በጎንደር ከተማ በበርካታ ሺዎች የሚቆጠር ሕዝብ ሰላማዊ ትዕይንተ ሕዝብ አካሄደ፡፡ አገራዊና ሕዝባዊ ጥያቄዎችን በማቅረብ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ለሚካሄደው ትግል ያለውን ድጋፍ ገለጸ፡፡ ስልታዊ ጥርነፋውን አልፎ ትዕይንተ ህዝብ ለማድረግ መቻሉ ብአዴን ህወሃት የሚዘውረውን ኢህአዴግ ለመክዳቱ ፍንጭ ሰጥቷል፡፡
እሁድ ሐምሌ 24፤2008ዓም በጎንደር ከተማ የተካሄደውን ሰላማዊ ሰልፍ ህወሃት/ኢህአዴግ ገና ከጅምሩ የማምከን ተግባር ለመፈጸም በርካታ የጸጥታ አባላትን በስፍራው መድቦ ነበር፡፡ ሆኖም ሕዝብ ከቀናት በፊት በተናገረው እና ራሱ ኢህአዴግ እመራበታለሁ በሚለው ሕገመንግሥት መሠረት ሰላማዊ ሰልፉን አስቀድሞ አሳውቆ፤ በአግባቡ መልዕክቱን አስተላልፎ በክብር ተመልሷል፡፡ ዓላማውን የሚያውቅና ለሚያምንበት የቆመ ህዝብ እስካለ ድረስ ኢህአዴግ ሰልፍ ቢፈቅድም ባይፈቅድም ሕዝብ ያለውን ከማድረግ የማይመለስ መሆኑን በማሳየት ለመማር ለሚፈልጉ ትምህርት ሰጥቶ አልፏል፡፡
ህወሃት ሰልፈኞቹ በአማራነት የጎሣ አስተሳሰብ ብቻ ጠብበው እንዲወጡ በርካታ ሙከራዎችን ቢያደርግም አልተሳካለትም፡፡ የትግራይ ሕዝብ ላይ ጥላቻ የሚቀባ ተግባር እንዲፈጸምና ይህንንም ለራሱ የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ ያሰበው ህወሃት “የሻዕቢያ ተላላኪ ራሱ ህወሃት እንጂ ወልቃይት አይደለም” በሚል መፈክር ምላሽ ተሰጥቶታል፡፡ ችግሩ ያለው ከህወሃት ጋር እንጂ ከትግራይ ህዝብ ጋር እንዳልሆነ ሰልፈኛው በማያሻማ መልኩ ግልጽ ማድረጉ ስርዓቱን እንደግፋለን ለሚሉ የትግራይ ተወላጆችና አክራሪ ወያኔዎች ከጅምላ አስተሳሰባቸው ወጥተው ምላሽ እንዲሰጡ ያስገደደ ሆኗል፡፡ የሰልፈኛው ብዛትና የተቃውሞው ብርታት መቶ በመቶ አሸንፌአለሁ ለሚለው ኢህአዴግ በዓለምአቀፍ ኅብረተሰብ ዘንድ ጥሩ የቤት ሥራ ሰጥቶ አልፏል፡፡
በዚህ ህዝብንና የፖለቲካ አስተሳሰብን ለይቶ ተቃውሞውን በግልጽ ባሰማ ትዕይንተ ህዝብ ላይ ለ25ዓመታት ሲደሰኮር የኖረው የህወሃት የሠንደቅ ዓላማ ጉዳይ በግልጽ ምላሽ አግኝቷል፡፡ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ብቻ አሁንም የኢትዮጵያ መለያ ሰንደቅ መሆኑን ሰልፈኞቹ በይፋ አሳይተዋል፡፡ ባለሰማያዊ ኮከቡን ባንዲራ ይዞ ያልወጡ ሕገመንግሥት ለመናድ የሞከሩ እየተባሉ ሲታሰሩ፣ ሲሰቃዩ፣ … በቆዩባት ህወሃት በግፍ የሚገዛት ኢትዮጵያ ኮከብ አልባውን ሠንደቅ አገር ውስጥ ከፍ ብሎ ሲውለበለብ ማየት የሥርዓቱን ክስረት በግልጽ ያሳየ ነው ተብሏል፡፡
ከዚህም ሌላ ሰልፈኞቹ “በኦሮሚያ የሚደረገው የወንድሞቻችን ግድያ ይቁም፤ በጎዳና ላይ የሚፈሰው የኦሮሞ ወንድምና እህቶቻችን ደም የእኛም ደም ነው” የሚሉ መፈክሮችን በማሰማት፤ በእጃቸውም ምልክት በማሳየት ወራትን ላስቆጠረው የኦሮሞ ትግል ያላቸውን ድጋፍ ሰጥተዋል፡፡ ይህም የኦሮሞን ትግል እንመራለን ለሚሉ ትልቅ ተግዳሮት የጣለ ሆኗ አልፏል፡፡ ምክንያቱም የሁሉም ችግር ፈጣሪ ህወሃት እንደመሆኑ ከጎንደር ለታየው ግልጽ የወገናዊነት ድጋፍና አጋርነት በኦሮሞ አካባቢዎችም እንዲታይ መመሪያ ይሰጡበታል ወይስ “የኦሮሞ ህዝብ ያለማንም አጋዥነት ራሱን ነጻ ያወጣል” በሚል ጭፍን አስተሳሰብ የህወሃትን የዘር ፖለቲካ ሳያውቁት እየደገፉ ይቀጥላሉ? ይህ በቀጣይ ግልጽ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በዚህ ትዕይንተ ሕዝብ ህወሃት በየቦታው ያቋቋመው የአምስት ለአንድና ሌሎች የመጠርነፊያ ስልቶች ዋጋቢስ እየሆኑ መሄዳቸው በግልጽ ታይቷል፡፡ የኦህዴድ የበታችና የመካከለኛ አመራሮችና ካድሬዎች ለህወሃት አንገዛም በማለታቸው በርካታ ተቃውሞዎች በኦሮሚያ ሊካሄዱ የመቻላቸውን ያህል በጎንደርም እንዲሁ በህወሃት የተዘረጋውን ጥርነፋ የብአዴን አመራሮች ከማላላት አልፈው ውስጥ ውስጡን መደገፋቸው ከዚህ ትዕይንተ ህዝብ ጋር በተያያዥ የሚጠቀስ ነው፡፡ ሁልጊዜ ሁለተኛነትን ቦታ በደስታ ሲጫወት የኖረው ብአዴን በዚህ መልኩ እየከዳ ከሄደ እና ከኦህዴድ ጋር ግልጽ አጋርነት ከፈጠረ ህወሃት በኢህአዴግ ስም ደኢህዴንን ብቻ እየዘወረ የትም እንደማይደርስ በተደጋጋሚ ሲነገር የኖረ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የትግል አጋርነት ማሳየትና ባለራዕይ መሆን እንደሚያስፈልግ አገራዊ አጀንዳ በሚያራምዱ ዘንድ በግልጽ ይነገራል፡፡
ፕ/ር መስፍን ፌስቡክ ገጻቸው ላይ በእንግሊዝኛ ባሰፈሩት ሃሳብ “ሕጋዊ ጥያቄዎች ህጋዊ ምላሽ ይሻሉ” ካሉ በኋላ “ይህ ፖለቲካ ነው፤ ሕገ አራዊት መወገድ አለበት፤ ጀማሪና ብቃት ያጠራቸው ሹሞች ወደአእምሯቸው ተመልሰው በአገሪቷ ላይ ያለው አደጋ እጅግ አደገኛ መሆኑን ሊያስተውሉ ይገባል” ብለዋል፡፡
“ሁላችንም ለእያንዳንዳችን፤ እንዳንዳችን ለሁላችንም፤ ስንተባበር እንቆማለን፤ ስንከፋፈል እንወድቃለን” በማለት “የኦሮሞ ደም የለም፤ የአማራ ደም የለም፤ … ሁላችንም የአንድ ደም ውጤቶች ነን፤ ከዘር በፊት ሰብዓዊ ፍጡራን ነን” በማለት የሚታወቁት አቶ ኦባንግ ሜቶ ከጎንደሩ ትዕይንት ጋር የተያያዘ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳሬክተር የሆኑት ኦባንግ በዚህ መልዕክታቸው ላይ “የተባበረ ህዝብ መቼም ቢሆን አይወድቅም፤ ሕዝባችን እንደ አንድ ቤተሰብ በአንድነት ሲቆም መመልከት የሁላችንም የምትሆነውን አዲሲቷን ኢትዮጵያን ለመመሥረት የሚያስችለን በመሆኑ ተስፋና መጽናናት ይሰጠኛል፤ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ በሆነው ሠንደቅ ዓላማ ስር በኩራት ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ መመልከት ታላቅ ደስታ ይሰጠኛል” ብለዋል፡፡ አቶ ኦባንግ በዚህ መልዕክታቸው የችግራችን ምንጭ አንድ በመሆኑ በአፓርታይዳዊ ስልት የዘር መከፋፈል ያመጣብንን የህወሃት ሥርዓት በአንድነት መታገል እንደሚገባ ሁሉንም የኢትዮጵያ ወገኖች በማሳሰብ ተባብረን ከቆምን ፍትህ በኢትዮጵያ የሚሰፍንበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡
በትዕይንተ ህዝቡ ላይ ከተሰሙት መፈክሮች ጥቂቶቹ፡-
የሻዕቢያ ተላላኪ ህወሃት እንጂ ወልቃይት አይደለም!
በኦሮሚያ የሚካሄደው የወንድሞቻችን ግድያ ይቁም!
አገራችንን ለሱዳን አሳልፈን አንሰጥም!
መብታችን ይከበር!
ለሱዳን የተሰጠው የሱዳን መሬት በአስቸኳይ ይመለስ!
በጋምቤላ የሚካሄደው አፈና በአስቸኳይ ይቁም!
ኮሎኔል ደመቀ በአስቸኳይ ይፈታ!
የወልቃይት ጠገዴ ጥያቄ የአማራ ሕዝብ ጥያቄ እንደሆነ እናረጋግጣለን!
በጎዳና ላይ የሚፈሰው የኦሮሞ ወንድምና እህቶቻችን ደም የእኛም ደም ነው!!
የሚሉና ሌሎችም ይገኙባቸዋል፡፡ (ፎቶዎቹን ያሰባሰብነው ከማኅበራዊ ገጾች ነው)
ሌሎች ፎቶዎችንና ባለፉት 24 ሰአታት በኦሮሚያ እየተካሄደው ስላለው ተቃውሞ ግርማ ሞገስ የላኩልንን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
tesfai habte says
የጎንደርን ህዝብ የጀብደንነቱ፡ ጀግነነቱን፡ ምስል ለዓለም ኣሳይተዋል። በቃ!!—ህውሃት የለቀለት መሆኑን ዛሬ ብተግባር ኣሳይተዋል። ይህ ነው የመስዋእትነት መንገድ።
Jijjaw says
ANDM have no choice except standing with its base, the Amhara people. TPLF put ANDM on the the edge by disrespecting them. What can ANDM do if Tigray send its commando to hijack people in the Amhara region?
Did you notice how TPLF medias are reporting today’s historic event? Read between the lines and you will see their despair and frustration. The “guardians of the constitution” are telling us that the demonstration is not legal, the demonstrators waved “clothe” which is not legal, the demonstrators “chant” so many things not legal, … not legal …not legal. They praise the “peace loving” Agazie forces for not shading any blood. Humm.. The demonstration in Gondar was peaceful not because of the mad tplf or its Agazi killing machine but the age old wisdom of Gondar: fire can be dealt only with fire. Your killing machine Agazi was positioned to shoot at people. But our gallant Militia was also positioned to slaughter them. The green yellow red flag that turn your stomach upside down is the Ethiopian flag. Bad you don’t like it but you have your Stalinist flag for your wogagoda state too. By the way, your true Agazi State is only Agame. Tembene and Enderta are Agaws, Raya is Oromo, Western Tigray and Axum are the heart and soul of Amhara. You will soon have your Independent Tigray aka Agame bordering to the west, south, and East with Ethiopia, and to the north Eritrea. I hope you will build your state with your ‘fingernails’ this time too. Sorry we don’t want you and I don’t think Eritrea will want you either. You are not worth to win the trust of Ethiopians and Eritreans.
One more thing to note: after 40 years of aggressive anti Amhara propaganda, who is standing with you now, tplf? Just few Sileties and Aderes?
On behalf of ANDM and All the Amhara people
Tebaber