የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ከፍተኛ አመራር አባይ ጸሃዬ፤ ሳሞራ የኑስን ጨምረው ሌሎች ከፍተኛ የህወሃት ባልደረቦቻቸውንና በመያዝ አሜሪካ አገር አጭር ቆይታ አድርገው መመለሳቸውን ጎልጉል አረጋግጧል። አሜሪካ በግል የተቃዋሚ ፓርቲዎችን በማነጋገር ውሉ ባግባቡ የማይታወቅ የሽግግር ሃሳብ ለመተግበር ማሰቧ ተሰምቷል። የሽግግር ሃሳቡ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) የያዘውን ስልጣን በተወሰነ መልኩ የሚያስቀጥል በመሆኑ ለአሜሪካ ፖሊሲ አውጪዎች ሃሳብ የሚያቀርቡ ተጽእኖ ፈጣሪዎች አሜሪካ ይህንን መሰሉን አቋም እንድትቀይር እየወተወቱ ነው። ለኦባማ አስተዳደር ፖሊሲ አውጪዎች ዕቅድ ለማቅረብ እነዚሁ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ዝግጅት አላቸው። ከሁለት ቀን በፊት አሜሪካ አጭር ቆይታ ያደረጉት እነ አባይ ጸሃዬ “እንወድቃለን” ብለው እንደሚሰጉ ለአለቆቻቸው አስታውቀዋል። የጎልጉል የዲፕሎማት … [Read more...] about እነ አባይ ጸሃዬ አሜሪካ ነበሩ፤ “ኦሮሞና አማራ ተባበሩብን፤ ሰግተናል”
Archives for August 2016
ዱቼ ሙሶሊኒ! ቻው ፋሽስት ወያኔ
ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ … [Read more...] about ዱቼ ሙሶሊኒ! ቻው ፋሽስት ወያኔ
ትድረስ በዚህ ዘመን ላላችሁ ካህናት
በምድራችን ላይ የሚደረጉት ነገሮች በጊዜ፤ በሚፈጸምባቸውና በሚፈጽሙት ሰዎች ይለያዩ እንጅ፤ ድግግሞሽ ናቸው። ባህታዊ አምኃ ኢየሱስ በወያኔ መንግሥት በተበደለው በጎንደር ህዝብ መካከል ቆመው ያሰሙን ድምጽ፤ በጣሊያን ወረራ ጊዜ እነመምህር ገብረ ኢየሱስ ላሰሙት ድምጽ ድጋሚ ነው። ወያኔ በወገን በአገር ላይ የሚፈጽመውን ግፍና መከራ በዝምታ በማለፍ ላይ ያላችሁ፤ ከህዝብ ጋራ አለመታየትን የመረጣችሁ ካህናት ሰባክያንና ጳጳሳትም፤ በጣሊያን ጊዜ ጣሊያንን ላለመስቀየም ዝም ያሉትንና ከህዝብ መካከል የተደበቁትን የካህናትን ዝምታ ደገማችሁ። የተደገመ ነው ብልም፤ ወያኔዎች በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚፈጽሙት መከራና ግፍ፤ ጣሊያኖች ከፈጸሙት መከራና ስቃይ ጋራ ስናነጻጽረው፤ ወያኔዎች የፈጸሙት ከተመሳሳይነቱ እጅግ የራቀ፤ የባሰና የከፋ እንደሆነ፤ በዚህ ዘመን ዝም ያላችሁትንና፤ ከህዝብ መካከል … [Read more...] about ትድረስ በዚህ ዘመን ላላችሁ ካህናት
ለመፍትሔው መፍትሔ
በሌ/ጄ ፃድቃን ገ/ተንሳይ የመፍትሔ ሀሳቦች ምላሽ ለ፡ ሌ/ጄ ፃድቃን ገ/ተንሳይ “የሃገራችን ፖለቲካ ሁኔታና የመፍትሔ ሀሳቦች” ጽሁፍ እነሆ 17 ዓመት በበረሃ 25 ዓመት በመንግሥት ሥልጣን የተቆናጠጠው ወያኔ ዛሬ የሥልጣን ዘመኑ ማብቂያው የመጨረሻው መጀመሪያ ላይ ደርሷል። በትግሉ ላይ ነበርን ብቻ ሳይሆን በከፍተኛ አመራር እርከን ላይ ነበርን የሚሉ የወያኔ ባለሥልጣን፤ የድርጅታቸውን 17 ዓመት የትግል ጉዞ አብረው ፕሮግራም ሲነድፉ፣ ፖሊሲ ሲያወጡ፣ የትግራይ ነፃ አውጪ ብለው በዘር ሲደራጁ፣ የዐማራ የበላይነት ሰፍኗል ብለው አማራ ላይ ሲያነጣጥሩ፣ የብሔር/ብሔረሰቦች መብት እስከመገንጠል ብለው የዘር ፖለቲካ ሲያራምዱ፣ ኤርትራ በኢትዮጵያ ቅኝ ተይዛለች ብለው ከሻቢያ ጋር ለኤርትራ ነፃነት ሲታገሉና ሲያታግሉ የነበሩ ዋናው የድርጅቱ አመራር ባልደረባ ዛሬ የወያኔ ወንበር እንዳበቃለት … [Read more...] about ለመፍትሔው መፍትሔ
አባተ መኩሪያ “ተንቀሳቃሹ ቴአትር ቤት” (1932 – 2008)
‹‹ጥበበኛ በጥበብ እግር ይመላለሳል›› (ጠቢብ የሐውር በእግር ጥበብ) እንዲሉ፣ አባተ መኩሪያ ከግማሽ ምታመት በዘለለ በኢትዮጵያ ቴአትር ሕዋ ውስጥ በጥበብ ለጥበብ ኖሯል፡፡ ለቴአትር እስትንፋሱ ነበርም ይሉታል፡፡ በርሱ ጥበብ ያለፉት ሁሉ፡፡ በጥበብ የባተው አዘጋጅ፣ የውዝዋዜ አሠልጣኝ (ኬሪዮግራፈር)፣ ጸሐፌ ተውኔት፣ የፊልም አዘጋጅ የነበረው አባተ መኩሪያ በአገሪቱ የቴአትር ታሪክ ውስጥ ስማቸው በግዘፍ ከሚነሱትና አሻራቸውን ካሳረፉ በኩሮች አንዱ ነበር፡፡ በተለይ በተውኔት አዘጋጅነት ስመ ጥር ለመሆኑ ዘመን ተሻጋሪ ተውኔቶችን ወጥ እና ትርጉሞች በማዘጋጀቱ ይጠቀሳል፡፡ ከታዋቂ ሥራዎቹ መካከል ሀሁ በስድስት ወር (1966) አቡጊዳ ቀይሶ (1971)፣ መልእክተ ወዛደር (1971)፣ የመንታ እናት (1971)፣ መቅድም (1972)፣ ጋሞ (1973)፣ አሉላ አባነጋ (1979) ይጠቀሳሉ፡፡ … [Read more...] about አባተ መኩሪያ “ተንቀሳቃሹ ቴአትር ቤት” (1932 – 2008)
መጪው ቅዳሜ ለት በመላው ኦሮሚያ ሰላማዊ ሰልፍ ይካሄዳል
እሁድ እለት በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ በአስርታት ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ ወያኔን ተቃውሞ በሰላም ወደ ቤቱ ተመለሰ። በጣም ጥሩና ታሪካዊ ሰልፍ ነበር። በእለቱ ከጥቂት ሰዓታት በኋል ግን በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ አወዳይ ከተማ ወጣቶች ሰልፍ ወጥተው በአጋዚ አልሞ ተኳሾች 26ቱ ቆስለው እስከ አሁን 6 ሞተዋል። ይሄንን እንደምሳሌ ጠቀስኩ እንጂ ኦሮሚያ ውስጥ ወያኔ ሰላማዊ ሰልፈኞችን በጥይት እሩምታ ሲፈጅ አዲስ አይደላም። ባለፉት 9 ወራት ካ600 በላይ ዜጎች ተገድለዋል፣ 5000 የሚሆኑ የመቁሰል ጉዳት ደርሶባቸውል። ይሄንን ቁጥር ወስደን ብናሰላው፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ በየእለቱ ባማካይ ከሁለት እስከ ሶስት ሰዎች ኦሮሚያ ውስጥ በመንግስት ታጣቂ ሃይሎች ሲገደሉ እንደነበረ ማየት ይቻላል። ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈጸም የአምባገኖች ጸባይ ነው ተብሎ ሲታለፍ ነበር። … [Read more...] about መጪው ቅዳሜ ለት በመላው ኦሮሚያ ሰላማዊ ሰልፍ ይካሄዳል
ለኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጥብቅና!
ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን በግሌ አላውቀውም፤ ነገር ግን እስከሚበቃኝ ድረስ አውቀዋለሁ። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ እኔን አያውቀኝም፤ ነገርግን እኔና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ጠበቆቹ እንዳለን ያውቃል። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጎንደር ውስጥ አንገረብ እስርቤት ባሁኗሰዓት - ምሽት፣ ረቡዕ ሐምሌ ፳፯ ቀን ፳፻፰ ዓመተ ምህረት - ለጊዜው አለ። እዚያ እንዲቆይ ያደረገው ወገኑ ነው። ሁላችንም እንደምናውቀው፤ በእስርቤት ያለ ግለሰብ፤ በትክክል ይሁን በድፍረት በመታሰሩ ብቻ፤ ጠበቃ ያስፈልገዋል። እናም ጠበቃው ነኝ። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ለኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጥብቅና!
የነፍጠኞች ፖሊቲካ
ነፍጠኛነት ባህላችን ነው፤ ፖሊቲከኛነት አዲስና ባዕድ የትግል ዘዴ ነው፤ ፖሊቲከኛነትና ነፍጠኛነት ተቃራኒ ተግባሮችን ያመለክታሉ፤ ተቃራኒ ተግባሮች አብዛኛውን ጊዜ ተቃራኒ ዘዴዎች ያስፈልጋቸዋል፤ ለምሳሌ መፍጨትና መቡካት ተቃራኒ ተግባሮች ናቸው፤ መፍጨት ሲበታትን፣ ማቡካት ሰብስቦ ያያይዛል፤ የሚፈጭ ሰው ማቡካት ይችላል፤ እንዲሁም ማቡካት የሚችል ሰው መፍጨት ይችላል፤ ፈጪ አቡኪ መሆን የሚችለውን ይህል ወይም አቡኪ ፈጪ መሆን የሚችለውን ያህል ነፍጠኛ ፖሊቲከኛ ወይም ፖሊቲከኛ ነፍጠኛ መሆን ይችላል ወይ? መልሱ ግልጽ ነው፤ አይችልም፤ የነፍጠኛ ትግል በጠመንጃ ነው፤ የፖሊቲከኛው ትግል በቃላት፣ በንግግር ነው፤ በሌላ አነጋገር የነፍጠኛ በዱላ፣ የፖሊቲከኛ ትግሉ በመላ ነው፡፡ የፖሊቲካ ሥልጣንን ነክሶ ይዞ ሕዝብን በሕዝብ በዱላ እያደባደቡ በማሸነፍም ሆነ በመሸነፍ የሥልጣንን ክብር ማግኘት … [Read more...] about የነፍጠኞች ፖሊቲካ
ታሪካዊው የጎንደር ሰልፍ እና እንድምታው
በሰሞነኛው የአዲስ አቤ ቀልድ ልጀምር። ወጣቱ፣ ሱሪ ለመግዛት ወጥቶ አንድ የልብስ ሱቅ ወስጥ ገባ። ባለ ሱቁ ጠየቀው። “የቻይና ይሁንልህ ወይንስ የአውሮፓ ሱሪ?” ወጣቱም መለሰ። “የለም የለም... የጎንደሩን ሱሪ ነው የምፈልገው።” እስረኞችን የማስፈታቱ ሰላማዊ ጥያቄ የእብሪት መልስ ሲያገኝ፤ ጨዋታውም ተቀየረ። “እንዲያውም አናውቅህም። ከህዝብ ጫንቃ ላይ ወረድ” ሲል ነበር የጎንደር ሕዝብ ብረትን ሰብሮ ዙፋኑን የነቀነቀው። “ወንዱን በምርቃና ሴቱን በቃና አደንዝዘን ይዘነዋል!” ያሉት ሕዝብ ከቶውንም እንዳልተዘናጋ አሳየን.... የመናገር እና ሃሳብን ያለፍርሃት የመግለጽ መብትን ህወሃት ሲፈልግ የሚሰጥ ሲያሻው ደግሞ የሚነፍገው የግል ሃብቱ አድርጎ ለ25 አመታት ሰንብቶ ነበር። ይህ መብት በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ አሸብርቆ ጎንደር ላይ ተከበረ። በባህርዳር፣ በደሴ፣ በኦሮምያ፣ … [Read more...] about ታሪካዊው የጎንደር ሰልፍ እና እንድምታው
ሕዝብን አፍኖና በኃይል ረግጦ መግዛት ያብቃ!
ባለፈው እሁድ ትንሽ ትልቅ፣ ወንድ ሴት፣ ከተሜ ገጠሬ፣ ሳይል የጎንደር ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር በነቂስ ወጥቶ ከተማዋን ባጨናነቀ መልኩ የህወሓት አገዛዝ የፈጠረውን የሽብርና የፍርሃት አጥር ሰብሮ በመውጣት የተቃውሞ ድምጹን በሰላማዊ መንገድ አሰምቶ ወደቤቱ ተመልሷል። ምንም እንኳን አገዛዙ የተቃውሞ ሰልፉ እንዳይካሄድ ማናቸውንም እርምጃዎች ቢወስድም፣ ግፍ የበዛበት፣ የቆረጠና የተባበረን ሕዝባዊ ማዕበል የሚመክተው አንዳችም ምድራዊ ኃይል የለምና ከፍተኛ ጨዋነት በተሞላው መልክ ሕዝቡ ተቃውሞውን አሰምቷል። በዕለቱ ካስተጋባቸው መፈክሮች ውስጥ "በኦሮሚያ የሚደረገው የወገኖቻችን ግድያ ይቁም" የሚለው የጎንደር ሕዝብ ምንጊዜም በኢትዮጵያዊነትና በሀገር አንድነት ላይ ያለው የሚታወቀውን ጠንካራ አቋሙን ያሳየበትና የትግል አጋርነቱን በግልጽ ያንጸባረቀበት ነው። ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ የሕዝብ … [Read more...] about ሕዝብን አፍኖና በኃይል ረግጦ መግዛት ያብቃ!