ባለፉት 5 ዓመታት ከተወለዱ 10 ሚሊዮን ህጻናት ውስጥ 84 በመቶዎቹ ያልተመዘገቡ ናቸው ተባለ። የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ባለፉት 5 ዓመታት የመዘገበው የውልደት ኩነት 16 በመቶ ብቻ መሆኑንና ይህም 84 በመቶ የሚሆኑት ተወላጆች በመንግስት ሰንድ ላይ ያልተመዘገቡ እና የማይታወቁ ናቸው ብሏል። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጀብ ጀማል ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ከአውሮፓውያኑ 2012 ጀምሮ 10 ሚሊየን ህፃናት ይወለዳሉ የሚል ግምት የነበረ ቢሆንም በወሳኝ ኩነት የተመዘገቡት ግን 2 ሚሊየን ያህሉ ብቻ ናቸው። በዚህ መሀል ያልተመዘገቡትን 8 ሚሊየን ህፃናት ስለመወለዳቸው እና ስለመኖራቸው መንግስት እንደማያውቅ ነው ዋና ዳይሬክተሩ የተናገሩት። በህገ መንግስቱ መሠረት ህፃናት እንደተወለዱ በ90 ቀናት ውስጥ መመዝገብ፣ ስም ማግኘት እና … [Read more...] about መዝገብ የማያውቃቸው 8.4 ሚሊዮን ህጻናት
Archives for August 2020
ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራና የነዋሪዎች ቅሬታ!
በአካባቢው ያለውን ህገ-ወጥ የመሬት ወረራ ለሚመለከታቸው አካላት ቢያሳውቁም እስካሁን መፍትሄ አለማግኘታቸውን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሃይሌ ጋርመንት አካባቢ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ህገ ወጦቹ በአካባቢው የሚገኘውን 20 ሜትር ስፋት ያለው መንገድ 10 ሜትር ገፍተው በማጠር አጥብበውታል ሲሉ ነው ለኢዜአ የገለጹት። ጉዳዩን ለወረዳው አስተዳደርና ለክፍለ ከተማው መሬት ይዞታ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ቢያመለክቱም ወንጀሉን ለማስቆም ያላቸው ዝግጁነት አናሳ እንደሆነ ነው የገለጹት። “ቦታውን ካጠሩት ሰዎች ጋር ተደራደሩ” ከሚል ምላሽ በቀር ሌላ ምላሽ እንዳልሰጧቸውም ኢዜአ ዘግቧል። የክፍለ ከተማው መሬት ይዞታ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ “በፅሁፍ ምላሽ ሰጥተናል” ቢሉም የኢዜአ ሪፖርተር ማስረጃ ጠይቆ ማግኘት አልቻለም። የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ … [Read more...] about ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራና የነዋሪዎች ቅሬታ!
አቶ ለማ መገርሳ ለምን ታገዱ?
ባለፉት ቅዳሜና እሁድ ለሁለት ቀናት ከተመሰረተ የመጀመሪያውን ኮንፌረንሱን ያካሄደው የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ ነው ትናንት ማምሻውን ስብሰባውን ያጠናቀቀው። በዚሁ ኮንፌረንስ ከተላለፉ ውሳኔዎች በትልቁ ትኩረት የሳበው ጉዳይም ከወራት በፊት በፓርቲው ተሳትፎያቸው እየደበዘዘ የመጣው፤ አሁን ሃገርን እያስተዳደረ ላለው የለውጥ መንግስት ስኬታማነት ግን የአንበሳውን ድርሻ ተጫውቷል የሚባልላቸው የአቶ ለማ መገርሳ እና ሌሎች ሁለት የፓርቲው አመራሮች ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት መታገድ ነው። የኮንፌረንሱን መጠናቀቅን ተከትሎ መግለጫ የሰጡት የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ኮንፌረንሱ ፓርቲውንና ፓርቲው የሚያስተዳድረውን ክልል አጋጥሞታል በሚል እንደ ክፍተት ከገመገማቸው ጉዳዮች አንደኛው የአመራሮች በኃላፊነታቸው ልክ አለመስራት … [Read more...] about አቶ ለማ መገርሳ ለምን ታገዱ?
108 ሕገወጥ ማኅተሞች ተያዙ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጎተራ አካባቢ በሚገኝ አንድ የጋራ መኖሪያ ቤት ውስጥ 108 ህገወጥ ማህተሞች መያዙን አስታወቀ። በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወርዳ 4 ጎተራ ኮንዶሚኒየም ውስጥ 108 ማህተሞች እና የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን ለተለያዩ ህገ-ወጥ ተግባራት ሲጠቀሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሰር መዋሉን ፖሊስ ገልጿል። በከተማችን አዲስ አበባ በተለያዩ ጊዚያት ሐሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም ህገ-ወጥ ተግባር ሲፈፅሙ በፖሊስ ቁጥጥር ውለው በህግ አግባብ የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸውን ግለሰቦች የወንጀል ድርጊት መረጃ በመስጠት ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክቶችን ማስተላለፋችን ይታወሳል። አሁንም በአንዳንድ አካባቢ መሰል የወንጀል ድርጊቶች ሲፈጸሙ ይስተዋላል በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወርዳ 4 ጎተራ ኮንዶሚኒየም ውስጥ ሀምሌ 1ቀን 2012ዓ.ም. ሁለት ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር … [Read more...] about 108 ሕገወጥ ማኅተሞች ተያዙ
ጃዋርና በቀለ ገርባ ለቅድመ ምርመራ የተሰየመው ዳኛ ይነሣልን ሲሉ አመለከቱ
አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ የ14 ተጠርጣሪ ጠበቆች ለቅድመ ምርመራ የተሰየመው ዳኛ ገለልተኛ ሆኖ ጉዳያችንን ሊመለከትልን ስለማይችል ይነሣልን ሲሉ ማመልከታቸው ተገለጸ። አሥራ አንዱም የተጠርጣሪ ጠበቆች በሰባት ገጽ ባቀረቡት አቤቱታቸው ሕግ ጠቅሰው ዳኛው ገለልተኛ ሆኖ ጉዳያችንን መመልከት አይችልም በማለት ነው ያመለከቱት። የምርመራ መዝገቡን ሲመለከቱ የቆዩት የዕለቱ ዳኛ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ 25/88 አንቀጽን በመጥቀስ የቀረበው አቤቱታ ተጨባጭነት የሌለው፣ በማስረጃ ያልተደገፈ በመሆኑ ልነሣ አይገባም በማለት ወስነዋል። ይሁን እንጂ በአዋጁ መሠረት መዝገቡ በሬጅስትራር በኩል ለፍርድ ቤቱ ቀርቦ በተመሳሳይ ሌላ ዳኛ አይቶ ውሳኔ እስኪሰጥበት እና መጥሪያ እስከሚደርሳቸው ድረስ ተጠርጣሪዎቹ ባሉበት በፖሊስ ማረፊያ እንዲቆዩ የፌዴራል … [Read more...] about ጃዋርና በቀለ ገርባ ለቅድመ ምርመራ የተሰየመው ዳኛ ይነሣልን ሲሉ አመለከቱ
የጃዋር፣ የበቀለና የእስክንድር የፍርድ ቤት ውሎ
“የመናገር መብት ከሌለን ለምን እንመጣለን?” ተጠርጣሪ በቀለ ገርባ “በጠበቆቻችሁ አማካይነት በቂ ጊዜ ተሰጥቷችሁ ተናግራችኋል” ፍርድ ቤት በተጠረጠሩበት የእርስ በርስ ግጭት በማነሳሳትና በሌሎች የወንጀል ድርጊቶች ከሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ጃዋር መሐመድና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች፣ የጊዜ ቀጠሮ ምርመራ መዝገባቸው ተዘግቶ በአንድ የምርመራ መዝገብ ተጠቃለው በተከፈተባቸው የቀዳሚ ምርመራ መዝገብ ላይ ያቀረቡት ተቃውሞ ውድቅ ተደረገ። ተጠርጣሪዎቹ ያቀረቡትን ተቃውሞ ውድቅ ያደረገው የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ልደታ ማስቻያ አንደኛ ወንጀል ችሎት ሲሆን፣ ከፌዴራል ፖሊስ የጊዜ ቀጠሮ ምርመራ ቡድን የምርመራ መዝገቡን ተረክቦ፣ ቀዳሚ ምርመራ በተመሳሳይ ፍርድ ቤት መክፈቱንና ምስክሮችን ለማሰማት ትዕዛዝ … [Read more...] about የጃዋር፣ የበቀለና የእስክንድር የፍርድ ቤት ውሎ
“… በዓለም እስካሁን ብቸኛው በጣም የሚጠላትን አገር የመራ ፓርቲ ህወሃት ብቻ ነው” ሙስጠፌ ዑመር
ህወሃት የሚጠላውን ነገር ሁሉ “አማራ ነህ” ይለዋል። ዶ/ር ዐቢይ ኦሮሞ እንደሆነ ስለማያውቁ ሳይሆን የጠሉትን ሁሉ አማራ ብለው መጥራት ስለሚፈልጉ ነው። ይኸውም ለነሱ አማራ ማለት ጠላት ማለት ነው። “በነገራችን ላይ ነፍጠኛና ትምክህተኛ ማለት ለአማራ ህዝብ የሰጡት የብዕር ስም ነው”። አማራ ጠላት ነው የሚለውን ትርክት ይዘህ ስታያቸው ቃላቶቹ አንድን ህዝብ ለማጥፋት የተሰሩ እንደሆኑ ይገባሀል። ... ህወሃት ማለትኮ አገር እየመራ አገራዊ ተቃርኖዎችን የሚተነትን አስማተኛ ድርጅት ነው። የትም ዓለም አገር እየመራ አገሪቱን የሚመራበት አካሄድ ትክክል ባለመሆኑ ሊፈርስ ይችል ይሆናል እንጂ መሪው አገር እንድትፈርስ የሠራ የለም - ከህወሃት ውጭ። አሁንም አይደለም ከግብጽ ህውሃት ከየትኛውም ኃይል ይሁን ኢትዮጵያን የሚያጠፋለት ከሆነ አይተባበርም ማለት ሃሰት ነው።... ሙስጠፌ … [Read more...] about “… በዓለም እስካሁን ብቸኛው በጣም የሚጠላትን አገር የመራ ፓርቲ ህወሃት ብቻ ነው” ሙስጠፌ ዑመር
አወዛጋቢው የሽመልስ አብዲሳ ሙሉ ንግግር ትርጉም
ኢህአዴግ የተሰራው ለህወሃት ነውና የተሰራበት ምክንያት ደግሞ ስልጣን ላይ ለመቆየት ነው። እኛም ብልፅግናን የሰራነው ከስልጣን ለመውረድ አይደለም። ብልፅግና ደግሞ ወደዳችሁም ጠላችሁም የኛ ነው። እኛ ነን የሰራነው። ለእኛ እንደሚሆነን አድርገን። በተመሳሳይ መንገድ ህወሃት ኢህአዴግ እንዲመቸው አድርጎ ነበር የሰራው። ኢህአዴግ ገና ሲፈጠር የቀድሞዎቹ የኦህዴድ መስራች ሰዎች ለመታገል ሞክረዋል። ግን አልቻሉም። ያልቻሉበት ምክንያት ደግሞ ጠብመንጃ ስለሌላቸው፣ ሀይል ስለሌላቸው ነበር። ኢህአዴግ ሳይመሰረት በፊት አሁን የምናወራውን ነገር አንስተው ነበር። አሁን ዶ/ር ቢቂላ ያነሳውን ነገር ሁሉ አንስተው ነበር። እነ ኢብራሂም መልካ ተገምግመው የተባረሩት በዚህ ነው። ስለ ውክልና እና ስለ ፍትሃዊነት ስለ ጠየቁ። ግን majorityን minority የሚያደርጉበት instrument ስለሆነ፤ … [Read more...] about አወዛጋቢው የሽመልስ አብዲሳ ሙሉ ንግግር ትርጉም
ከትግራይ ክልል የከዱ 30 የፀረ ሽምቅ እና የልዩ ኃይል አባላት አማራ ክልል ገቡ
ከትግራይ ክልል የከዱ የፀረ ሽምቅ እና የልዩ ኃይል አባላት ወደ አማራ ክልል መግባታቸው ታውቋል። ከሰሞኑ ወደ ክልሉ የገቡ የፀረ ሽምቅ እና የልዩ ኃይል አባላት 30 ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ 20ዎቹ 17 ክላሽ ሸንኮቭ እና ሦስት ሽጉጦችን እንደያዙ በደባርቅ በኩል መግባታቸውን የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ ለምለሙ ለአብመድ አረጋግጠዋል። ተጨማሪ የጸረ ሽምቅና የልዩ ኃይል አባላትም እየከዱ እየገቡ መሆኑ ተመላክቷል። አስሩ ደግሞ በጠገዴ በኩል ነው ወደ አማራ ክልል የገቡት። ከእነዚህ መካከል ዘጠኙ ከነሙሉ ትጥቃቸው፣ አንዱ ያለ ጦር መሳሪያ እንደገቡ ነው የተገለጸው። የጸጥታ አባላቱ ሕዝቡ ሀሳቡን በነጻነት ማራመድ አለመቻሉን እና በክልሉ እየተካሄደ ያለውን የጦርነት ቅስቀሳ መቃወማቸውን ለመክዳታቸው በምክንያትነት አቅርበዋል ብለዋል ዋና አስተዳዳሪው። “ምርጫ … [Read more...] about ከትግራይ ክልል የከዱ 30 የፀረ ሽምቅ እና የልዩ ኃይል አባላት አማራ ክልል ገቡ
ከሚገድለኝ ሰይጣን ይልቅ የሚሰድበኝ ባለስልጣን ይሻለኛል! ሽመልስ የተናገረው በወቅቱ ትክክል ነው‼️
አቶ ሽመልስ አብዲሳ “በትላንትናው እለት የተናገረው ነው” ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ከሰባት ወር በፊት የብልፅግና ፓርቲ ገና በምስረታ ሂደት ላይ እያለ የተናገረው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። በወቅቱ የድርጅቱን አባላትና አመራሮች በኦቦ ለማ መገርሳ፣ ወ/ሮ ጠይባ እና በዶ/ር ሚልኬሳ ከሚመራው ብሔርተኛ ቡድን ለመነጠልና በድርጅቱ ውስጥ ተፈጥሮ በነበረው የኃይል ሹኩቻ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት በሚደረግ ጥረት የተናገረው እንደሆነ ተረጋግጧል። አቶ ሽመልስ የተናገረበት ግዜና ቦታ ምን ያህል የተለያየ ቢሆንም አዲስ አበባን አስመልክቶ የተናገረው ነገር መቼም፥ እንዴትም ትክክል አይሆንም። ይሁን እንጂ በወቅቱ ድርጅቱ ውስጥ የጃዋር መሃመድ ጉዳይ አስፈፃሚ የነበሩት ከላይ የተጠቀሱት የኦዴፓ አመራሮች ከኮዬ_ፈቼ ኮኖደሚኒዬም ጋር በተያያዘ ሲያራምዱት የነበረው አቋምና ጉዳዩ በብሔርተኞቹ ዘንድ … [Read more...] about ከሚገድለኝ ሰይጣን ይልቅ የሚሰድበኝ ባለስልጣን ይሻለኛል! ሽመልስ የተናገረው በወቅቱ ትክክል ነው‼️