ህወሃት የሚጠላውን ነገር ሁሉ “አማራ ነህ” ይለዋል። ዶ/ር ዐቢይ ኦሮሞ እንደሆነ ስለማያውቁ ሳይሆን የጠሉትን ሁሉ አማራ ብለው መጥራት ስለሚፈልጉ ነው። ይኸውም ለነሱ አማራ ማለት ጠላት ማለት ነው።
“በነገራችን ላይ ነፍጠኛና ትምክህተኛ ማለት ለአማራ ህዝብ የሰጡት የብዕር ስም ነው”። አማራ ጠላት ነው የሚለውን ትርክት ይዘህ ስታያቸው ቃላቶቹ አንድን ህዝብ ለማጥፋት የተሰሩ እንደሆኑ ይገባሀል።
… ህወሃት ማለትኮ አገር እየመራ አገራዊ ተቃርኖዎችን የሚተነትን አስማተኛ ድርጅት ነው። የትም ዓለም አገር እየመራ አገሪቱን የሚመራበት አካሄድ ትክክል ባለመሆኑ ሊፈርስ ይችል ይሆናል እንጂ መሪው አገር እንድትፈርስ የሠራ የለም – ከህወሃት ውጭ።
አሁንም አይደለም ከግብጽ ህውሃት ከየትኛውም ኃይል ይሁን ኢትዮጵያን የሚያጠፋለት ከሆነ አይተባበርም ማለት ሃሰት ነው።… ሙስጠፌ ዑመር (የሶ/ክ/ር/መስተዳድር) ለፋና ቲቪ ከተናገሩት የተወሰደ፤ በነጋሪት የተጻፈ።
በሌላ ዜና ሰሞኑን በአፋር በደረሰው ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ የተጎዱ ወገኖችን ለመታደግ የሶማሊ ክልል የሕክምና ባለሙያዎችን ያካተተ ቡድን ልኳል። ከቡድኑ ጋር የተለያዩ የምግብና የቁሳቁስ ዕርዳታም አብሮ እንደተላከ ከክልሉ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። እንዲህ ዓይነቱን የፈጥኖ ደራሽ ዕርዳታ በመስጠት ሙስጠፌ ዑመር የሚመሩት የሶማሊ ክልል ቀዳሚነቱን ይዟል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply