
የኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረስ ከፍተኛ አመራር አባላት አቶ ጉርሜሳ አያኖ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ አቶ አዲሱ ቡላላ እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 22 ተከሳሾች ዛሬ ልደታ ምድብ ፍርድ ቤት ቀርበው የሰጡት የእምነት ክህደት ቃል ከዚህ የሚከተለው ነው።
ጉርሜሳ አያኖ፤ “ክሱ ግልፅ አልሆነልኝም እኔ ፖለቲከኛ ስሆን የመድረክ ፓርቲ-አባል ነኝ፡፡ የእኛ ፓርቲ ህገመንግስቱን ተከትሎ የተቋቋመ ህጋዊ ፓርቲ ነው፡፡ የተከሰስኩት ግን የኦነግ አባል ነህ በሚል ነው፣ እኔ እስከማውቀው አንድ ሰው የሁለት ድርጅት አባል መሆን አይችልም፡፡ ይሄ ክስ መንግስት መሬቴን አሳልፌ አልሰጥም ያለዉን የኦሮሞን ህዝብ በጅምላ አሸባሪ ብሎ እየከሰሰ ነዉ ያለው ስለዚህ ቃሌን ለዚህ ፍ/ቤት አልሰጥም፡፡”
ደጀኔ ጣፋ፤ “የኢትዮጵያ ፍ/ቤት በግልፅ ህገመንግስቱን እያፈረሰ ያለ ተቋም ስለሆነ ለዚህ ፍ/ቤት ቃሌን አልሰጥም፣ ከአሁን ወዲህም ወደዚህ ፍ/ቤት መምጣት አልፈልግም፣ ውሳኔውም ግልጽ ስለሆነ ባለሁበት ሆኜ ይድረሰኝ! የኢትዮጵያ ህዝብ ግን እኛ ላይ የተፈጸመውን በደል እንዲያውቅልን እፈልጋለሁ፡፡”
አዲሱ ቡላላ፤ “የደረሰኝ ክስ የሚመስል ድርሰት ግራ አጋብቶኛል፡፡ እኔ የመድረክ ፓርቲ እንጂ የኦነግ አባል አይደለሁም፣ ለህዝቤ ብዬ ባደረግኩት ነገር በሙሉ ደስተኛ ነኝ፣ በአዲሱ ስም የተመሰረተው ክስ በኦሮሞ ላይ የተመሰረተ ክስ መሆኑን ሁሉም ሰው እንዲያውቅልኝ እፈልጋለሁ፤ እኔ ለዚህ ፍትህ አልባ ፍ/ቤት ቃሌን መስጠት አልፈልግም ተመካክራችሁ ውሳኔውን ባለሁበት አድርሱኝ!”
በቀለ ገርባ፤ “ባለፈዉ ቀጠሮ የክስ መቃወሚያችን ላይ ወንጀሉ ተፈጸመ የተባለው ኦሮሚያ ክልል ሆኖ ሳለ ለምን በፌዴራል መንግስት እንዳኛለን?! በክልላችን በቋንቋችን እንዳኝ ብለን አቤቱታ አቅርበን ነበር ቢሆንም የሰማን የለም፡፡ እኛን ግን ገብቶናል ለምን ክሳችን በፌዴራል እንዲታይ እንደተደረገ፣ ፍ/ቤቱ በተጻፈለት መሰረት ሊፈርድብን ነዉ፡፡ ይህ ፍ/ቤት ታዞ እንደሚሰራ ከዚህ በፊት ስምንት አመት ያለጥፋቴ ተፈርዶብኝ እኔ በራሴ ህይወት ችግሩ ደርሶብኝ አይቻለሁ ስለዚህ ለዚህ ፍ/ቤት ቃሌን አልሰጥም፡፡”
በዓለምአቀፍ ደረጃ በአሸባሪነት በሚታወቀው ህወሃት፣ “አሸባሪ” ተብለው በግፍ የተከሰሱት እነ በቀለ ገርባ በዚህ መልኩ ተቃውሟቸውን ቢገልጹም ፍርድ ቤቱ ግን ክደው እንደተከራከሩ መዝግቧል።
(ዜናውን ያጠናከርነው ከቪኦኤ ዘገባና #oromoprotest ነው)
Leave a Reply