነበረ መሣሪያ ተያዘ
መነሻውን አዲስ አበባ ከተማ ያደረገ አንድ ህገወጥ የገንዘብ አዘዋዋሪ ግለሰብ ዶላር እና ዩሮ በመኪና ጭኖ ወደ ጅቡቲ በጉዞ ላይ እያለ በቁጥጥር ስር ውሏል። ግለሰቡ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ3-68991 በሆነ ኮንቴነር ተሽከርካሪ ላይ 166 ሺህ 800 የአሜሪካን ዶላር እና 19 ሺህ 850 ዩሮ በመጫንና መዳረሻውን ጅቡቲ በማድረግ በመጓዝ ላይ እያለ በተደረገ ጥብቅ ክትትል መያዙን የኢፕድ ምንጮች ገልጸዋል። በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ላይ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በደረሰው ጥቆማ አዘዋዋሪውን ከነ ገንዘቡ በቁጥጥር ስር እንዲውል ማድረጉንም ነው ምንጮቻችን ጨምረው የገለጹት፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ መነሻቸውን ሀረሪ ክልል ሀረር ከተማ ያደረጉ ሶስት ህገወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪ ግለሰቦችም ከእነጦር መሳሪያቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እነዚሁ … [Read more...] about 166, 800 የአሜሪካን ዶላር፤ 19,850 ዩሮና ለሸኔ ሊተላለፍ የነበረ መሣሪያ ተያዘ
በሰባት ወር ውስጥ ከ2.3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ በሕጋዊ መንገድ በዳያስፖራው ወደ አገር ቤት ተልኳል
ዳያስፖራው በ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት ሰባት ወራት ወራት ከ2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ (ሬሚታንስ) በሕጋዊ መንገድ ወደ አገር ቤት መላኩን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ። በ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት ሰባት ወራት ዳያስፖራው 2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ወደ አገር ቤት በሕጋዊ መንገድ እንዲልክ ታቅዶ 2 ነጥብ 35 ቢሊዮን ዶላር መላኩን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል። በበጀት ዓመቱም አራት ቢሊዮን ዶላር ከሬሚታንስ ለመሰብሰብ መታቀዱን አመልክቷል። በተያያዘም በ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት ሰባት ወራት 4 ሺህ 83 የዳያስፖራ አባላት በአገር ውስጥ በሚገኙ ባንኮች 4 ሚሊዮን 953 ሺህ 333 ዶላር ተቀማጭ እንዲያደርጉ ታቅዶ፤4 ሺህ 7 ዳያስፖራዎች ከ3 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተቀማጭ ማድረጋቸውን ገልጿል። ዳያስፖራው … [Read more...] about በሰባት ወር ውስጥ ከ2.3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ በሕጋዊ መንገድ በዳያስፖራው ወደ አገር ቤት ተልኳል
ምኒልክን ከዓድዋ ለመነጠል መሞከር ባርነት መምረጥ ነው
ጀግንነቱን ዓለም መስክሮለታል፣ ስሙን ከፍ አድርጎ ጠርቶታል፣ ታሪክ በማይጠፋ ቀለም፣ በማያረጅ ብራና አስፍሮታል፡፡ ጠላት ሮጦለታል፣ በስሙ ተሸብሮለታል፣ ከእግሩ ሥር ወድቆ ይማሩኝ ንጉሥ ኾይ ብሎለታል፡፡ በጀግንነቱ በጠላቶቹ ልብ ላይ የነገሠ፣ በዝናው ዓለምን ያዳረሰ፣ የጠላቶቹን አንጀት የበጠሰ፣ የወዳጆቹን አንጀት ያራሰ ጀግና ነው እርሱ፡፡ የማይገመት ልብ ያለው፣ ጠላት የማይችለው፣ ጀግንነት፣ ብልሃት፣ አሸናፊነትና ጽናት የታደለው ኃያል ንጉሥ፡፡ ነጭ ባየለበት ዘመን በነጭ ላይ የገነነ፣ የነጭን ኃያልነት የበጣጠሰ፣ የነጭን አብዮት ያፈራረሰ፣ የጥቁርን ክብር የመለሰ፣ ያለቀሱትን እንባቸውን ያበሰ፣ በጨለማ ውስጥ ለነበሩት የደረሰ፣ በድል ብቻ የገሰገሰ፣ በጨለማው ምድር ብርሃን ያበራ፣ ከተራራ የገዘፈ፣ ዘመናትን በክብር ያለፈ ታሪክ የሠራ፣ የጥቁር አባት፣ የነጻነት መሪ፣ … [Read more...] about ምኒልክን ከዓድዋ ለመነጠል መሞከር ባርነት መምረጥ ነው
“ምኒልክ ዛሬም ንጉሥ ነው!”
የዓለም ህዝብ ሁሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ነጭን ድል ያደረገውን የጥቁር ጦር መሪ አጤ ምኒልክን ለማወቅ እጅግ ጓጓ፡፡ ምስላቸውን ለማየት ተቁነጠነጠ፡፡ ሙሉ ታሪካቸውን ለመስማት ተንሰፈሰፈ፡፡ ይህንኑ ተከትሎም፤ “እንኳንም ደስ አለዎት” ለማለት ከቁጥር የበዙ ደብዳቤዎች ይጎርፉላቸው ነበር፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ በፖስታ ቤት በኩል የኢትዮጵያ ቴምብር የተለጠፈበት መልስ እንዲላክላቸው ይጠይቁ ነበር፡፡ ለምን… ? ቴምብሩ ላይ ያለውን የምኒልክን መልክ ለማየት፡፡ ባለ ብዙ ዝናና ክብር ባለቤት የሆኑትን የምኒልክን ጥቁር ፊት ለማየት፡፡ የሰው ሀገር ሰው ሁሉ፤ “ዝናውን እንደሰማሁ መቼ ሄጄ ባየሁት”፣ “በጀግንነቱ እንደ ተማረኩ መች ተጉዤ ባገኘሁት”፣ “ካሁን ካሁን ፈቅዶልኝ ወታደር ሆኜ ባገለገልኩት” ያለላቸው አጤ ምኒልክ የኛ ናቸው፡፡ በዓለም ታሪክ … [Read more...] about “ምኒልክ ዛሬም ንጉሥ ነው!”
፻፳፮ኛው የዓድዋ በዓል በፎቶ
“… የተተከለው ድንኳን ሲታይ ከብዛቱ የተነሳ አፍሪካ ኤሮጳን ለመጠራረግ የተነሳች ይመስላል፡፡ የጦርነቱ ዕለት ኢትዮጵያውያኑ ደማቅ ቀለም ያለው ካባ ለብሰው፤ ጠመንጃና ጦር ይዘው፤ ጎራዴ ታጥቀው፤ የነብር ያንበሳ ቆዳ ለብሰው፤ አዝማሪዎቹ እየዘፈኑ፤ ቄሶች፤ ልጆች፤ ሴቶች ሳይቀሩ ፀሐይዋ ፈንጠቅ ስትል በተራራው ላይ በታዩ ጊዜ የኢጣሊያን ክፍል አሸበሩት” የበርክለይ ምስክርነት፤ አጤ ምኒልክ በጳውሎስ ኞኞ፤ ገጽ 195 ዛሬ የተከበረው ፻፳፮ኛው የዓድዋ በዓል በእምዬ ምኒልክ አደባባይና በተለያዩ አካባቢዎች ተከብሯል። በፎቶ ይህንን ይመስላል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ፻፳፮ኛው የዓድዋ በዓል በፎቶ