በጎንደር ከተማ በበርካታ ሺዎች የሚቆጠር ሕዝብ ሰላማዊ ትዕይንተ ሕዝብ አካሄደ፡፡ አገራዊና ሕዝባዊ ጥያቄዎችን በማቅረብ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ለሚካሄደው ትግል ያለውን ድጋፍ ገለጸ፡፡ ስልታዊ ጥርነፋውን አልፎ ትዕይንተ ህዝብ ለማድረግ መቻሉ ብአዴን ህወሃት የሚዘውረውን ኢህአዴግ ለመክዳቱ ፍንጭ ሰጥቷል፡፡ እሁድ ሐምሌ 24፤2008ዓም በጎንደር ከተማ የተካሄደውን ሰላማዊ ሰልፍ ህወሃት/ኢህአዴግ ገና ከጅምሩ የማምከን ተግባር ለመፈጸም በርካታ የጸጥታ አባላትን በስፍራው መድቦ ነበር፡፡ ሆኖም ሕዝብ ከቀናት በፊት በተናገረው እና ራሱ ኢህአዴግ እመራበታለሁ በሚለው ሕገመንግሥት መሠረት ሰላማዊ ሰልፉን አስቀድሞ አሳውቆ፤ በአግባቡ መልዕክቱን አስተላልፎ በክብር ተመልሷል፡፡ ዓላማውን የሚያውቅና ለሚያምንበት የቆመ ህዝብ እስካለ ድረስ ኢህአዴግ ሰልፍ ቢፈቅድም ባይፈቅድም ሕዝብ ያለውን … [Read more...] about ብአዴን እንደ ኦህዴድ ከዳ?!
Archives for August 2016
“ወጥቼ ስመለስ የዐሥራ ሦስት ዓመት ልጄ አስክሬን ቤት ጠበቀኝ” የአወዳይ ከተማ ነዋሪ ወ/ሮ ኢፍቱ አብደላ
በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች ላለፉት ዘጠኝ ወራት ሲካሄድ የነበረው ተቃውሞ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በድጋሚ ማገርሸቱንና የሰባትና የ13 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሕፃናትን ጨምሮ በርካቶች እየተገደሉ መሆኑን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስና ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ። “ወጥቼ ስመለስ የዐሥራ ሦስት ዓመት ልጄ አስክሬን እቤት ጠበቀኝ” ያሉ የአወዳይ ከተማ ነዋሪም ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። ተቃውሞው በምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ፣ በምዕራብ አርሲና በምዕራብ ሸዋም እንዳለ ነዋሪዎቹ ይናገራሉ። በምስራቅ ሐረርጌ አወዳይ ከተማ ነዋሪ እንደሆኑ የገለጹት አቶ መሐመድ አብዱራህማን “የዐስራ ሦስት ዓመት ልጄ ተገሎብኛል፤ ቀብሩ ላይ መገኘትም አልቻልኩም” ይላሉ። በምስራቅ ሐረርጌ የሰላምና መረጋጋት ኃላፊ ኢንስፔክተር ግርማ ገላን በበኩላቸው ሞቱ ስለተባሉት ሰዎች የተጣራ መረጃ … [Read more...] about “ወጥቼ ስመለስ የዐሥራ ሦስት ዓመት ልጄ አስክሬን ቤት ጠበቀኝ” የአወዳይ ከተማ ነዋሪ ወ/ሮ ኢፍቱ አብደላ