* “ብልጡን ባለ ራዕይ መሪ” ክፉኛ ናፍቋል! የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር /ህወሃት/ አመራሮች ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ከመግደልና ከማስገደል እንዲታቀቡ ታዘዋል። ግድያው የሚቀጥል ከሆነ ከወትሮው በተለየ ርምጃ እንደሚወሰድ ተነግሯቸዋል። “ወልቃይትን ለባለቤቱ ህዝብ ብንመልስ ይሻላል” በሚሉና “አንመልስም” ሲሉ በሚቃወሙ መካከል ክርክር የጀመረው ህወሃት ስምምነት ሊደርስ አልቻለም። ሁኔታው መለስን ከመቃብር ቀስቅሷል። አባይ ጸሃዬ፣ ሳሞራ የኑስና ሌሎች ባለስልጣናት አሜሪካ እንደነበሩ ለጎልጉል ጠቁመው የነበሩት የመረጃው ምንጮች እንዳሉት ባለስልጣናቱ ግድያ እንዲያስቆሙ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ተቀብለዋል። በአማራ ክልል የተነሳው ተቃውሞ ያሳሰበው ህወሃት በተመሳሳይ አሜሪካ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወደ ሰላማዊ ድርድር እንዲመጡ ጫና እንድታደርግ ጠይቀዋል። ለዚህም ይመስላል በአሜሪካ በኩል የተቀናቃኝ … [Read more...] about ወልቃይትን ለባለቤቱ ህዝብ ለመመለስ ህወሃት እየመከረ ነው
Archives for August 2016
የህዝባችንን የትግል ፈር እንከተል!!
ለወራት በኦሮሞ ወጣቶች ሲካሄድ የቆየው ለዴሞክራሲ የሚደረገው ህዝባዊ ትግል ሳያቋርጥና እየሰፋም እየሄደ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እየደጋገሙ ሲታገሉለት የቆየው የህዝቦች ወንድማማችነትና የትግል አንድነት ጥያቄም ባለፉት ሳምንታት በአማራውና በኦሮሞ ክልሎች በሚካሄዱት ሰላማዊና ህዝባዊ ትግሎች አማካኝነት ስር እየሰደደ መሆኑን እየታዘብን ነው፡፡ በዚያው ልክ ደግሞ በትግሉ ማየልና መስፋት ብርክ የያዛቸው የወያኔ/ ኢህአዴግ መሪዎች ህዝቡ በሰላማዊ መንገድ ለሚያቀርባቸው ጥያቄዎች ለመስጠት የሚሞክሩት አጸፋ በለየለት ጸረ ህዝብ አመጽ መሰማራት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ በዚህ መልክ ባለፉት ወራት በኦሮሞ ታጋዮች ላይ ያወረዱትና በመቶ የሚቆጠሩ ንጹህ ዜጎችን መግደልና በሽህ የሚቆጠሩ ሌሎችን ለእስር መዳረግ ሳይበቃቸው አሁን ደግሞ በኦሮሞም በአማራም ታጋዮች ላይ ይህንኑ … [Read more...] about የህዝባችንን የትግል ፈር እንከተል!!
የትግሬዎች መንግሥት አወዳደቁና ክፋቱ!
ባሁን ሰዓት፤ በገዥነት ሕልሙ እየተንሳፈፈ ካለው የትግሬዎች ቡድን በስተቀር፤ ኢትዮጵያን አደጋ ላይ የጣላት ይሄው ቡድን፤ የውድቀት አፋፉ ላይ መሆኑ ለሁላችን ግልጽ ነው። አሁን ካለንበት ሰዓት እስከመጨረሻው ውድቀቱ ያለው ጊዜ ግን፤ በጣም የከፋና የተመሰቃቀለ ነው። ይህ የሚሆነው፤ ከፊል በዚህ ወራሪ ቡድን ተግባር ሲሆን፤ ከፊሉ ደግሞ በኛው በታጋዩ ክፍል ያለነው ለዚህ ውድቀት በማድረግና ባለማድረግ ላይባለው ሂደታችን ነው። በተጨማሪ ደግሞ፤ የሃያ አምስት ዓመት የዚህ ቡድን ፀረ-ኢትዮጵያ አገዛዝ፤ ሀገራችንን ለከፋ ወደፊት አዘጋጅቷታል። ሀቁን ተቀብለን ከአሁኑ መደረግ ያለበትን ካላደረግን፤ በኋላ ይሄን ብናደርግ ኖሮ ብለን የመቆጫ ሰዓት አናገኝም፤ ያኔ ሁኔታውን አንገዛውምና! ይህ ወራሪ ቡድን፤ የመጨረሻ እስትንፋሱን የሚያወጣው በቃሬዛ ነው።ሕዝቡ አቸናፊ ሆኖ እንደሚወጣ ምንም ዓይነት … [Read more...] about የትግሬዎች መንግሥት አወዳደቁና ክፋቱ!
የትግሬ-ወያኔ የዐማራ እና የኦሮሞ ነገዶችን ሕዝብ ጨርሶ ለማጥፋት ያቀደው ሚስጢራዊ አዲስ ሤራ
ላለፉት 25 ዓመታት የትግሬ-ወያኔ በሕዝብ ላይ የፈጸመው ግፍና በደል ከመጠን በላይ በመሆኑ፣ ሕዝቡን ለእምቢተኝነት አነሳስቷል። ይህ ግፍና በደል መጠን የለሽ በመሆኑ፣ በአገሪቱ ልዩ ልዩ ክፍሎች፣ በተለይም በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋ፣ በወሎ፣ በሐረርጌ፣ በአርሲና በወለጋ ክፍለ-ሀገሮች የሚኖረው ሕዝብ፣ የትግሬ-ወያኔ «ለብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ዕኩልነት» ሲል «አመጣሁት» ያለውን «ሕገ-መንግሥት» የማይቀበለው መሆኑንና፣ የዚሁ «ሕገ-መንግሥት» ተብየ መገለጫ የሆነውን ሠንደቅ ከተሰቀለበት በማውረድ፣ ከጥንት ጀምሮ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት መገለጫ፣ የነፃነት ቀንዲል የሆነችው ሠንደቅ ከፍ-ብላ እንድትውለበልብ እያደረገ መሆኑ በግልጽ ተስተውሏል። ይህም የትግሬ-ወያኔ አመጣሁት ያለው ዕኩልነትና የነገዶች አንድነት ውሸት መሆኑን፣ ባንፃሩ ግን የትግሬ-ወያኔ የውስጥ ቅኝ ገዥ ኃይል … [Read more...] about የትግሬ-ወያኔ የዐማራ እና የኦሮሞ ነገዶችን ሕዝብ ጨርሶ ለማጥፋት ያቀደው ሚስጢራዊ አዲስ ሤራ
በሆላንድ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ
“መዝሙሩማ…”!
“መዝሙሩማ” መዝሙር ነው - የኅብረ-ዜማ ውጤት፣ ሕዝብን ያስተሳሰረ - የአንድነት ሰንሰለት፤ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ - ከደቡብ እስከ ሰሜን... ተዳርሶ በድንገት፣ በቅብብሎሽ ያስተጋባ - የነጻነት አዝማች ልደት! ደራሲውም ሕዝብ ነው - መሳሪያውም ባህላዊ፣ ዘረኞችን እሚያሸማቅቅ፣ ግፈኞችን እሚያርበደብድ... ኃያል ድምፅ ምትሃታዊ! “መዝሙሩማ” መዝሙር ነው - የብሩህ ዘመን ብስራት፣ በደም ቀለም የተጻፈ! - እሚዘመር በሕዝብ አንደበት! (ስማ! አቶ “ጌታቸው”!) . . . ከእንግዲህማ አትልፋ - ዘመንህን በከንቱ አትጨርስ፣ ክፋት ፕሮፓጋንዳህን - እሳት ባገር ከመለኮስ፣ ይልቁንስ ጠጋ በል -“ሕዝበ-መዝሙሩን” በደንብ አጥና፣ ያንተም መፃዒ ዕድል - በሕዝብ ድል እንዲቃና! እንጂማ!... መዝሙሩማ ኀብረ-መዝሙር … [Read more...] about “መዝሙሩማ…”!
“የማን ተጋድሎ ነው…?”
ወያኔ ኢትዮጵያን እያፈራረሰና ህዝቡን ‘ርስ በርስ እያባላ ያለው ብቻውን አይደለም። የሀገሪቱ ጠላቶች፣ ሆድ-አደሮች፣ መሀል-ሰፋሪዎች፣ ግብዞችና የመሳሰሉ ሁሉ አጋጣሚውን ይጠቀማሉ። ሲጠቀሙም ኖረዋል። ወያኔና ግብረ–አበሮቻቸው እኮ ኢትዮጵያን የማፈርስረሱን መረሀ-ግብር የተቀበሉት ከምዕራቡና ከዐረቡ ዓለም ነው። መርሳት የሌለብን ወያኔ ከዚህ ደረጃ እንዲደርስ የኛ አስተዋ’ጾ መሆኑን መቀበል አለብን። ማርቲን ሉተር ይመስለኛል፤ "ካልተጎነበስክላቸው እነሱ ከአንተ ጀርባ ላይ አይወጡም!" ያለው። ቁምነገሩ ካለፈው መማር መቻላችን ላይ ነው። በርግጥ አሁን ብዙሀኑ የወያኔን “አሪወሳዊነት” ከማንኛውም ግዜ በበለጠ የተረዳበትና የ40 ዓመት የከፈፍለህ የቤት ስራ "ፉርሽ" የሆነበት ነው። ይሁን እንጂ ብዙ ድህረ-ገጾች፣ ዜና – ዘጋቢዎች፣ ዘፋኞች፣ ሰላማዊ … [Read more...] about “የማን ተጋድሎ ነው…?”
The Untold Plight of the Amhara People
The massive civil uprising in Ethiopia last week has captivated the attention of the world. Needless to say the world is now well aware of the protest by the Oromo ethnic group, the so called Oromo Protest, that has been going on for the last nine months. The second largest ethnic group, the Amhara, joined the uprising last week. The magnitude and consistency of the uprising in Amhara is quite a surprise and uncommon for many non-Ethiopians, including the mainstream media. It has however been … [Read more...] about The Untold Plight of the Amhara People
የዋዜማ አቋም እና ጥሪ በወቅታዊው የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ
“የዋዜማ አቋም እና ጥሪ በወቅታዊው የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ” በሚል ርዕስ የዋዜማ ሬዲዮ ይፋ ያደረገውን መግለጫ የጎልጉል ኤዲቶሪያል ቡድን ተወያይቶበታል፡፡ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ከተቋቋመበት ዓላማና ከሚከተለው የአስተሳሰብ መስመር አንጻር የዋዜማ መልዕክት አብሮት የሚሄድ በመሆኑ የቀረበውን ወቅታዊ ጥሪ ከነሙሉ ዓላማ ከዚህ በታች አትመናል፤ በቀጣይ ለሚደረጉ ሥራዎችም እንደ ሚዲያ የሚጠበቅብንን ሁሉ ለመፈጸም ፈቃደኞች መሆናችንን እና ሌሎችም በተመሳሳይ ተግባር ላይ ያላቸውን ትብብር እንዲያሳዩ በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ ኢትዮጵያ አሁን የደረሰችበት ፖለቲካዊ ቀውስ ከወትሮው በተለየ አስጊና አስከፊ አደጋን ያረገዘ ሆኖ ይታያል። የፖለቲካ ቀውሱን “የመልካም አስተዳደር እጦት፣ የዴሞክራሲ አለመዳበር” እያሉ መግለጽ ከፊታችን የተደቀነውን አደጋ አቅልሎና የተለመደ … [Read more...] about የዋዜማ አቋም እና ጥሪ በወቅታዊው የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ
ኢህአዴግ ወደ ወታደራዊ አገዛዝ ሊቀየር ይችላል
በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እየተካሄደ ያለው የሕዝብ እምቢተኛነት ያሰጋው የኢህአዴግ አገዛዝ በይፋ ወታደራዊ አገዛዝ ለማወጅ ዕቅድ እንዳለው እየተሰማ ነው። ህወሃት ወታደራዊ አገዛዝን ለማወጅ አማራጭ መንገድ የያዘው “አጋር” በሚላቸው ድቃይ ድርጅቶቹ ላይ ያለው እምነት እየተሟጠጠና የቀድሞው ታዛዥነታቸው በመመናመኑ ነው። አገርን ለማዳን በሚል ለአሠራር ያልተመቹትን እያስወገደ ለብቻው ይነግሣል ተብሎ ተነግሯል፡፡ የጎልጉል ዜና አቀባዮች የመረጃ ምንጮቻቸውን ጠቀሰው እንደዘገቡት በኢህአዴግ ስም ህወሃት ራሱ ያደራጃቸው “አቻ ድርጅቶች” አሁን የተነሳበትን የከፋ ተቃውሞ እንደተቀላቀሉበት፣ በነዚሁ ታዛዥ ድርጅቶች አማካይነት የተዘረጋው የጥርነፋና የስለላ ሰንሰለት መፈረካከሱና አባላቱ እንደከዱት ከድምዳሜ ላይ ደርሷል። በዚህም የተነሳ ሁኔታዎች ከቁጥጥር ከወጡና ህዝባዊ እምቢተኛነቱ ከሁለቱ … [Read more...] about ኢህአዴግ ወደ ወታደራዊ አገዛዝ ሊቀየር ይችላል