ዓለምአቀፉ የፖሊስ መሥሪያ ቤት (ኢንተርፖል) እንደሚለው ከሆነ አሸባሪዎችን የማድረቂያው አንዱ መንገድ የገንዘብ እንቅስቃሴያቸውን መከታተል ነው። መ/ቤቱ አሸባሪዎችን በገንዘብ የመርጃ መንገዶች ብሎ የሚከተሉትን አስፍሯ፤ ዕርዳታ ከደጋፊዎች በማሰባሰብ፣ በማጭበርበር፣ ትርፍ አልባ ድርጅት በመመሥረትና አለአግባብ በድርጅቱ ስም መበልጸግ (OMN በአሜሪካ አገር በትርፍ አልባ ድርጅትነት የተመዘገበ መሆኑን ልብ ይሏል)፣ ሰዎችን አፍኖ በመውሰድና በምላሹ ካሣ በመጠየቅ፣ በሕገወጥ ንግድ በመሠማራት (ይህም በነዳጅ፣ በከሰል፣ በአልማዝ፣ በወርቅና በአደንዛዥ ዕጽ የሚጠቀልል ነው)። ይህንን የገንዘብ (የዕርዳታ ድጋፍ) ማሰብሰብና ማዘዋወር ለመቆጣጠር በአገራት መካከል መረጃ የሚለዋወጥና ደረጃ የሚያወጣ Financial Action Taskforce (FATF) የሚባል ግብረኃይል ኢንተርፖል አለው። … [Read more...] about የጃዋር ፋይናንስ በክትትል ራዳር ውስጥ – ዳያስፖራ ደጋፊዎች ስለ ነገ አያውቁም!
Archives for November 2019
ስብሃት ነጋ ስለ ደመቀ መኮንን፤ “ደመቀ የሸወደንን ያክል መሰሪው ጀበሃ (ሻእቢያ) እንኳን አልሸወደንም!”
የህወሓት ዘመን ማብቂያው አካባቢ ኃይለማርያም ደሳለኝ “ከሥልጣኔ ለቅቄአለሁ” ካለ በኋላ ለጠ/ሚ/ር ቦታ በተደረገው ሽኩቻ ዶ/ር ዐቢይ (የለማ ቡድን) አሸንፎ በወጣ ጊዜ የህወሓት ቡድን ወደ መቀሌ ሄዶ ሲመሽግ ስብሃት ነጋ በተፈጠረው ተናድዶ የሚከተለውን መናገሩ ታማጭ የመረጃ ምንጫችን አስታውቆናል። ስብሃት ነጋ በትግሪኛ የተናገረውና በአማርኛ ተተርጎመው የስብሃት ንግግር እንዲህ ይነበባል፤ “(ደመቀ) ለትህነግ ታማኝና ታዛዥ ነበር። ፈፅም! የተባለውን ነገር ለመፈፀም 'ለምን?' ብሎ እንኳን አያውቅም። አንድ ቀን ግን የሱዳን ግዛት የሆነውን አዋሳኝ መሬት ለመስጠት ‘ፈርም’ ሲባል ‘አይሆንም አልፈርምም!’ ብሎ አሻፈረኝ ሲል ያኔ ይህ ሰው አንድ ቀን እንደሚሸውደን እርግጠኛ ሁኜ ለጓዶቼ ነግሬያቸው ነበር። ሁሉም የእኔን እይታ ሳያቅማሙ ሲቀበሉኝ ጌታቸው (አሰፋ)ግን ‘አታስብ እሱ … [Read more...] about ስብሃት ነጋ ስለ ደመቀ መኮንን፤ “ደመቀ የሸወደንን ያክል መሰሪው ጀበሃ (ሻእቢያ) እንኳን አልሸወደንም!”
ህወሓት/ትህነግ በአጥር ላይ
ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት/ትህነግ) በማለት የሚጠራውና በኢትዮጵያ እጅግ አስከፊ የሚባልና ትውልድን ያወደመ ርዕዮት በመከተል አገር ያፈረሰው የተገንጣዮች ጥርቅም፤ አዲስ የተመሠረተውን ብልጽግና ፓርቲ አልቀላቀልም ብሎ ካፈነገጠ ወዲህ ሁኔታዎች መስመር እየለቀቁበት ነው። ላሁኑ አጥር ላይ መንጠልጠሉን አማራጭ አድርጓል። እስካሁን በዓለምአቀፍ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት በአሸባሪነት ተመዝግቦ የሚገኘው ትህነግ/ህወሓት መሪ የነበረው መለስ በሥልጣን በቆየበት ዘመን ሲዘልፋቸው የኖረውን ተቃዋሚዎች ባንድ ወቅት እንዲህ ብሏቸው ነበር፤ አጥር ላይ መሆንና አንድ እግር ከግቢ ውስጥ ሌላኛውን ከውጭ ማድረግ አይቻልም። በአሁኑ ወቅት ህወሓት ያለችበት ወቅታዊ ሁኔታ የመለስን አጽም ካላበት ቦታ እንዲላወስ ያደረገ ሆኗል። አንድ እግሯ መቀሌ፤ ሌላው እግሯ አዲስ አበባ … [Read more...] about ህወሓት/ትህነግ በአጥር ላይ
ህወሓት/ትህነግ ጊዜ እንዲሰጠው የሚጠይቅ “ስልታዊ” ውሳኔ አሳለፈ
"ሳይወሰንልኝ" አልሳተፍም አለ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ/ህወሓት በቀጥታ መቃወሚያ ሳያቀርብ የኢህአዴግ እህትና አጋር ድርጅቶች እንዲዋሃዱ በሚወሰንበት የግንባሩ ጉባዔ ላይ ለመገኘት ፈቃድ አለማግኘቱን አስታወቀ። ይህንኑ የሚጠበቅ ውሳኔ ይፋ ሲያደርግ በተዘዋዋሪ ቀን እንዲሰጠው መጠየቁንና አሁንም ተጨማሪ ጊዜ እንደሚፈልግ ማብራሪያ ያላቀረበበትን የህግና የፖለቲካ ጉዳይ አስታኳል። በህዳር 6 ቀን 2012 የግንባሩ ሥራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ላይ በውህደቱ አጀንዳ በድምጽ ተሸንፎ የወጣው ህወሃት የሶስት ቀን ተጨማሪ ጊዜ መጠየቁን ከስብሰባው ማግስት በኋላ ሲያስተባብል የቆየው ትህነግ፣ ዛሬ ባሰራጨው መግለጫ “የትህነግ ማእከላዊ ኮሚቴ በጥናቱ ላይ እንዲወያይ ተወስኖ እያለ ምንም ዓይነት ውይይት ሳይደረግ በጥድፊያ የምክር ቤት ስብሰባ ማድረግ ተገቢ … [Read more...] about ህወሓት/ትህነግ ጊዜ እንዲሰጠው የሚጠይቅ “ስልታዊ” ውሳኔ አሳለፈ
የተቃውሞ ሠልፍ “ሱስ”?!
ሠልፍ፣ ተቃውሞ፣ መፈክር፣ … ያለፉት 50ዓመታት መለያችን ሆኖ ቆይቷል። በተለይ ባለፉት 27ዓመታት ዘመነ ፍዳ ወወያኔ ደግሞ በተለይ በአውሮጳና አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን “ሼም ኦን ዩ …” ሳይሉ የሚያልፍ ወር አልነበረም ቢባል ማጋነን አይሆንም። ለዚህም ይመስላል “አሜሪካ አገር ኋይት ሃውስ ደጃፍ ቆመህ “ኦባማ ይውረድ” ስትል ብትውል ማንም የሚነካህ የለም ሲባል የሰማው ክበበው ገዳ “እኛስ ሃገር ቢሆን አራት ኪሎ ቤተመንግሥት በር ላይ ቆመህ “ኦባማ ይውረድ!” እያልክ ብትጮህ ማን ይነካሃል?” በማለት የቀለደው። ይህ “ማንም አይነካኝም” የሚለው አስተሳሰብ ሊሆን ይችላል በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያውያን የሰልፍ ሱሰኛ እስኪመስሉ ድረስ ለሁሉም ችግር ሰልፍን ብቸኛ አማራጭ ሲያደርጉ የሚታዩት። ያለፉት 27ዓመታት የተወጣው ሰልፍ ውጤት አላመጣም ለማለት አይቻልም። የተወጡም ሰልፎች … [Read more...] about የተቃውሞ ሠልፍ “ሱስ”?!
በአማራና ትግራይ ህዝብ መካካል አብሮነቱ እንዲጠናከር የሁለቱ ክልሎች ፖለቲከኞች ተቀራርበው ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለጸ
በአማራና በትግራይ ክልል ህዝቦች መካካል ለዘመናት የዘለቀው የአብሮነት እሴት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሁለቱ ክልሎች መንግሥታትና ፖለቲከኞች ልብ ለልብ ተቀራርበው ሊሰሩ ይገባል ሲሉ በጎንደር ከተማ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ተናገሩ። የጎንደር ከተማ አስተዳደር በከተማው ከሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ጋር በወቅታዊ፣ ክልላዊና ሀገራዊ ሁኔታ ላይ ያዘጋጀው የምክክር መድረክ ዛሬ ተካሂዷል። በምክክር መድረኩ ላይ ተሳታፊ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች እንደተናገሩት መንግስትና የፖለቲካ ስርአት አላፊ ሲሆኑ፤ ህዝብና አገር ግን የሚቀጥሉና የታሪክ ባለቤት ናቸው። “ጎንደር ያደኩባት፣ የሸመገልኩባት፣ ልጅ ወልጄና አሳድጌ ለወግ ማዕረግ የበቃሁባት ህዝቡም በፍቅር ያኖረኝ ከተማ ነች” ያሉት አቶ ወልደገብርኤል ተክኤ የተባሉ ነዋሪ ናቸው። “በኖርኩባቸው 40 ዓመታት በከተማው አማራ እና ትግሬ … [Read more...] about በአማራና ትግራይ ህዝብ መካካል አብሮነቱ እንዲጠናከር የሁለቱ ክልሎች ፖለቲከኞች ተቀራርበው ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለጸ
ህወሓት እንቅጩን ተናገረ!!
ሦስቱ ፓርቲዎችና አጋር ድርጅቶች አቋማቸውን ግልጽ አድርገዋል ህወሃት “በሁሉም መለኪያዎች አንድ ፓርቲ ለመሆን የሚያስችል መነሻና ምክንያት በሌለበት ኢህአዴግን አፍርሶ ሌላ ፓርቲ ለማቋቋም ማሰብ አገርን የሚበትን ተግባር ነው” ሲል ጉዳዩ የሞት ሽረት መሆኑንን አስታውቋል። አሁን ግጭት እየተባባሰ የሄደውም በዚሁ ምክንያት ነው ሲል አክሏል። እስከ ዛሬ ከውህደት ተገለው የነበሩ አጋር ድርጅቶች በኢህአዴግ ሥር ተጠቃለው እንዲቀጥሉ ምኞቱን ያኖረው ህወሃት፤ አጋር ፓርቲዎች ስለምን ተገለው እንደቆዩ ቁጭቱንም ሆነ ምክንያቱን በመግለጫው አላካተተም። ሰሞኑንን አጋር ፓርቲዎች ሙሉ በሙሉ፣ ሶስቱ እህት ድርጅቶች ውህደቱን እንደሚደግፉና እንደሚቀላቀሉ ይፋ ማድረጋቸውን በድጋፍም ሆነ በነቀፌታ ያላስቀመጠው የህወሃት መግለጫ “ውህደቱ አገር ያፈራርሳል፣ ፍፁም ፀረ-ዴሞክራሲያዊ” ከማለት … [Read more...] about ህወሓት እንቅጩን ተናገረ!!
የዶ/ር አሚር የ“በቃኝ” ጥያቄ፤ የ“ዘይት አስገባልኝ” ጥያቄ!!
አማራ ክልል የሚሸጥ የምግ ዘይት አነጋጋሪ እየሆነ ነው የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማን የሥራ መልቀቂያ ማስገባታቸውን ተከትሎ የተለያዩ መላምቶች ሲሰነዘሩ ቆይተዋል። መንግሥትም ሆነ የሚመሩት ተቋም፣ እንዲሁም ራሳቸው በግልጽ ማስተባበያም ሆነ ማረጋገጫ አልሰጡም። ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ ባደረገው ማጣራት የዶ/ር አሚር መልቀቂያ ማቅረብ ትክክል መሆኑንን ለማወቅ ችሏል። በዚሁ መሠረት ሚኒስትሩ “በቃኝ” ማለታቸው በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች ሲባል እንደከረመው ከአዴፓ ጋር በተያያዘ ሳይሆን የመገልገያ ጊዜው (expiry date) ሊጠናቀቅ ቀናት የቀሩት የምግብ ዘይት አገር ቤት ለማስገባት ከአንድ ባለሃብት የቀረበላቸውን ማመልከቻ ውድቅ በማድረጋቸው ነው። የጎልጉል የአዲስ አበባ ዜና አቀባይ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑትን የመረጃ አጋሮቹን ጠይቆ ሪፖርት እንዳደረገው ከውጭ … [Read more...] about የዶ/ር አሚር የ“በቃኝ” ጥያቄ፤ የ“ዘይት አስገባልኝ” ጥያቄ!!
ሰላምን ከጦርነት፣ መፍረስን ካለመፍረስ የሚለይ ቀይ መስመር የለም!
በድሉ ዋቅጅራ (ዶ/ር) “እንደቀልድ፣ ሳናውቀው አገራችን ወደ ፍርስራሽነት ተቀየረች” አለ፣ አንድ ታዋቂ የየመን ጋዜጠኛ፤ በአንድ ቃለመጠይቁ ላይ። ነገሮች የረዥም፣ ተከታታይ ሂደት ውጤት ወይም መጨረሻ ናቸው፤ የድንገቴ ክስተት አይደሉም። ጦርነት ያለመግባባትና የቅራኔ ሂደት ውጤት ነው። ሞት ከጤንነት ጀምሮ፣ እየጠነከረ የሚሄድ ህመም ሒደት ውጤት ነው። በሥርዓትና ደንብ የቆመ ሀገር መፍረስም እንዲሁ የረዥም ጊዜ፣ ተከታታይ ከሥርዓትና ደንብ ማፈንገጥ ሒደት ውጤት ነው። የሀገር መሪዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ፖለቲከኞች . . . ሁላችንም፣ “ኢትዮጵያ አትፈርስም” እያልን እንጮሀለን። ከጩኸቱ ጀርባ የቻሉትን እያደረጉ ያሉት ግን የሀይማኖት አባቶች ብቻ ናቸው፤ ዕንባቸውን ሽቅብ ወደ ፈጣሪ መንበር እየረጩ የመንፈስ ልጆቻቸውን ይለምናሉ፤ ምእመኑን በጸሎትና በጾም ያተጋሉ። ፖለቲከኞች … [Read more...] about ሰላምን ከጦርነት፣ መፍረስን ካለመፍረስ የሚለይ ቀይ መስመር የለም!
ሐሜትን በዜናነት ሲዘግብ የኖረው የሐሰት ዜና በመፈብረክ ተጠምዷል
“የሚዲያው” ባለቤት በሼራተን የቪአይፒ ተስተናጋጅ ሆኗል የ“ሹክሹክታ” (ጎሲፕ ወይም ሐሜት) አምራች በመሆኑ ትልቅ ዋጋ የተሰጠውና በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የዓመቱን ሽልማት የለገሰው ዘ-ሐበሻ ትላንት “በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሁለት ተማሪዎች ሞቱ” ሲል ያሰራጨው ዜና ፍጹም ሃሰት መሆኑንን ዩኒቨርሲቲው ባሰራጨው የማስተባበያ ዜና ይፋ አደረገ። የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት የዚሁ “ሚዲያ” ባለቤት ነው የሚባለው ሔኖክ ዓለማየሁ በሸራተን አዲስ በልዩ የዕንግዳ መስተናገጃ /ቪአይፒ/ ሲስተናገድ እንደሰነበተ አስታውቀዋል። “ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በተነሳ ብጥብጥ ምክንያት ሁለት ተማሪዎች በህክምና ሲረዱ ቆይተው ህይወታቸው ማለፉን ሰምተናል” በማለት ዘ-ሐበሻ የሐሰሰት ዜናውን ሲረጭ በስምንት ሰዓታት ውስጥ 556 ሰዎች ስሜታቸውን የገለጹ፣ … [Read more...] about ሐሜትን በዜናነት ሲዘግብ የኖረው የሐሰት ዜና በመፈብረክ ተጠምዷል