• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ታሪካዊው የጎንደር ሰልፍ እና እንድምታው

August 2, 2016 01:18 am by Editor Leave a Comment

በሰሞነኛው የአዲስ አቤ ቀልድ ልጀምር። ወጣቱ፣ ሱሪ ለመግዛት ወጥቶ አንድ የልብስ ሱቅ ወስጥ ገባ። ባለ ሱቁ ጠየቀው። “የቻይና ይሁንልህ ወይንስ የአውሮፓ ሱሪ?”  ወጣቱም መለሰ። “የለም የለም… የጎንደሩን ሱሪ ነው የምፈልገው።”

እስረኞችን የማስፈታቱ ሰላማዊ ጥያቄ የእብሪት መልስ ሲያገኝ፤  ጨዋታውም ተቀየረ።   “እንዲያውም አናውቅህም። ከህዝብ ጫንቃ ላይ ወረድ” ሲል ነበር የጎንደር ሕዝብ ብረትን ሰብሮ ዙፋኑን የነቀነቀው። “ወንዱን በምርቃና ሴቱን በቃና አደንዝዘን ይዘነዋል!” ያሉት ሕዝብ ከቶውንም እንዳልተዘናጋ አሳየን….  የመናገር እና ሃሳብን ያለፍርሃት የመግለጽ መብትን ህወሃት ሲፈልግ የሚሰጥ ሲያሻው ደግሞ የሚነፍገው የግል ሃብቱ አድርጎ ለ25 አመታት ሰንብቶ ነበር። ይህ መብት በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ አሸብርቆ ጎንደር ላይ ተከበረ። በባህርዳር፣ በደሴ፣ በኦሮምያ፣ በመቀሌ…. ላይም ይቀጥላል..

ከአርባ አመት በፊት የቬትናም ህዝብ ባዕዳን ያነገሱትን አሻንጉሊት መንግስት በሃይል ሲነቀንቀው፤ አሻንጉሊቱ ስርዓት ለሕዝብ እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አልነበረውም። የህዝብ ያልነበረው ይህ መንግስት ወደ አመሻሹ ላይ ካመሸገበት የአይጥ ጉድጓድ ሆኖ መግለጫ ሰጠ። እንዲህ ሲል፣

“ስልጣኑን ለህዝብ ለማስረከብ ከንጋት ጀምሮ እየጠበቅኩ ነው።…“

የሰሜኑ ህዝብም ምላሽ የተጠበቀው ነበር፣  “ይህን ለማድረግ ትንሽ ዘገየህ።… የሌለህን ስልጣን እንዴትስ ልታስረክብ ትችላለህ?…“

ይህ ተላላኪ መንግስት ወድቆ የነበረው ከህዝባዊው አመጽ እና እንቢተኝነት በፊት መሆኑን አላስተዋለውም። ስርዓቱ የወደቀ ራሱ ያወጣውን ህግ ራሱ ሲሽረው ነበር። ሕዝብ “መንግስት የለም!” ማለት የጀመረው ለአፋኝ አዋጆች አልንበረከክም ብሎ አደባባይ በወጣ ግዜ ነበር።  ይህ መንግስት የተወገደውም ለዜጋው የመብት ጥያቄ የጥይት ምላሽ በሰጠ ግዜ ነው።

“የዘመናችን ትልቁ ክስተት!”  ብሎታል የኩባው ፊደል ካስትሮ።

ባለፈው እሁድ በጎንደር የታየው የሕዝብ እንቢተኝነትም የዘመናችን ትልቁ ክስተት ነበር። ሕዝብ የተፈጥሮ መብቱን ተነጥቆ በጫንቃው ላይ ተጭኖ የነበረውን ቀንበር ያስወገደበት ክስተት!  ስልጣን የህዝብ እንጂ የጥቂቶች መፈንጫ አለመሆኑ የታየበት ክስተት። በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ወርቃማ አሻራ ጥሎ ያለፈ፤ ለሀገር የፍቅር፣ ለዜጎች የፍትህ እና የህብረት ሃውልትን የተከለ ክስተት። የማይቻል የሚመስለውን ተራራ ደርምሶ የናደ ሃይል ስለነበር ታሪክ ይህንን ሰልፍ ይዘክረዋል።

ግዙፉ የጎንደር ሕዝብ ሰላማዊ ሰልፍ እንደተተናቀቀ፣ የህወሃት መገናኛ ብዙሃን የሆነው ፋና ራዲዮ ሲዘግብ፤

“የጎንደሩ የተቃውሞ ሰልፍ በሰላም ተጠናቀቀ።…” ነበር ያለው። “ጋዜጠኛው” ከምጥ እንደተገላገለች ሴት በረጅም ተነፈሰ።

በስፍራው ያልነበረው መገናኛ ብዙሃን በስፍራው የነበረውን ክስተት ሲደሰኩር፣ ለሰላማዊ ሰልፍ ፍቃድ የተከለከለ ህዝብ በራሱ ፈቃድ መውጣቱን፤ በሰልፉም ላይ እነሱ የከለከሉትን ባንዲራ ብቻ መያዙን ጨምሮ አበሰረ።

ይህንን የዜና እወጃ ያዳመጠው የጎንደር ሕዝብ “ይህን ለማድረግ ትንሽ ዘገየህ። …” ሳይለው አልቀረም። ልክ እንደ አሻንጉሊቱ የቬትናም መንግስት፣ የህወሃት የአፈና ግዜ ማብቃቱን እያረጋገጡት ይመስላል። አንድ ስርዓት መንግስትነቱ የሚያከትመው ራሱ ያወጣውን ህግ ራሱ ሲረግጠው እና ሕዝብም ለሱ አዋጅ ተገዥ አለመሆኑን ሲያሳየው ነው። አላስተዋልነው ይሆናል እንጂ ህወሃት እድሜውን ጨርሶ በባከነ ሰዓት እንደሚንገዳገድ “የልማቱ” ተጠቃሚዎች ሳይቀሩ ነግረውን ነበር። እነ ፃድቃን ገ/ትንሳኤ እና አበበ ተ/ኃይማኖት (ጆቤ) ከማጀታቸው ወጣ ወጣ ብለው አገሪቱ እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ፣ መንግስት በሚባለው እና በፓርቲ መሃል እንኳን ልዩነት እንደጠፋባቸው ነግረውናል። ይህ ጉዳይ ጻድቃንን ግራ ካጋባው ሌላው ምን ይበል? ጆቤ የህወሃት ሙስና እና የፍትህ እጦት ካስፈራው ተራው ህዝብ ምን ይሰማው? የሚገርመው ነገር፣ እያየነው ያለው ቀውስ  የነ ፃድቃን እና የነ ጆቤ “ሌጋሲ”ም ጭምር መሆኑ ነው።

የጎንደሩ አመጽ ሁለት አበይት ነገሮችን ጥሎልን አልፏል። አንደኛው መተባበር እና መደጋገፍን ማስተማሩ ነው። አፍንጫ ሲመታ አይን ያለቅሳል እንዲሉ፤ በተለይ የኦሮሞ ወገናችን ደም የሁላችንም ደም ነው ማለታቸው የህወሃትን ከፈፍሎ መግዛት እቅድ የሚያፈርስ መፈክር ነበር። የአኙዋክ መገደል ከአማራው መገደል ተለይቶ አለመታየቱን፣ የሲዳማው ሰቆቃ … የሁሉም ወገን ስእቆቃ እንደሆነ … የሚያሳይ ትእይንት ነበር። በማን አለብኝነት የሚጫኑ አዋጆችን መስበር መቻሉ ደግሞ ስልጣን ዛሬ በህዝብ እንጂ በአንባገነኖች እጅ አለመሆኑን አሳይቶናል። ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ለመብቱ ፈቃድ እንደማያስፈልገው ብቻ ሳይሆን ይልቁንም ጥንት አባቶቹ  በአደራ ያስረከቡትን ባንዲራ ይዞ በመውጣቱም የስርዓቱን ማክተም አሳይቶናል።

የማይነካ የመሰለው ጉልበቱ ሲፈታ፣ የማይሰበር የመሰለው ሃይል ሲሰበር ይህ የመጀመርያው አይደለም። በዘረፉት ሃብት እና በሰራዊታቸው ጉልበት ብቻ እየተማመኑ የገዛ ወገናቸውን ሲበድሉ የኖሩ አንባገነኖች ከቶውንም መቶ አመት ሲቆዩ አላየንም። በአለማችን የተነሱ ብርቱ የሚባሉ አንባገነኖች በህዝብ ሃይል እየተዋረዱ መውደቃቸውን የታሪክ መዛግብት ይመሰክራሉ።

የማያልቅ መንገድ እና የማይነጋ ጨለማ የለም። በአንጻሩ የማይመሽ ቀን የለም። የብዙዎ አንባገነኖች ችግርበ ጉልበታቸው ብቻ በመተማመን ዙፋናቸውን ዘላለማዊ ለማድረግ ማሰባቸው ነው።  በዚህች ተለዋዋጭ አለም ውስጥ ለውጥ  የሰው ልጅ ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ግደታም ነው። ዘገምታኛም ይሁን ቅጽበታዊ፣ እኛም በተራችን ለውጥን የምናይበት ወቅት ላይ ደርሰናል።

ይህ ሊሆን ግድ ነው። ጽዋ እስኪሞላ የሚጨመርለትን ሁሉ ይሸከም እና ከሞላ በኋላ መፍሰሱ ሳይንሳዊም፤ ተፈጥሯዊም ህግ ነውና ከአቅሙ በላይ ሲሞላ ሁሉም ነገር ይፈስሳል። ከየአቅጣጫው ሕዝቡን ገፍተው እዚህ አደረሱት። እነሆም የሕዝብን የቁጣ ወላፈን ትላንት በኦሮሞ ወንድሞቻችን፣ ዛሬ ደግሞ በጎንደር አዩት። ነገ በደቡብ፣ ከዚያም በምስራቅ እና በምእራብ ይቀጥላል። ይህ ቁጣ የመጀመርያው እንጂ የመጨረሻው አይደለም።

“የዚህን መንግስት ያህል በህዝብ ክፉኛ የተጠላ ስርዓት በህይወት ዘመኔ አይቼም ሆነ ሰምቼ አላየሁም።” ሲሉ አንድ ከፍተኛ የኢህአኤግ ባለስልጣን ሲናገሩ አድምጫለሁ። ከውስጣዊ ሰዎች  እንደምንሰማው ከሆነ 90 በመቶ የሚሆኑት የኦህዴድ እና የብአዴን አመራር አባላት ከህወሃት ጋር ሆድና ጀርባ ከሆኑ ሰንበትበት ብለዋል፤ የህዝቡ በደል አንገሽግሿቸው ህዝባዊውን አመጽ ለመቀላቀል በመጠባበቅ ላይም ናቸው። በራሱ በአገዛዙ ውስጥ ያሉ ሁለተኛ ረድፈኞች ሳይቀሩ እንደሚመሰክሩት፤ የህወሃት ወንጀል ደርግ ከሰራው ወንጀል እንኳን ሊወዳደር አይችልም። የበደሉን ብዛት እና የዝርፊያውን ግዙፍነት የሚመሰክሩት ሁሉ ይህ ስርዓት በቅርጽ እንጂ በይዘት እንደሌለ ነው እየመሰከሩ ያሉት። “በአሁን ሰዓት በመንግስት ስም የሚነግድ የማፍያ ቡድን እንጂ መንግስት የለም!” ነው ያለው አንድ ከፍተኛ የብአዴን ሰው።

ሕዝቡ ይህንን ሰርዓት ለምን አይጥላው? ሁሉም ስለታፈነ ሕዝብ ነው የሚናገሩት።  አንድ ለአምስት ተጠረንፎ የተያዘ ሕዝብ፣ እስከውስጥ ገመናው በኢህአዲግኛ መስፈርት እየተገመገመ የሚሰቃይ ሕዝብ፣ ሌት ተቀን በሙስና እንደመዥገር እየተበዘበዘ ያለ ሕዝብ። ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል እንኳን ለመጥራት እየተጸየፉ፣ ሀገርን እና ታሪካዊ ባንድራዋን እየጠሉ፣ … እንዴት ሊቆዩ ይችላሉ?

ለችግሮች ሁሉ መፍትሄያቸው ጠመንጃ ነው። የጎንደሩንም ችግር በጠመንጃ ለመፍታት እየመከሩ ይገኛሉ። በመጀመርያ ከህዝቡ መሳርያ መንጠቅ። ከዚያም እንደ በኦሮሞ ወጣቶች እንዳደረግነው በአልሞ ተኳሾች አማጺውን መልቀም ይኖርብናል ሲሉ ዶ/ር ደብረጽዮን መናገራቸው እየተሰማ ነው። ከ500 ያላነሱ የኦሮሞ ወገኖቻችንን ጨርሰው ሲያበቁ፤ እርምጃው ተመጣጣኝ እና ፍትሃዊ ነው ሲሉ ቀለዱብን። ለመሆኑ ከአንድ ሰብዓዊ ፍጡር እንደዚህ አይነት ፍጹም አረመኔያዊ ነገር ይሰማል? የጭካኔ ጣርያው የት ድረስ ነው?…

መገናኛ ብዙሃን ላይ እየወጡ በህዝብ ላይ የሚያላግጡት ነገር ደግሞ እጅግ ያሳምማል።  ለጥያቄዎች ሁሉ አንድ መልስ ነው ያላቸው። መልሱም “ሻዕቢያ” የሚባል ግዑዝ ነገር። የኦሮሞ ሕዝብ ሰቆቃ ይቁም ብለው የተነሱት ወጣቶች በሙሉ “የታጠቁ እና የተደራጁ የሻዕቢያ ቡድኖች ናቸው” ተባልን። የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ያነሱት ወገኖች ሁሉ ያሻዕቢያ ተላላኪዎች እንደሆኑ ነገሩን። የታገልነው ለነጻነታችን እንጂ ትግሬ ለመሆን አይደለም ያሉት ከራሳቸው ውስጥ ያሉ ታጋዮችም የሻዕቢያ መልዕክተኞች ናቸው። የችግሮቻቸው ሁሉ መንስኤው ሻእቢያ ነው። ይህ ሊሆን ይችላል። 10 ሰው የሻዕቢያ ተላላኪ ሊሆን ይችላል። 100 ሰውም የሻዕቢያ ተላላኪ ሊሆን ይችላል። 1000 ሰው የሻዕቢያ ተላላኪ ሊሆን ይችላል። አንድ ሚልየን ህዝብ የሻዕቢያ ተላላኪ ከሆነ ግን ከነጻነት ትግሉ ጀርባ ሻዕቢያ እንዳለ ነው እየነገሩን ያሉት። ፖለቲካን እንደ ማስንቆ እየቃኘ የሚጫወትበትን ህዝብ፣ እነሱ የሚናገሩትን ሁሉ እንደ ስንዴ እየፈለፈለ እንደሚያበጥረው እንኳን አይገነዘቡም።

የምስራቁ ፈላስፋ ኮንፋሽየስ “ትልቁ እውቀት የራስን የድንቁርና መጠን ጠንቅቆ ማወቅ ነው“ ይለናል። ይህንን ሁሉ ህዝብ የሻዕቢያ ተላላኪ ሲሉ በድፍረት መናገራቸው የድንቁርናቸው መጠን ምን ያህል የወረደ መሆኑን ያመላክተናል። “በወልቃይት ጠገዴ ስቃይ እና እስር ይብቃ!“ የሚለው መፈክር የሻዕቢያ ከሆነ ሻዕቢያ ለወልቃይት ህዝብ መብት በመነሳቱ ሊወገዝ ሳይሆን ይልቁንም ሊወደስ ይገባዋል። እንደ ጣዕረ-ሞት እየተከተለ እንቅልፍ የሚነሳቸው ሻዕቢያ “ለሱዳን የተሸጠው ድንበራችን ባስቸኳይ ይመለስ!“ የሚል መልዕክት ይዞ ህዝብን ማሰለፍ ከቻለ ወዳጅ እንጂ ጠላት አይሆንም።

ሁሌም ህዝብን ማታለል የሚችሉ ይመስላቸዋል። ትላንት የተጫወቱበትን ካርታ ሳይቀይሩ ዛሬም ለመጫወት ይሞክራሉ። በኮብልስቶን፣ በአነስተኛና ጥቃቅን … ወዘተ የተያዘ ወጣት ሁሉ፣ በደል ያላመረረው፣ ንቀት ያላስቆጣው መሆኑን አሁን ማረጋገጥ ይችላሉ።

ካሁን በኋላ እነሱ ሊያደርጉ የሚችሉት አንድ አስፈሪ ነገር ቢኖር፤  የትግራይን ህዝብ ከወንድሙ የአማራና ከኦሮሞ ህዝብ ጋር ደም ማቃባት ብቻ ነው። እዚህ ላይ ነው ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ የሚገባው። የትግራይ ህዝብ የዚህ አናሳ ቡድን እዳ ከፋይ መሆን የለበትም። የትግራይ ሕዝብም በቡድን-በቡድን ተከፋፍሎ የሚሰቃይ መሆኑን መረዳት ይኖርብናል። የተገመገመ፣ የሚገመገም እና ለት ተቀን የሚገመግም ቡድን!  ይህ ሕዝብም ነጻ መውጣት አለበት።


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule