
አማራ ክልል የሚሸጥ የምግ ዘይት አነጋጋሪ እየሆነ ነው
የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማን የሥራ መልቀቂያ ማስገባታቸውን ተከትሎ የተለያዩ መላምቶች ሲሰነዘሩ ቆይተዋል። መንግሥትም ሆነ የሚመሩት ተቋም፣ እንዲሁም ራሳቸው በግልጽ ማስተባበያም ሆነ ማረጋገጫ አልሰጡም። ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ ባደረገው ማጣራት የዶ/ር አሚር መልቀቂያ ማቅረብ ትክክል መሆኑንን ለማወቅ ችሏል። በዚሁ መሠረት ሚኒስትሩ “በቃኝ” ማለታቸው በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች ሲባል እንደከረመው ከአዴፓ ጋር በተያያዘ ሳይሆን የመገልገያ ጊዜው (expiry date) ሊጠናቀቅ ቀናት የቀሩት የምግብ ዘይት አገር ቤት ለማስገባት ከአንድ ባለሃብት የቀረበላቸውን ማመልከቻ ውድቅ በማድረጋቸው ነው።
የጎልጉል የአዲስ አበባ ዜና አቀባይ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑትን የመረጃ አጋሮቹን ጠይቆ ሪፖርት እንዳደረገው ከውጭ በርካሽ ግዢ ወደ አገር ቤት እንዲገባ ጥያቄ ያቀረቡት አማራ ክልል የሚገኙና በዘይት ንግድ ከፍተኛ ሃብት እንዳሰባሰቡ የሚነገርላቸው ባለሃብት ናቸው። ዶክተር አሚን “ይህ አይሆንም፤ አልፈርምም” በማለት ውሳኔ ከሰጡ በኋላ ባለሃብቱ በአንድ ከፍተኛ የፌዴራል የበላይ ባለሥልጣን ትዕዛዝና ፍቃድ የተከለከሉት ዘይት እንዲገባላቸው በመደረጉ ዶ/ር አሚር የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው ታውቋል።
የሥራ መልቀቂያው የቀረበላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ ዶ/ር አሚር በሥራ ላይ እንዲቆዩ አነጋግረው እንዳሳመኗቸውና ሥልጣናቸውን ተጠቅመው መመሪያ በመስጠት ዘይቱ ወደ አገር ቤት እንዲገባ ያዘዙትን ከፍተኛ የአዴፓና የፌዴራሉ መንግሥት አመራር እየገመገሙ እንደሆነ የደረሰን ዜና ያስረዳል።
ከተለያዩ አካላት እንደሚሰማው የመገልገያ ጊዜያቸው ሊጠናቀቅ የተቃረበ ምርቶችን ወደ አገር ቤት ማስገባት በተለይ ህወሓት ሲገዛት በነበረቸው ኢትዮጵያ የተለመደ ነው። ለጊዜው ስም መጥቀስ ባያስፈልግም አንዳንድ የታሸጉ ምግቦችን የሚያስገቡ ድርጅቶችና ባለሃብቶች ግዢ ከፈጸሙ በኋላ ዕቃውን በመጋዘናቸው በማድረግ የአግልግሎት ጊዜውን እየቀየሩና እያራዘሙ በአዲስ ዕሽግ ለገበያ በማቅረብ የግፍ ሃብት እንዳከማቹ ይታወቃል። ዕሽጉን መቀየር የማያይመች ሲሆን ደግሞ ዕቃው ከተገዛበት አገር ከሚገኘው ሻጭ በድርድር የአገልግሎት ዘመን የማራዘም ሥራ በስምምነት ያከናውናሉ። ሥራውንም የሚያከናውኑት በቤተሰብና በቅርብ ሰዎች እንደሆነ ጥቆማ አለ።
ባለሃብቱ በከፍተኛ ባለሥልጣን ፈቃድና ትዕዛዝ አስገቡት የተባለው ዘይት በአማራ ክልል በብዛት እየተሸጠ መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን የዕሽግ ለውጥ ይደረግበት ወይም ቀኑ ብቻ ተቀይሮ እንዳለ ለገበያ ይዋል የዜናው ባለቤት ማጣራት አልቻለም። የዘይት አስመጪነት ሥራ በተወሰኑ ባለሃብቶች በትሥሥር ተይዞ ጥቂቶችን ያበለጸገ ንግድ በመሆኑ ዘወትር ከውዝግብ የጸዳ የንግድ መስክ እንዳልሆነ የሚታወቅ ነው። በቅርቡ ዘይት ማስገባት እንዳልችል ተደረኩ በሚል ከፍተኛ ውዝግብ መነሳቱ የሚታወስም ነው።
ይህ ዜና እስከታተመበት ድረስ ዶ/ር አሚር ውሳኔያቸውን ስለመቀየራቸው በይፋ ማረጋገጫ አላቀረቡም። የባህር ዳር ተወላጅ የሆኑት የዶ/ር አሚር ኃላፊነታቸው ተጥሶ ወደ አገር ቤት የገባውን ዘይት አስመልክቶ ዝምታቸውን ሳይሰብሩ ሕዝብ ከመጎዳቱ በፊት አስተዳደራዊ ርምጃ እንዲወሰድ ጥረታቸውን ሊቀጥሉ እንደሚገባ የዜናው ጠቋሚዎች አሳስበዋል።
በመጨረሻ በተገኘ ዜና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዘይቱ ሙሉ በሙሉ እንዳይገባና ውሳኔ ማሳለፋቸው፣ በገባውም ዘይት ላይ ክትትል እንዲደረግ ለዶ/ር አሚር ኃላፊነታቸውን እንዲጠቀሙ አንዳሳሰቧቸው ተሰምቷል።

በሌላ ዜና ዶ/ር አሚር አማን በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ባሳዩት የአመራር ብቃት ተሸላሚ መሆናቸው ታውቋል። ዶ/ር አሚር የተሸለሙት በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ባሳዩት የአመራር ብቃት ነው፣ በዓለምአቀፍ የልማት አጋሮች ተሸላሚ የሆኑት በአመራር ላሳዩት ትጋት እና ወደ እውነት በቀረበ የጤና መረጃ አሰባሰብ ሥራቸውና በጤናው ዘርፍ ላይ ያለውን ክፍተት ለመሙላት ከፍተኛ ተግባር በማከናውናቸው ነው።
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።
ዶ/ር ኣሚር ከጤና ጥበቃ ምንስትር ለመነሳት ያቀረቡት ጥያቄ የኢትዮጵያን ሕዝብ አደጋ ላይ የሚከተው በመሆኑ እኝህ በለስልጣን በስራቸው መቀጠል ለሕዝባችን ጤና መፍትሔ ነው። የአገሪቱ የማፊያ ድርጅቶች መልካም ስራ የሚሚሰሩትን በለስልጣን ማሸማቀቅ ለ27 አመት ያካበቱት የወንጀል ዘዴ ነውና የአገሪቱ ጠቅላይ ምንስትር የማፊያ ድርጅት የውስጥ አርበኞችን መመንጠርና ለፍርድ ማቅረብ ተገቢ ነው። በኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ዶ/ር ኣሚር መልካምና በሙያቸው ብቃት ያላቸው ታታሪ የስራ ሰውና በጥቅም የማይሸነፉ ጠንካራ መሪ ናቸውና ሌቦቹኑና ፀረ ጤና ምርት የሚሸጡና የሚያስመጡ ወንጀሎች ሊቀጡና በውጭም ይህንን ወንጀል የሚያደርጉ የውጭ ድርጅቶችም በWHO ምርመራ ሊደረግባቸው ይገባል። ዶ/ር የኢትዮጵያን ሕዝብ በሐቅ ለማገልገል የተነሱ ጠንካራ ወጣት መሪ ናቸውና ኣስፈላጊውን እንክብካቤና ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል። የሳቸው መልቀቅ ኢትዮጵያኖችን ለበሽታና ለችግር ማጋለጥ እንዳይሆን እፈራለሁ። መልካምና ጥሩ መሪዎችን መደገፍ ይቀጥል።
“በሌላ ዜና ዶ/ር አሚር አማን በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ባሳዩት የአመራር ብቃት ተሸላሚ መሆናቸው ታውቋል። ዶ/ር አሚር የተሸለሙት በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ባሳዩት የአመራር ብቃት ነው፣ በዓለምአቀፍ የልማት አጋሮች ተሸላሚ የሆኑት በአመራር ላሳዩት ትጋት እና ወደ እውነት በቀረበ የጤና መረጃ አሰባሰብ ሥራቸውና በጤናው ዘርፍ ላይ ያለውን ክፍተት ለመሙላት ከፍተኛ ተግባር በማከናውናቸው ነው”
Excuse me but who gave the prize to Dr. Amin? And your whole writing is, let us say, in favour of or biased towards Amin. When you ‘insert’ your opinion then . . .
ስምህን እየቀያየርህ እኛን መዝለፍ ሥራህ ያደረግኸው ግለሰብ …
በቅድሚያ ሃሳብህን በእንግሊዝኛ የመግለጽ ብቃትህ በጣም የወረደ ነው። ያገርህን ቋንቋ ብትጠቀም የበለጠ እንግባባለን። ለማንኛውም ጽሁፉ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው “በሌላ ዜና ዶ/ር አሚር አማን በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ባሳዩት የአመራር ብቃት ተሸላሚ መሆናቸው ታውቋል። ዶ/ር አሚር የተሸለሙት በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ባሳዩት የአመራር ብቃት ነው፣ በዓለምአቀፍ የልማት አጋሮች ተሸላሚ የሆኑት በአመራር ላሳዩት ትጋት እና ወደ እውነት በቀረበ የጤና መረጃ አሰባሰብ ሥራቸውና በጤናው ዘርፍ ላይ ያለውን ክፍተት ለመሙላት ከፍተኛ ተግባር በማከናውናቸው ነው።”
ማንበብና መረዳት ብቻ ሳይሆን ማየትም አትፈልግም እንጂ የሽልማቱን ፎቶ ጎላ አድርገህ ብታየው በግልጽ ሸላሚው ይታያል።
ተመለሰልህ?
የጎልጉል አርታኢ
ዶ/ር አሚር በመጀመሪያ የተሰጣቸውን ሃላፊነት መወጣት ብቻ አይደለም መስዕዋትም ለመቀበል ዝግጁ እንደነበሩ ያመለክታል።ምክንያቱም ጭንቅላታቸዉ በብር የተገነዙ ባለሀብቶች በገንዘባቸዉ ህዝብን በሽተኛ ከማደረጋቸዉም በተጨማሪ እንደ ዶክተሩ የሚሞግታቸዉን ከራሩም ያሳስራሉ ምሳሌ መላኩ ፈንታ ካራሩም ያስገድላሉ። ዶ/ር አሚር መልቀቂያ ማስገባቱም ትክክል ነበር ምክንያቱም በማይመለከታቸዉ ገብተዉ ስራ የሚያበላሹ ብዙ አሉና። በችሎታዉ የማይሰራ ከሆነ መብቱን ተጠቅሞ መልቀቅ ለህሌናዉ እረፍት ይሰጠዋል። ዶ/ር ዓብይ ማግባባታቸዉና እንዲቆይ ማድረጋቸዉ ትክክልና ትክክል ነዉ። ግን ስራ ያደናቀፈዉን ባለስልጠን ቆነረጠጥ ማድረግ ደግሞ አስተማሪ ይሂናል።
Golgul editor (or so you say)
You still suffer from the old complex – your comment on my english from the times where “knowing” english is in itself a mark of expertise. Sadly. u still suffer from this syndrome.
First of all Amin is an eprdf cadre belonging to the sell out party of Amhara who served as a pimp in the past 27 years of woyane rule. You can’t pick and choose from such party – I have the same disdain for Amir as I have for Demeqe, Addisu, Tadesse – the whol lot. They are no better than tplf or oromooma political pimps under meles and idiotic hailemarim. So for you so called editor to praise a woyane cadre who is barely 40 years old masquarading as a minister shows you are no better than him.
As for prize even meles was given many and for praise – he was admired by stupid ferenjis as well. So don’t waste your time on that. If you really want to be an ‘editor’ find out how AMir and the whole cabinet is ‘appointed’ and what the criteria was. You find your answers there instead of angry replies. What is the problem if people different names? Your system allows it and more importatnly why does it bother you – it should be the contents that you should focus. Havin haign opinions of one of your own ‘editorial’ ability is not uncommon in the ethio cyber world and in the media – just like you all seem to be experts, analysts, editors, show hosts – so the public sees you as another egoistic ‘editor’. No, you havent answered my question.
Dearest dictatorial editor!
The hitlerites of cyberspace want to hear only what they want – and you repeatedly proved you are ahead of the rest, first among equals. Self appointed gate keepers have neither shame nor elementary scruples while they call them selves “editors” and vigorously go about the censorship “duties”. When they can’t defend their biased opinions put across as news or facts, when they don’t have the ability to defend their “editorial” farce they just delete comments and pretend they never saw them. Easy that way than man up to the challenging views of readers. Sad. Even living in the west none it rubbed off on such die hard “editors” from bygone times.
Speak your mind? How can we with the “editor” himself as censor. It is a sad joke. Democracy in ethiopia – just look at your actions, it speaks volumes why it would take us many, many decades to achieve it at this rate. Don’t even bother with a trashy reply – your excellency “editor” of golgule. When are you getting off your high “editorial” horse and leave comment be?
“Your comment is awaiting moderation” – moderation, as in delete if you don’t like it?
እንዲህ ትላላችሁ
ስለ እኛ!
ህዝብ “የነጻ” ሚዲያ ረሃብ አለበት፡፡ ፖለቲከኞችም ከድጋፍና ከሙገሳ ባለፈ መልኩ ግልጽ የሕዝብ ትችትና የባለሙያ አስተያየት ያስፈልጋቸዋል፡፡ በሁሉም አቅጣጫ ግን ክፍተት አለ – ይህ ክፍተት ደግሞ የመረጃ አፈና በሚካሄድባት ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ነጻነት አለበት በሚባልበት የውጪው ዓለምም በተደጋጋሚ ሲከሰት ይስተዋላል፡፡ ይህንን ክፍተት መሙላት ባይቻልም የበኩላችንን ማበርከት እንዳለብን በማመናችን በተለያዩ አገራት የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ለመመስረት ወሰንን፡፡
ወቸ ጉድ – ከመልካም ቃላት ጀርባ መደበቅ ማለት ይቺ ናት፡ እናንተ (ብዙ ከሆናችሁ) የሚደርስባችሁን ትችታ አስተያየትን ተከታትላችሁ እይደለዛችሁ ሌሎችን ትችት እንዲቀበሉ ታሳስባላችሁ? አርታኢው እየተከታታለ በመደለዝ ሥራ ተጠምዷል፤ ከቶ እኛን ማን ተችቶን የሚል አስተሳሰብ ስላወራችሁ ደጋግሞ ከማሳበድ ሌላ አማራጭ የለም፤ እናንት “በተለያዩ አገራት የምትገኙ ባላሙያዎች” ሆይ ለዚህ አምባገነናዊ ሥራ ነው የተሰባስባችሁትን?