Memorandum of Understanding (MoU) Oromo Democratic Front (ODF) and Patriotic Ginbot 7 (PG7) August 11, 2016 After several candid discussions and careful considerations of the current political, social, economic and humanitarian situations in Ethiopia, and all the damages caused by successive regimes and the TPLF/EPRDF regime in particular on the welfare and national interests of the peoples of Ethiopia and the security and sovereignty of our country, the ODF and PG7 have made important … [Read more...] about A Breakthrough agreement between ODF and Patriotic G7
Archives for August 2016
ከትህወሓት/ኢህአዴግ ከስልጣን ይውረድ የሽግግር መንግስት ይቋቋም
በአጠቃላይ ለ25 ዓመታት ሙሉ ህዝባችንን አፍኖ ሲገዛ የቆየና፣ ለ40 ዓመታት ሰላማዊ ዜጎችን እየረሸኑ አገራችንን እየዘረፉ የቆዩ ባለስልጣኖች ያሉበት ህወሓት/አህአዴግ በተለይ በዚህ ዓመት በኦሮሞና በአማራ ህዝባችን ላይ ጦርነት ከፍቷል። የአገዛዙን የግድያ ወንጀሎች እናወግዛለን፤ የህዝቡን ተቃውሞ እንደግፋለን። ስለዚህ በአገራችን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲገነባ፣ የህዝባችን አንድነት እንዲጠናከርና የአገራችን ሉኣላዊነት እንዲከበር᎓- 1. ህወሓት/ኢህአዴግ ከስልጣን መወገድ አለበት 2. በኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሲቪክ ማህበሮችና ብቃት ባላቸው ግለሰቦች የሽግግር መንግስት መቋቋም አለበት። ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን ዓላማዎች ለማሳካት የሚከተለውን ጥሪ እያቀረብን ፣ እኛም ከህዝባችን ጐን ተሰልፈን ለትግሉ መሳካት የአቅማችንን እንደምናበረክት ቃል እንገባለን። 1. ሁሉም … [Read more...] about ከትህወሓት/ኢህአዴግ ከስልጣን ይውረድ የሽግግር መንግስት ይቋቋም
ከኢሕብፓ በሃገራችን ወቅታዊ ሁኔታ የተሰጠ መግለጫ
የዘረኛውን ወያኔ አምባገነን የግፍ አገዛዝ ለማስወገድ ጀግናውና ሀገር ወዳድ ወገኖቻችን ለሃገራችሁ የምታደርጉት ታሪካዊ ተጋድሎና በጀግንነት የምትከፍሉት የህይወት መስዋትነት ሁሉንም ወገን የሚያኮራ ተግባር ነው። እኛ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሔራዊ ፓርቲ (ኢሕብፓ) አባሎች ከጎናችሁ ተሰልፈን የትግሉ አጋር ለመሆን አስፈላጊውን ትብብር: አስተዋጽዎና መስዋትነት ለመክፈል ቆርጠን ተነስተናል፡፡ (የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ከኢሕብፓ በሃገራችን ወቅታዊ ሁኔታ የተሰጠ መግለጫ
“ትውልድ አምጿል!”
“ሕዝቡን ካፈንከው እና ከመቃወም ሌላ አማራጭ ካሳጣኸው ይፈነዳል፤ ወጣቱ በሙሉ ዓመጽ ላይ ነው፤ ትውልድ አምጿል”፡፡ “(ትግሉን) በአንድ ጥላ ሥር እያስተባበርን ነው”፡፡ የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጠኛ JEFFREY GETTLEMAN በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ በተነተነበት ጽሁፍ ላይ የጠቀሳቸው ሁለት ግለሰቦች የተናገሩት ነበር ከላይ የሰፈረው፡፡ ጋዜጠኛው ዘገባውን ሲጀምር “ኢትዮጵያ እየተሰነጣጠቀች ነውን” በማለት ይጠይቅና በሁሉም አቅጣጫ ያለውን አመለካከት ያሰፍራል፡፡ (ከዜና ዘገባው ጋር Violent Protests in Ethiopia በሚል ርዕስ የጸጥታ ኃይሎች ሰላማዊ ሰልፍ በወጣ ህዝብ ላይ የሚፈጽሙትን አሰቃቂ ግፍ እና ጨካኝ ድብደባ እዚህ ላይ መመልከቱ የግድ ይላል)፡፡ “ልማት” አካሂዳለሁ የሚለው ህወሃት/ኢህአዴግ የሕዝብን መሠረታዊ ጥያቄዎች አለመመለሱን የሚያትተው ዘገባ … [Read more...] about “ትውልድ አምጿል!”
ጀግና ውለጅ እባክሽ !
የምሁር መሃይም - ተባይ አላዋቂ፤ የመሃይም ኩፍስ - አስመሳይ አዋቂ፤ የጅብ ባለ ጊዜ - ታፋ መራጭ ከሽንጥ፤ ያንበሳ ልክስክስ - ልፋጭ የሚያላምጥ የቁራ ዕርግብ መሳይ - ሠላምን አብሳሪ፤ የፈረስ አዝጋሚ - የግመል ሰጋሪ፤ ንጹህ ሰው ታሳሪ - በፈጠራ ወንጀል፤ ፍርደ ገምድል ዳኛ - ፈራጅ በቂም በቀል፤ የባዕድ ባለቤት - የነባር ባይተዋር፤ ሥልጡን ሥራ ፈቶ - ሞያ ቢስ ሲገብር፤ ልማድ ሆኖ ቀረ - አቀርቅሮ መኖር፤ በተወሇድንባት በጦብያ ምድር :: (ሙሉውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ጀግና ውለጅ እባክሽ !
ወልቃይት የማን ነው? የማይረባ ጥያቄ!
አንድ በነገረ አስተሳሰብ ወይም በአስተሳሰብ ሕግ (ሎጂክ) ትምህርት ላይ አንድ የማስታውሰው ምሳሌ አለ፤ ‹‹ሚስትህን መደብደብ ትተሃል ወይ?›› የሚል ጥያቄ ነው፤ ጥያቄው የሚነሣው ጠያቂው አውቃለሁ ብሎ ከያዘው እውቀት ወይም እምነት ነው፤ ስለዚህም ጠያቂው የሚፈልገው ጥያቄ ለማስተላለፍና መልስ ለማግኘት አይደለም፤ ጠያቂው የሚፈልገው በጥያቄ መልክ የራሱን ‹‹እውቀት›› ወይም እምነት ለተጠያቂው ለማስተላለፍና ተጠያቂውን የጠያቂው ደቀ መዝሙር ለማድረግ ነው፡፡ ሚስትህን መደብደብ ትተሃል ወይ? መልስ የሌለው ጥያቄ ነው፤ ‹‹አዎ›› የሚል መልስ ሰውዬው ሚስቱን ሲደበድብ እንደነበረ አመነ ማለት ነው፤ ‹‹አልተውሁም›› ከአለ በራሱ ላይ መሰከረ፤ ሁለቱም መልሶች ተጠያቂውን የሚያስወነጅሉ ስለሆኑ መልስ አይደሉም፤ ከዚያም በላይ ጥያቄው ትክክል አይደለም፤ የማይረባ መጥፎ ጥያቄ … [Read more...] about ወልቃይት የማን ነው? የማይረባ ጥያቄ!
ቅኝ ተገዥነቱን ያወቀ ሕዝብ በከፊል ነፃ ነው!
የኢትዮጵያ ሕዝብ በትግሬ ወያኔ ቅኝ ተገዥ ከሆነ ድፍን 25 ዓመት ሆነው። በእነዚህ ረጅም ዓመታት፣ የተማሩትም ሆነ ያልተማሩት ዜጎች፣ በቅኝ ተገዥነት መያዛቸውን ያወቁትም ሆነ ለማወቅ የጣሩት በጣም ጥቂቶች ናቸው። እነዚህ በቅኝ ተገዥነት ተይዘናል ያሉት የጥቂቶቹ ድምፅ፣ በብዙኃኑ፣ ከሁሉም በላይ በጎሣ ፖለቲከኞቹ ድምፅ ተውጦ፣ ወያኔ፣ ያላንዳች ሀግ ባይ፣ ሩብ ምዕተ ዓመታት የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅምና ሉዓላዊነት በእጅጉ የጎዱ ሥራዎችን እንዲሠራ ሠፊ ዕድል ሰጠው። በመሆኑም የኢትዮጵያዊነት አያያዥ ማገርና ወራጅ፣ መሠረትና ጭምጭም የነበሩትን፣ የኢትዮጵያዊነት ዕሴቶቻችን ከሥራቸው ነቀላቸው። ሕዝቡን በነገድ ከፋፍሎ እሣትና ጭድ አደረጋቸው። የኢትዮጵያ ነገዶች ሙጫ በመሆን ከሌሎች ነገዶችና ጎሣዎች ጋር ሰምና ፈትል ሆኖ፣ ኢትዮጵያዊነትን ሲገነባ የኖረውን የዐማራ ነገድ፣ በዘር ጠላትነት … [Read more...] about ቅኝ ተገዥነቱን ያወቀ ሕዝብ በከፊል ነፃ ነው!
“ለባስልጣናት ለሚታዘዝ ፍ/ቤት (ቃላችንን) አንሰጥም” እነ በቀለ ገርባ
የኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረስ ከፍተኛ አመራር አባላት አቶ ጉርሜሳ አያኖ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ አቶ አዲሱ ቡላላ እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 22 ተከሳሾች ዛሬ ልደታ ምድብ ፍርድ ቤት ቀርበው የሰጡት የእምነት ክህደት ቃል ከዚህ የሚከተለው ነው። ጉርሜሳ አያኖ፤ “ክሱ ግልፅ አልሆነልኝም እኔ ፖለቲከኛ ስሆን የመድረክ ፓርቲ-አባል ነኝ፡፡ የእኛ ፓርቲ ህገመንግስቱን ተከትሎ የተቋቋመ ህጋዊ ፓርቲ ነው፡፡ የተከሰስኩት ግን የኦነግ አባል ነህ በሚል ነው፣ እኔ እስከማውቀው አንድ ሰው የሁለት ድርጅት አባል መሆን አይችልም፡፡ ይሄ ክስ መንግስት መሬቴን አሳልፌ አልሰጥም ያለዉን የኦሮሞን ህዝብ በጅምላ አሸባሪ ብሎ እየከሰሰ ነዉ ያለው ስለዚህ ቃሌን ለዚህ ፍ/ቤት አልሰጥም፡፡” ደጀኔ ጣፋ፤ “የኢትዮጵያ ፍ/ቤት በግልፅ ህገመንግስቱን እያፈረሰ ያለ ተቋም ስለሆነ ለዚህ ፍ/ቤት ቃሌን አልሰጥም፣ … [Read more...] about “ለባስልጣናት ለሚታዘዝ ፍ/ቤት (ቃላችንን) አንሰጥም” እነ በቀለ ገርባ
ይድረስ ለእኛ—ከእኛ!
ይድረስ ለእኛ-ከእኛ! - ከላይ ልጀምር ካ’ናቱ፣ በብረት ኃይል ተከቦ - ከተኮፈሰው በከንቱ፣ ይድረስልኝማ ለወያኔ - ለጊዜያዊው ባለጉልበቱ፤ … “ለሕዝባዊነት መጣሁ” ብሎ - ሕዝብን በጥይት መቁላት የለምና፣ አቆልቁለህ እየውማ - የምትሄድበትን ጎዳና! የጭካኔ መጠንህ ጫፍ ደረሰ - የውሸት ቋትህ ሞላ፣ የ’እውቀት‘ ገደብህ አበቃ - ከእንግዲህ ላይኖርህ የቀረ ‘መላ’፣ ከወደቁ ወዲያ መንፈራገጥ.. እንዳይሆን ለመላላጥ፣ ሳሩንም ላለመጋጥ.. መሬቱንም ላለመናጥ…፣ ከአውሬነት ባህል ተላቆ - ሰውነትን ይሻልና፣ ይድረስ! ይድረስ! እልሃለሁ፤ ይድረስ! እንደገና፤ ዛሬ እንኳን እንደማመጥ - ይቅርብህማ ወንድሜ፣ በግፍ ተሞልተህ ጉዞ - ላይሆንህ መልካም ዕድሜ፣ “አበቅቴ ውሉን ሳይስት” - የአመሻሽ ጀንበር ሳትጠልቅብህ፣ ቆም ብለህ ማሰብ ጀምር - እንደ “ጆቤ”ህ፣ እንደ … [Read more...] about ይድረስ ለእኛ—ከእኛ!
“ጸጥታ አስከባሪው” ህወሃት/ኢህአዴግ ጸጥታው ሊገመገም ነው
ከዚህ በፊት ሆኖ የማያውቅ በሚመስል ሁኔታ ኢትዮጵያ በህወሃት/ኢህአዴግ ዘመን ዓለምአቀፋዊ ዕውቅና ያገኘች አስመስሎ የሚያወራው ህወሃት “ጸጥታ አስከባሪ ነኝ” እያለ በአፍሪካ ሳይጠሩት አለሁ የሚለውን ያህል አሁን ደግሞ በተራው በአገር ውስጥ ህዝብን ጸጥታ በመንሳት ሊገመገም መሆኑ ተነገረ፡፡ “በኢትዮጵያ ሰላም ለማስከበር በሚል የህወሃት ጄኔራሎች የተባበሩት መንግሥታትን ምደባ እየጠየቁ ነው” በማለት አስተያየት ሰጪዎች ተሳልቀዋል፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ምክርቤት ድምጽ የማትሰጥ አባል ሆና መመረጧ የህዳሴው ውጤት ነው፤ የመለስ ራዕይ ተግባራዊነት ነው፤ … በማለት ከፍተኛ ዲስኩር የነፋው፤ ከበሮ የደለቀው ህወሃት “ህዝብን ጸጥታ ነስተሃል” ተብሎ በተባበሩት መንግሥታት የምርመራ ግዴታ ተጥሎበታል፡፡ በንጉሡ ዘመን እንዲሁም በደርግ ጊዜ የጸጥታው … [Read more...] about “ጸጥታ አስከባሪው” ህወሃት/ኢህአዴግ ጸጥታው ሊገመገም ነው