ከትግራይ ክልል የከዱ የፀረ ሽምቅ እና የልዩ ኃይል አባላት ወደ አማራ ክልል መግባታቸው ታውቋል። ከሰሞኑ ወደ ክልሉ የገቡ የፀረ ሽምቅ እና የልዩ ኃይል አባላት 30 ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ 20ዎቹ 17 ክላሽ ሸንኮቭ እና ሦስት ሽጉጦችን እንደያዙ በደባርቅ በኩል መግባታቸውን የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ ለምለሙ ለአብመድ አረጋግጠዋል።
ተጨማሪ የጸረ ሽምቅና የልዩ ኃይል አባላትም እየከዱ እየገቡ መሆኑ ተመላክቷል። አስሩ ደግሞ በጠገዴ በኩል ነው ወደ አማራ ክልል የገቡት። ከእነዚህ መካከል ዘጠኙ ከነሙሉ ትጥቃቸው፣ አንዱ ያለ ጦር መሳሪያ እንደገቡ ነው የተገለጸው።
የጸጥታ አባላቱ ሕዝቡ ሀሳቡን በነጻነት ማራመድ አለመቻሉን እና በክልሉ እየተካሄደ ያለውን የጦርነት ቅስቀሳ መቃወማቸውን ለመክዳታቸው በምክንያትነት አቅርበዋል ብለዋል ዋና አስተዳዳሪው። “ምርጫ ይካሄድ” የሚለውን ሀሳብ ያልደገፉ በርካቶች ስለመታሰራቸውም ተናግረዋል ነው ያሉት አቶ ወርቁ።
አብመድ
Leave a Reply