
ባለፉት ቅዳሜና እሁድ ለሁለት ቀናት ከተመሰረተ የመጀመሪያውን ኮንፌረንሱን ያካሄደው የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ ነው ትናንት ማምሻውን ስብሰባውን ያጠናቀቀው።
በዚሁ ኮንፌረንስ ከተላለፉ ውሳኔዎች በትልቁ ትኩረት የሳበው ጉዳይም ከወራት በፊት በፓርቲው ተሳትፎያቸው እየደበዘዘ የመጣው፤ አሁን ሃገርን እያስተዳደረ ላለው የለውጥ መንግስት ስኬታማነት ግን የአንበሳውን ድርሻ ተጫውቷል የሚባልላቸው የአቶ ለማ መገርሳ እና ሌሎች ሁለት የፓርቲው አመራሮች ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት መታገድ ነው።
የኮንፌረንሱን መጠናቀቅን ተከትሎ መግለጫ የሰጡት የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ኮንፌረንሱ ፓርቲውንና ፓርቲው የሚያስተዳድረውን ክልል አጋጥሞታል በሚል እንደ ክፍተት ከገመገማቸው ጉዳዮች አንደኛው የአመራሮች በኃላፊነታቸው ልክ አለመስራት መሆኑን ጠቁመዋል።
በዚህም “በየደረጃው ያሉት አመራሮች ተጨባጭ ውጤት ከማስመዝገብ ይልቅ አውርተው የመኖር አዝማሚያ መስተዋሉ ተገምግሟል” የሚሉት የጽህፈት ቤት ኃላፊው በቅርቡ በክልሉ ከተፈጠረው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ ክፍተት አሳይተዋል የተባሉ ከ800 በላይ የወረዳ፣ እንዲሁም 117 የዞንና ከተማ አስተዳደር አመራሮችን ለማጥራት መታሰቡን አስረዱ።
መሰል ውሳኔ በታችኛው የአመራር እርከን ብቻ መቆም የለበትም የሚል ሃሳብ ከአባላቱ ተነስቷል ያሉት አቶ ፍቃዱ ተሰማ በተደረገው ግምገማ ለጊዜው ሶስት የድርጅቱ የበላይ አመራሮች ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ታግደዋል። ከነዚህ መሃከል አንደኛው የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንትና የአሁኑ የመከላከያ ሚንስትር አቶ ለማ መገርሳ ናቸው።
የጽህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ፍቃዱ ተሰማ አቶ ለማ መገርሳ ከማዕከላዊ ኮሚቴው የታገዱበትን ምክኒያት ሲያስረዱም፤ “ጓድ ለማ በአንድ ወቅት ሃሳባቸውን በሚዲያ መግለጻቸው ይታወሳል። ያንን ተከትሎ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ ከመከረ በኋላ እሳቸውም ተሳስቻለሁ ብለው ይቅርታ ጠይቀው ነበር። ከዚያም በአመራርነታቸው እንዲቀጥሉ ተደረገ። ይሁንና በብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚም ሆነ ማዕከላዊ ኮሚቴ እንዲሁም ኃላፊነቱን ሰጥቶአቸው የነበረውን አካል ወክለው ድምጽ እንዲያሰሙ ቢጠየቁም ያን አላከበሩም። ይህ ደግሞ በፓርቲው መተዳደሪያ አሰራር ክልክል በመሆኑ የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች ጉዳዩን ካዩት በኋላ እኚ ሰው ምንም እንኳ አገራዊ ለውጥ በማምጣት ሂደት ውስጥ ትልቅ ክብር የሚገባቸው ቢሆኑም፤ ማንም ከፓርቲውና ከኦሮሞ ህዝብ በላይ ባለመሆኑ፣ በዚህ ኮንፌረንስ ላይም እንዲሳተፉ በተደጋጋሚ ተጠይቀው መሳተፍ ባለመቻላቸው፣ ሃሳባቸውንም ዴሞክራሳዊ በሆነ መንግድ ወደ መድረክ ለማቅረብ ፈቃደንነትን ባለማሳየታቸው፣ ለጊዜው ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ታግደዋል” ብለዋል።
አቶ ለማ መገርሳ እንደ ክፍተት የተነሳባቸውን ነጥቦች ለማስተካከል ፈቃደኛ ሲሆኑ ወደ የፓርቲው አመራርነት መመለስ እንደሚችሉ ውሳኔ ላይ መደረሱም ነው የተገለጸው። ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት የታገዱ ሌሎች የፓርቲው አመራሮች ዶ/ር ሚልኬሳ ሚዴጋ እና ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን ናቸው።
አቶ ፍቃዱ ለእነዚህ አመራሮች መታገድም ምክኒያቱን ሲያስረዱ፤ “ዶክትር ሚልኬሳ ሚዴጋ የፓርቲውን አሰራር ጠብቀው እዲሳተፉ ብጠየቁም መፈጸም ስላልቻሉ፣ ያላቸውን የሃሳብ ልዩነትም በፓርቲው ውስጥ ማንጸባረቅ ሲችሉ ወደ ውጪ በመውሰዳቸው በፓርቲው ደምብ መሰረት በአመራርነት ሊያስቀጥላቸው ባለመቻሉ ነው ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት የታገዱት።
በርግጥ ይህ ጉዳይ በቀጣይነት በብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሚረጋገጥ ነው የሚሆነው። ወ/ሮ ጠይባ ሀሰንም በተለያዩ መንገዶች ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ብቆዩም ከአባላቱ በተነሳው ሃሳብ መሰረት በተለያዩ አከባቢዎች በተፈጠሩ ችግሮች ላይ በእጅ አዙር ተሳትፈዋል የሚል ጥርጣሬ ስለተፈጠረ ጉዳያቸው እስኪጣራ እሳቸውም ታግደዋል” ነው ያሉት።
ኮንፌረንሱ የፓርቲው ውስጣዊ ችግር ነው ብሎ የገመገመው ሌላው ጉዳይ የአመራሮቹ የተለያዩ ቦታዎችን መርገጥ ነው ተብሏል። ችግሩ በየአመራር እርከኑ በሰፊው የተስተዋለ ቢሆንም በርካቶቹ ህሳቸውን አውርደው በቀጠይነትም እንደሚሰራበት ነው የተጠቆመው። ሌላው በየደረጃው ያሉ አመራሮች ይታሙበታል የተባለው የሌብነት ጉዳይ እንዲለዩና ማስተካከያ እንዲደረግበትም አቅጣጫ መቀመጡ ተገልጿል። ውሳኔዎቹ የተላለፉትም በመገፋፋት ስሜት ሳይሆን የፓርቲው አሰራርና የህግ የበላይነትን ለማስከበር በማሰብ ነው ሲሉም አስረድተዋል አቶ ፍቃዱ ተሰማ።
የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ በኮንፌረንሱ የአርቲስ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን እና ግድያውን ተከትሎ በክልሉ በተፈጠረው አለመረጋጋት በዜጎች ላይ የደረሰውን ጉዳት በማውገዝ “ለውጡን ለማደናቀፍ እየጣሩ ነው” ያሏቸውን ህወሃትና ኦነግ ሸኔን እታገላቸዋለሁ ብሏል።
በሃይማኖት መሃከል የነበሩ ችግሮችን መፍታት፣ ስኬታማ የዲፕሎማሲ ስራ፣ ገጠርን ያማከለ የልማት ፖሊሲ፣ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ከችግር የማውጣት ስራ፣ የጸጥታ ዘርፍ ሪፎርም እና በህዝብ ምጣነ ተሳትፎን የሚፈቅደውና አምስት ቋንቋዎችን ያካተተው የፓርቲ ሪፎርምን ኮንፌረንሱ ስኬታማ ተግባራት የነበሩ ናቸው ሲል ገምግሟል።
©ጀርመን ድምፅ
የአቶ ለማ ባህሪ የተቀየረው ሚኒሶታ መመላለስ ከጀመሩ ወዲህ ነው። ያው በኦሮሞ ወልጋዳ እኛ ብቻ በሚለው የፓለቲካ ሰንሰለት የተጠለፉት ደግሞ በዚሁ ስቴት “የካውንስሌት ቢሮ” ለመክፈት በመጡ ጊዜ በድብቅ ከተመከረው የፓለቲካ ጥንስስ ጭማሪ በመቃመሳቸው ነው። የሚያሳዝነው በሃገሪቱ የደረሰውን በደልና ግፍ ሰዎች በመረጃ ሲናገሩ እኮ ታዲያ የሞተው ቁጥሩ የሚበዛው የኦሮሞ ተወላክ እኮ ነው ይሉናል። ይህ የፓለቲካ ሽንክነት ነው። ለእኔ የህዝባችን ደም ቋንቋን ጎጥናና ዘርና ሳያማክል አንድ ነው ባይ ነኝ። ለክልል ፓለቲከኞች ደግሞ ሁሌ ምንዛሪያቸው በክልልና በጎሳ ነው። ማንም ይሁን ምንም የፓለቲካ ድርጅትና ሃይል ያለ ጉድለት አለሁ የሚል የለም። ሁሉም የራሱ የሆነ ድክመትና እይታ አለው። ችግሩ ሁሌም በነገሩና በፎከሩበት ጎራ ላይ አለመገኘታቸው ነው። በለውጡ ሂደት ግባር ቀደም የነበረ ለማ ልቡ ሻክሮ አፍቃሪ ኦሮሞ ብቻ የሆነበት መንገድ የታወቀ ነው። ከጃዋር ጋር አፍ ለአፍ ቀርቦ መጫወት ከጀመረ በህዋላ ጥበቃም ያቆመለት አቶ ለማ በራሱ ትዕዛዝ ነው ይባላል። አቶ ለማ የቅርብ የትግል ጉድን ዶ/ር አብይን ከከዳ ለሃገርና ለወገን ይጠቅማል ብሎ ለማሰብ ይከብዳል። ግን እኮ ደጋግሜ ፓለቲካ የወሽካቶች ፊሽካ ነው የምለው ለዚያ ነው። ግብ ሳይገባ ፊሽካ ነፍቶ ኳሷን ማህል ሜዳ ላይ ማድረግ አይነት። ተጫዋች አልባ አጫዋች።
በቅርብ እንዲህ ሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ አበባ ከደረሰ በህዋላ በነበረው የአየር ጸባይ ማረፍ ይቸገራል። ካፒቴኑ ያለውን ችግር አስረድቶ ከ 45 ደቂቃ በረራ በህዋላ አስመራ ላይ እናርፋለን በማለት እዚያው ሂዶ አረፈና ቆይቶ አዲስ አበባ ገባ። የሰላም ፍሬ ይህ ነው። ግብጽ የኤርትራውን መሪ በመደለል የጦር ሰፈር በኤርትራ ምድር ለመመስረት የሞከረቸው የከፋፍለህ ግዛው እቅድ በመክሸፉ ፕሬዝዳንቱ ድሮም ቢሆነ በራሳቸው አስበው የሚኖሩ በመሆናቸው አል ሲሲን አፍንጫህን ላስ ማለታቸው በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ላለው ሰላም ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳያል። ግን ግብጾች አይተኙልንም። መጠንቀቅ አለብን! በዚሁ ሂሳብ መቀሌ ላይ ወደ መሸገው ወያኔ ስመለስ 46 ዓመት አፍኖ የያዘውን የትግራይ ህዝብ ዛሬም በባሰ ሁኔታ በማፈን ያን ሩህሩህና ሃገር አፍቃሪ ህዝብ በየቀኑ እየገደለው እንደሆነ እንሰማለን። ወያኔ ወንድም ወንድሙን በህይወቱ የሚቀብር፤ እልፍ የትግራይ ልጆች ጥያቄ ጠይቀዋል፤ አመራር ተቃውመዋል በመባል በሚስጢርና በይፋ ብዙዎች ሀለዋ ወያኔ (ባዶ ስድስት) ውስጥ ተገለዋል። አሁን አማራ መጣብህ፤ ኤርትራ መጣብህ የዶ/ር አብይ መንግስት ሊወርህ ነው የሚሉት የፈጠራ ወሬ ለራሳቸው ስልጣን ቋሚነት እንጂ ለትግራይ ህዝብ ጀሪካ ውሃ አያመነጭም። ወያኔ የማፊያ ቡድን ነው። ለዚህም ነው ኦነግና ሌሎችም ከወያኔ ጎን የሚሰሩ ሃይሎች ሁሉ ማፊያ ባህሪ የሚላበሱት። የኦሮሞን ህዝብና ስም ተገን አርገው አንገት የሚቀሉት፤ ነፍሰጡር ሴት ሆድ የሚቀድት፤ ቤትና ንብረት የሚያቃጥሉት። በምዕራብ አርሲ፤ በሻሸመኔ፤ በባሌ፤ በሃርር፤ በጂማ ወዘተ የታየው ጭካኔና ዘረፋ በወያኒያዊ ባህሪ የተለወሰ ነው። ባህርዳር ላይ በአልሞ ተኳሽ ሰዎች ሲመቱ ለእርዳታ የቀረቡትን ሁሉ ነው ወያኔ የገደለችው። የህክምና ባለሙያዎችን ሳይቀር። ይህ ነው የወያኔ ግፍ። ሶዶማዊው ወያኔ በሰው ፍጥረት ላይ ሽንት የሚሸና ቆለጥ ላይ ውሃ የሚያንጠለጥል፤ በሴት እና በወንድ ብልቶች ምናምኔ ነገር ከቶ የሚስቅ፤ ጥፍር በፒንሳ የሚያወልቅ የእብዶች ስብስብ ነው። ለትግራይ ህዝብም ሆነ ለቀሪው የሃገራችን ህዝብ መከፋፈልንና መገዳደልን ያስተማረ መሰሪ ድርጅት ነው። አንባቢ ታዲያ ይህ ሁሉ ከአቶ ለማ መታገድ ጋር ምን አገናኘው ይል ይሆናል። ይገናኛል። ስልጣን ጭንቅላት ላይ ሲወጣ ሰው ያስጠላል። ራስን ብቻ ያሳያል። የአቶ ለማም ኩርፊያና በኦሮሞ የፓለቲካ ልክፍቶች መለከፍ ከዚሁ ማን ሊነካኝ ነው ከሚል አስተሳሰብ የመነጨ ነው። ኦሮሞነት ብቻውን ሱስ ሆኖበት የምናየው ለዚያ ነው። ህብረ ብሄርነት የጠላው የኦሮሞ ፓለቲከኞች ስብስብ እይታው ሁሉ ብቀላና ልዪነትን ማጉላት ነው። ተፋቱ፤ አትግዙ፤ አትሽጡ፤ በቋንቋቸው አትናገሩ። የድንጋይ ዘመን አስተሳሰብ። ግን እኮ የኦሮሞ ቋንጭራ አንጋች ጭፍራዎች ያን ሁሉ ህይወትና ሃብት ሲያወድሙ ዝም ያለው መከላከያ በወላይታ ሆነ በተባለው ነገር ላይ ፈጥኖ ደርሶ ሰዎችን መግደሉ ካለፈው ተምረናል ለማለት ይሆን? በእኔ እምነት የማንም ዘር ይሁን ማንም ቆንጨራ ይዞ ሰው ማረድ ከጀመረ በቅድሚያ እንዲበተኑ ማስጠንቀቂያ በመሰጠት አሻፈረኝ ካሉ የሚገባቸውን መስጠት ተገቢ ይመስለኛል። ዝም ብሎ ብዙ እኮ የሞተው ኦሮሞ ነው ማለት የሰውን ደም ማራከስ ነው። ሁሉም ህይወት ነው። ግን ጥቃቱ የተፈጸመው በዘር፤ በሃይማኖት ዙሪያ እንደ ነበረ የዓይን ምስክሮች የሚነግሩን እናምናለን ከመንግስት መግለጫ ይልቅ። ከገደሉን በላይ ገዳዪዎች ጉዳዪን የሚያጣጥሉ የኦሮሞ ጽንፈኞችና አንዳንድ የማእከላዊ መንግስቱ ባለስልጣናት ናቸው። ይህ የማማታት ፓለቲካ ለማንም አይበጅም። ዋ በህዋላ ሃገሪቱ እንደ ሶሪያና ሊቢያ ትሆንና አትራፊ አይኖርም። እናስብ። በቃኝ!
የኣቶ ለማ መገርሳ ከስራቸው መታገድን በተመለከተ ስናወራ መጀመሪያ፤ የብዙኃኑ ሃሳብ ከሆነ፤ ጥፋቱ የሚያሳግዳቸው ከሆነ፤ ያለፈው ግብራቸውን በማቅረብና በገንዘብ፤ የግለሰቡ በቦታው መቆየት ፓርቲውን የሚጎዳ ከሆኑ፤ ግለሰቦችን ከቦታ እያስነሱ መቀያየር ለፓርቲው ጉዳት የማያመጣ ከሆነ፤ እናም ሌላም ሌላም መታዘቡ ጥሩ ነው።