በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እየተካሄደ ያለው የሕዝብ እምቢተኛነት ያሰጋው የኢህአዴግ አገዛዝ በይፋ ወታደራዊ አገዛዝ ለማወጅ ዕቅድ እንዳለው እየተሰማ ነው። ህወሃት ወታደራዊ አገዛዝን ለማወጅ አማራጭ መንገድ የያዘው “አጋር” በሚላቸው ድቃይ ድርጅቶቹ ላይ ያለው እምነት እየተሟጠጠና የቀድሞው ታዛዥነታቸው በመመናመኑ ነው። አገርን ለማዳን በሚል ለአሠራር ያልተመቹትን እያስወገደ ለብቻው ይነግሣል ተብሎ ተነግሯል፡፡
የጎልጉል ዜና አቀባዮች የመረጃ ምንጮቻቸውን ጠቀሰው እንደዘገቡት በኢህአዴግ ስም ህወሃት ራሱ ያደራጃቸው “አቻ ድርጅቶች” አሁን የተነሳበትን የከፋ ተቃውሞ እንደተቀላቀሉበት፣ በነዚሁ ታዛዥ ድርጅቶች አማካይነት የተዘረጋው የጥርነፋና የስለላ ሰንሰለት መፈረካከሱና አባላቱ እንደከዱት ከድምዳሜ ላይ ደርሷል።
በዚህም የተነሳ ሁኔታዎች ከቁጥጥር ከወጡና ህዝባዊ እምቢተኛነቱ ከሁለቱ ክልሎች ማለትም ከኦሮሚያና ከአማራ ክልል ወደ ሌሎች ከተዛመተ ህወሃት “አጋር” የሚባሉትን ድርጅቶች በይፋ ያፈርሳል፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያውጃል፤ ለይስሙላ ይጠቀምበት የነበረውን ሕገመንግሥት ያግዳል፤ የሰዓት ዕላፊ ይደነገጋል፤ ከወታደራዊ ምክርቤቱ (ደርግ) በሚወጣ ትዕዛዝ ብቻ አገሪቱን ማስተዳደር ይጀምራል፤ ይህንንም በማድረግ የነፍጥ አንጋች /ወታደራዊ/ አገዛዝ በማቋቋም የሽግግር ጊዜ ያውጃል። በዚህ ወቅት የተወሰኑ መለሳለሶችና ውጥረት ማርገቢያ ውሳኔዎችን ሊያስተላልፍና ተግባራዊ ሊያደርግ ይችላል፤ ይህም ህወሃትን እንደ አዲስ በማደራጀት የላዕላይ መዋቅሩን እንደያዘ አሁን ካለው ሁኔታ “የተሻለ” የሚያስብል “ጥገናዊ ለውጥ” ማድረግን ይጨምራል፡፡ እንደ መረጃው ምንጮች ከሆነ ይህ ሃሳብ በወታደራዊና ደኅንነት ዙሪያ በርካታ መዋዕለ ንዋይ ባፈሰሱት የህወሃት ለጋሾችና አንጋሾችም ጭምር ተቀባይነት አለው።
ኦሮሚያና አማራ ክልል ህዝብ የራሱን አስተዳደር በማወጅ የገጠርና አነስተኛ ከተሞችን በድንገት ይቆጣጠራል የሚል ስጋት ያለው ህወሃት፣ ከወዲሁ ወታደራዊ አስተዳደር የሚያቋቁምበትንና ህገ መንግስት አፍርሶ አገር በማዳን ሰበብ ያፈቀደውን ርምጃ ለመውሰድ ለራሱ ፈቃድ ለመስጠት ከውሳኔ ላይ መድረሱን ለማወቅ ተችሏል። የመረጃው ምንጮች አካሄዱን “ባጭሩ ኢህአዴግ ፈርሶ ህወሃት ብቻውን ይነግሳል” ሲሉ ነው የገለጹት፡፡
ስለጉዳዩ አስተያየት የሰጡ “ይህ አዲስ አይደለም። አሁንም አገሪቱ በወታደራዊ አስተዳደር ነው የምትመራው። ልዩነት ቢኖር አዋጅ የሚያውጁ ከሆነ ብቻ ነው” ይላሉ። አያይዘውም ካሁን በኋላ እንደኩፍኝ ተገልብጦ የወጣውን የህዝብ ቁጣ አሁን ባለው መልኩ ማስቆም የሚቻል እንዳልሆነ ይናገራሉ። በሌላ በኩል ውሳኔው የሰሩት ግፍና የዘረፉት ሃብት፣ የያዙት እቅድና የተለሙት ህልም ድምር ውጤት ከመሆን እንደማያልፍ ጠቁመዋል።
በኦሮሚያ ለወራት የዘለቀው የመስዋዕትነት ተቃውሞ ኦህዴድ ለመክዳቱ ግልጽ ማስረጃ የሰጠ ሆኗል፡፡ በተለይም በመቶዎች የሚቆጠሩ አባላቱ በህወሃት እንዲወገዱ ከተደረጉ በኋላ በክልሉ የዘለቀው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ህወሃት ኦሮሚያን በወታደራዊ ዕዝ ሥር እንዲያውል አስገድዶታል፡፡
በይፋ ባይረጋገጥም ሰሞኑን በማኅበራዊ ገጾች የተሰራጨው መረጃ ህወሃት ተመሳሳይ እርምጃ በአማራ ክልል የመውሰድ ሂደት ላይ መሆኑን ጠቁሟል፡፡ በብአዴን ታዛዥነት ለዓመታት በሥራ ላይ ሲውል የነበረው ስለላና ጥርነፋ ከአገልግሎት ውጪ በመሆኑ የአማራን ክልል በወታደራዊ ዕዝ ለመምራት ዕቅድ መነደፉን ይኸው ራሱን “የአማራ ተጋድሎ” በሚል የመረጃ ልውውጥ የሚያደርገው ክፍል በዝርዝር አስታውቋል፡፡
በፌዴራላዊ አወቃቀር የይስሙላ ሥልጣን ለክልሎች እየሠጠ የአገዛዝ ዕድሜውን ያራዘመው ህወሃት አሁን ከገባበት አጣብቂኝ ለመውጣት “አገርን ማዳን” በሚለው ፈሊጥ አዲስ ስሌት መቀመሩ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ይሰማል፡፡ በመሆኑም በኦሮሚያ ተግባራዊ ከሆነው ጋር ተዳምሮ በአማራ ክልል ለመተግበር እየተወጠነ ያለው የአስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር በዓለምአቀፍ ኅብረተሰብ ዘንድ (የሰብዓዊ መብቶች አስጠባቂ ድርጅቶችና የተባበሩት መንግሥታትን ጨምሮ) በማያስጠይቅ መልኩ ህወሃት አገሪቱን በፈላጭ ቆራጭ ወታደራዊ የበላይነት እንዲገዛ በር የሚከፍት ይሆናል፡፡
“የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት” በሚል ነገር ግን ጸረ-እኩልነት በሆነ ስልት አናሳው ህወሃት በአገዛዝ የመቀጠሉ ጉዳይ አሳሳቢ ስለሆነበት ኦህዴድ ላይ እንደዘመተው ሰሞኑን ብአዴን ላይም እያመረረ ይገኛል፡፡ ከዚህ አንጻር የህወሃት ልሣን በሆነው አይጋ ፎረም ላይ ብአዴን መብጠልጠሉ የመጨረሻውን መጀመሪያ እንደሚያመላክት ሃሳብ እየተሰጠበት ይገኛል፡፡ Exhibits of the Hijack of ANDM by Rotten Neftegnas በሚል ርዕስ የወጣው ጽሁፍ ላይ ስለብአዴን እንዲህ ተብሏል፤ (የአማርኛውን ትርጉም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
“ብአዴን የራሱ ነፍስ የሌለው ደርግን ለመጣልም በተደረገው ትግልም ብአዴኖቹ ከሞነጫጨሯቸው ጥቂት ግጥሞችና የፍቅር ደብዳቤዎች ውጭ ምንም ሚና የተጫወቱት ነገር አለመኖሩም ገሃድ የወጣ እውነት ነው። እንደውም ብአዴን የህወሃትን ገድል የሚያሳይ ቪዲዮ ሰርቆ ፫፭ኛ ዓመት በዓሉን ሲያከብር በአማራ ቴሌቪዥን ላይ ምንም አይነት ለውጥ ሳያደርግ የራሱ ገድል አስመስሎ አሳይቷል። ብአዴን ይህንን ያደረገው በጦርነቱ ወቅት በባልተቤትነት ይዞት የነበረ አንድ ነጠላ የቪዲዮ ክር እንኳን ስለመኖሩ የሚታውቅ ነገር በሌለበት ሁኔታ ውስጥ ነው።
“በዚሁ የሰላሳ አምስተኛ አመቱ ክብረ በዓል ላይ ከሃቁ ባፈነገጠ መልኩ ተጣመውና ተጋነው ከቀረቡትጭብጦች መካከል ብአዴን ያለማንም እርዳታ በራሱ ግዜ እራሱን ችሎ የተፈጠረ አስመስሎ ለመዘከር የሄደበት ደረጃ ነው። ይህ ማለት ባጭሩ ብአዴንን ህወሃት የፈጠረው አይደለም ለማለት ተፈልጎ ነው።”
ይህ “ፈጣሪህ ነበርኩ፤ አሁን ደግሞ እንዳትኖር አደርግሃለሁ” የሚለው የህወሃት አስተሳሰብ ግልጽ በሆነ መልኩ በህወሃትና በብአዴን መካከል የተከሰተውን ፍቺ የሚያሳይ ሆኗል፡፡ ህወሃት በዚህ መልኩ “ኢህአዴግ” በሚል ማታለያ ከሰበሰባቸው ድርጅቶች ጋር ፍቺ እየፈጸመ ሄዶ ኢህአዴግን ወደ ወታደራዊ አገዛዝ በመቀየር “ንግሥናውን” ለብቻው ይቆጣጠረዋል፡፡
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
አለም says
ጎልጉል፤ [እባካችሁ አስተያየቴን አታንሱ። እንኳን እናንተ የህወሓት ገጾች ወቀሳዬን ለጥፈዋል፡)]
ጻድቃን በህወሓት ብሎግ ሆርን አፌርስ ስለ ለጠፈው ጽሑፍ ትንሽ ልበል። ሁለቴ በጥንቃቄ አንብቤለታለሁ። በዝብዝቡ መንገላታት አያሻንም። በግልጽ ያስቀመጣቸውን እንመልከት። 1/ ስለ ኢትዮጵያ ሁኔታ ከጓደኞቼ ጋር ተመካክረን ነበር ብሎናል፣ ጓደኞቹ እነማን እንደሆኑ ግልጽ ነው 2/ ስለኢትዮጵያ የነገረን የማናውቀውን አይደለም፤ ህወሓትን አሳጥቶ መጻፉ ለአንዳንዶች አስገራሚ መስሎ ይታይ ይሆናል። ጉዳዩ ግን፣ ህወሓት በራሱ ሊለው የማይችለውን ተመካክረው እያለላቸው ነው 3/ ምርጫ ይኑር፣ የምርጫ ውጤት ለመቀበል ፈቃደኛ መሆን አለብን ብሎአል 4/ የርሱ ሃብት ማካበት በራሱ ጥረት እንደሆነ ሊያሳምነን ሞክሯል 5/ ስዬን ጠቅሷል 6/ የኢትዮጵያን ሠራዊት በትኖ የህወሓትን መተካቱን በወቅቱ “National defense and economic development”ብሎ ያቀረበውን ሰነድ ቆንጽሎ ሙሉውን ሰነድ ሊደብቀን ሞክሯል 7/ ዛቻ ብጤም አሰምቷል፤ ካለዚያ ደም በደም እንሆናለን ብሎ። ድምዳሜዬ? 1/ የህወሓት አካሄድ እንደማያዋጣ ተረድቷል፤ ስዬ እንደሞከረው [ትዝ ይልሃል? አንዴ እስር ቤቱ ኦሮምኛ ይናገራል ያላትን?] 2/ ደቡብ ሱዳን ላይ ለአሜሪካኖች ዓላማ አስተባባሪ ሆኖ እየሠራ ነው፤ ስዬ ምዕራብ አፍሪካ ላይ። 3/ ህወሓት ከመለስ ሞት በኋላ መስማማት ስላልቻሉ ኃ/ማርያምን አስቀምጠው ካብ ለካብ እየተያዩ ነው፤ “ኮሌክቲቭ ሊደርሽፕ” በሚል ማጭበርበሪያ ኃ/ማርያምን ደብረጽዮን፣ በረከት፣ አባይ፣ ብርሃነ ገ/ክ ገንዘቡን ሥልጣኑን ተቀራምተውታል፤ አንዱ ችግር ይኸው ነው። አሜሪካኖች የችግሩን መጠን ያውቁታል፤ አታላይነቱ ስለገባቸው የመለስ መወገድ እረፍት ሆኗቸው ነበር፣ አሁን ደግሞ የዋለለ ጉዳይ እንዲቀጥል አይፈልጉም። ህወሓት ሶማሌን፣ ደቡብ ሱዳንን በኢትዮጵያውያን ደም እየነገደ አመቻችቶላቸዋል። ይህን ነገር መፍትሔ ስጡ እያላቸው ነው። የወገኖቻችን ደም መፍሰስ ምንም ያልመሰለው ለዚህ ነው። በተባበሩት መንግሥታት ጸጥታ ጉዳይ ኢትዮጵያ ወንበር ያገኘችው በአሜሪካና በእንግሊዝ እርዳታ ነው። አሁን የሚፈለገው ጻድቃን [ወይም ስዬ] እንደ ታዳጊ ቀርቦ የአሜሪካኖችን ዓላማ ያስፈጽማል፤ በዚያውም የህወሓትን የበላይነት ይታደጋል ማለት ነው። ፕሮፌሰር መሳይ ይህን እንዴት እንዳልተረዳው ገርሞኛል። በናይጄሪያ ያደረጉት ይህንኑ ነው፤ ጆናታን ጉድለክ በጄኔራል ሙሐመዱ ቡሃሪ የተተካው በአሜሪካኖች እርዳታ ቦኮሃራምን ለመዋጋር በሚል ነው። ብዙ ሌላ ሐተታ በማቅረብ እንዳላሰለች ጉዳዩን ለማስረዳት የቀረበው በቂ ይመስለኛል። [በነገራችን ላይ የህወሓት ብሎግ ሆርን አፌርስ በእንግሊዝኛ የተረጎሙት ለህወሓት አመቻችተው ነው፤ ጊዜ ካገኛችሁ ትርጉሙን ከአማርኛው ቅጂ ጋር አስተያዩ። አሁንማ የጻድቅቃንን ኢንተርቪው እያሰሙን ነው። ፐብሊክ ሪሌሽንስ ነው ነገሩ፤ ለምርጫ ውድድሩ ፓርቲ ሳይኖር ተጀምሯል!]። ሌላ የሚያሣስበው የነዶ/ር ብርሃኑ መወላገድ ነው፤ ከጻድቃን ባላነሰ ለአገራችን መቅሠፍት ናቸው የሚል ግንዛቤ ላይ ደርሻለሁ። ብትፈቅዱ ይህን አስተያየቴን አትሙልኝ። እኔም ለአገሬ ማሰቤ ነውና፣ ሌሎች ይስሙትና የሚመስላቸውን ግንዛቤ ይውሰዱ። አመሰግናለሁ።
Naji says
Is anybody surprised? As a matter of fact, I am not. The ruling party has to do anything that helps it survive. When things get tougher, one is in a precarious situation feels hopeless anything that gives a twenty-four hours time can be an option. This is obvious, no one should be surprised.
The Ethiopian youth is determined and strongly fighting against a menacing, yet an establishment that has huge force at its disposal and service.
I believe no amount of force will win the determination of the people. To minimize the duration and cost, every effort needs to be coordinated and channeled in an overpowering manner.
The ruling party is weaker than it was a year ago. Those who claim to love their country and fight, need to have a strategy to isolate TPLf from it base support.
We heard that TPLF evcuated Tegray origins from towns and cities. Given the long history of togetheness, and metual respect of Ethiopian people to one another, what does this reaction tells us? Do those evacuated individuals really see danger and voletired?
The ruling party miserably fail to win the hearts and minds of the Ethiopian people. Its support is complitely gone.
The only way out the ruling party sees is to fool the Tegray people once again. The last one was sychological and rhitoric.This time it has show evidence and display. The main intetion of the ruling part is to scare away the Tegray citizens from joining the Ethiopian popular struggle.That is the evacuation all about.
soon or later the evacuatees and Tegray people will know what has been done behind the back.
Tyranny has no compassion and respect to anything, except itself and its bottomless appitiet. Everybody else is either an instrument or a tool. We have seen a lot.