• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ትውልድ አምጿል!”

August 13, 2016 07:39 am by Editor 2 Comments

“ሕዝቡን ካፈንከው እና ከመቃወም ሌላ አማራጭ ካሳጣኸው ይፈነዳል፤ ወጣቱ በሙሉ ዓመጽ ላይ ነው፤ ትውልድ አምጿል”፡፡ “(ትግሉን) በአንድ ጥላ ሥር እያስተባበርን ነው”፡፡

የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጠኛ JEFFREY GETTLEMAN በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ በተነተነበት ጽሁፍ ላይ የጠቀሳቸው ሁለት ግለሰቦች የተናገሩት ነበር ከላይ የሰፈረው፡፡ ጋዜጠኛው ዘገባውን ሲጀምር “ኢትዮጵያ እየተሰነጣጠቀች ነውን” በማለት ይጠይቅና በሁሉም አቅጣጫ ያለውን አመለካከት ያሰፍራል፡፡ (ከዜና ዘገባው ጋር Violent Protests in Ethiopia በሚል ርዕስ የጸጥታ ኃይሎች ሰላማዊ ሰልፍ በወጣ ህዝብ ላይ የሚፈጽሙትን  አሰቃቂ ግፍ እና ጨካኝ ድብደባ እዚህ ላይ መመልከቱ የግድ ይላል)፡፡

“ልማት” አካሂዳለሁ የሚለው ህወሃት/ኢህአዴግ የሕዝብን መሠረታዊ ጥያቄዎች አለመመለሱን የሚያትተው ዘገባ የዓለምአቀፍ ቀውስ ቡድን ተመራማሪ የሆኑትን ራሺድ አብዲ “ይህችን አገር አንድ አድርጎ ወደፊት ለመግፋት ሁልጊዜ አስቸጋሪ” እንደሆነ በመጥቀስ አሁን ለሚታየው ሕዝባዊ ዓመጽ ማብብራሪያ ይሰጣል፡፡

protest 3ኢኮኖሚውን አሳድጌአለሁ የሚለው ኢህአዴግ የሰብዓዊ መብት መግፈፉንም አብሮ እንዳሳደገው የሚናገረው የዜና ትንተና በአገር ውስጥ የሚደረገው አፈና፣ ግድያ፣ እስር፣ እንግልት፣ … በርካታ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ምስክርነታቸውን ሲሰጡበት የቆየ መሆኑን ያስረዳል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚቀርበው አቤቱታ ስፍር ቁጥር የለውም፤ መሬት ከመንጠቅ ጀምሮ የፓርላማ ወንበርን መቶ በመቶ የራስ እስከማድረግ እና የአንድን ቡድን የበላይነት ከፍ እስከማድረስ የዘለቀ ነው፡፡ ይህም በየጊዜው የፈጠረው ምሬት አሁን ያለበት ሁኔታ ላይ እንዲደረስ አድርጎታል፡፡

በኢትዮጵያ የዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ስዩም ተሾመ የተናገሩትን የዜና ዘገባው ይጠቅሳል፤ “ሕዝቡን ካፈንከው እና ከመቃወም ሌላ አማራጭ ካሳጣኸው ይፈነዳል፤ ወጣቱ በሙሉ ዓመጽ ላይ ነው፤ ትውልድ አምጿል”፡፡

ለዚህ አገር አቀፋዊ ዓመጽ ምክንያቶች ናቸው ያላቸውን ሦስት ነጥቦችን ጋዜጠኛው ያነሳል፤

  1. ልባምስልኮች – ዘመናዊዎቹ “ስማርት” ስልኮች (ልባምስልኮች) በርካታ መረጃ በማስተላለፍ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው፡፡ የኢንተርኔት አገልግሎት አገዛዙ እንደፈለገ እየከፈተ የሚዘጋው ቢሆንም እንኳን ወጣቱ ትውልድ እነዚህን ስልኮች በመጠቀም ፎቶ በማንሳት፤ ቪዲዮ በመቅረጽ፤ በማኅበራዊ ድረገጾች በማስተላለፍ መረጃ ይለዋወጣል፡፡ ወጣቶች በነዚህ ስልኮች ግንኙነት በማድረግ ለተቃውሞ ሰልፍ መውጣታቸውን ጋዜጠኛው እማኝ አድርጎ ይጠቅሳቸዋል፡፡protest 1
  2. በአማራና በኦሮሞ ወገኖች በመካከል የተፈጠረው የጋራ እንቅስቃሴ ሌላው ተጠቃሽ ነጥብ ነው፡፡ ህወሃት የሥልጣን ዘመኑን ለማራዘም በሁለቱ መካከል ልዩነትን እያሰፋ የተጠቀመበትና በታሪክ በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለው ቁርሾ በህወሃት አማካኝነት ለተፈጠረው በደል እንዲተባበሩ ምክንያት ሆኗቸዋል፡፡ ሁኔታዎች መቀየራቸውን በመናገር ጋዜጠኛው በኦሮሞ ትግል ውስጥ አመራር የሆኑት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር ሙላቱ ገመቹ “(ትግሉን) በአንድ ጥላ ሥር እያስተባበርን ነው” ማለታቸውን ጠቅሶ የትብብሩን አቅጣጫ ጠቁሟል፡፡ ከኢትዮጵያ ሕዝብ በአናሳነት የሚጠቀሰው የትግራይ ክፍል (ስድስት በመቶ ነው) የአገሪቱን የወታደራዊ፣ የስለላ፣ የደኅንነት፣ የንግድና የፖለቲካ መዘውሩን በእጁ ማስገባቱን በመጥቀስ የግፍ መበራከት ሁለቱን ወገኖች አስተባብሯቸዋል የሚል እንደምታ ይሰጣል፡፡
  3. ህወሃት እንደ መለስ ዓይነት መሰሪ መጣቱ አሁን ለሚታየው ተቃውሞ እንቅስቃሴ ምክንያት እንደሆነ ዘገባው ያስረዳል፡፡ መለስ የሚመጣባቸውን ውድቀትና ጥፋት አስቀድሞ በማየት ወጥመድ ከማዘጋጀት እስከ ማለሳለስ ድረስ የመጠቀም ብቃት የነበራቸው መሆኑን በማብራራት የመለስ ጫማ የሰፋቸው የደቡቡ ኃይለማርያም ደኅንነቱንና ስለላውን በሚቆጣጠሩት ትግሬዎች አመኔታ እንደሌላቸው ይናገራል፡፡

ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ የበለጠ ደም መፋሰስ እንደሚኖርና አሁንም በየማኅበራዊ ድረገጾች እንዲሁም ተቃውሞ በተደረገባቸው አንዳንድ ቦታዎች ከጥላቻ ጀምሮ እስከ ጥቃት የዘለቀ በግልጽ የሚታይ እንቅስቃሴ እንዳለ ጋዜጠኛ ጌትልማን ይናገራል፡፡

የምዕራብ ተላላኪና አሽከር በመሆን በሥልጣን ለመቆየት የበቃው ህወሃት/ኢህአዴግ ከአንጋሾቹ በሚያገኘው ዕርዳታ ዜጎችን መግደሉና መብቶችን ማፈኑ ምዕራባውያንን ባልፈለጉበት ቦታ ላይ አስቀምጧቸዋል፡፡ የህወሃትን አሠራር ለመቃወምም ለመንቀፍም አጣብቂኝ ውስጥ አስገብቷቸዋል፡፡ ዴሞክራሲን መጨፍለቅና ሎሌያቸውን መደገፍ ወይም ፊታቸውን ማዞርና ከህዝብ ጋር መቆም!protest 2

ራሺድ አብዲ ይህ ሁኔታ ምዕራባውያንን “በጣም ቀጭን በሆነ ገመድ ላይ እንዲራመዱ እያደረጋቸው ነው” ማለታቸውን ጠቅሶ ዘገባው ያበቃል፡፡

“የትውልድ ዓመጽ” የሆነው የሰሞኑ የነጻነት ጥያቄ ህወሃትን ብቸኛ እያደረገው እንደሆነ በስፋት ይነገራል፡፡ አፍቃሪ ህወሃት የሆኑ በኦሮሞና በአማራ መካከል ልዩነቶች መኖራቸውን በመናገር አሁንም ልዩነቶችን ለማስፋት የሚደርጉት ሙከራ የበለጠ የመለስን እኩይ ባህርይና “እውነተኛ ውርስ” በግልጽ ያስረዳ እንደሆነ ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡ ከዚህ ሌላ ግን አሁን በኢትዮጵያ የተነሳው የተቃውሞ እንቅስቃሴ በአንድ ፓርቲ ወይም ቡድን የተቀሰቀሰና ለአንድ ፓርቲ የሚገዛ ሳይሆን የሕዝብ ዓመጽ ነው፡፡ አብዛኛዎቹ ደግሞ ህወሃት/ኢህአዴግ ስልጣን በያዘ ጊዜ ህጻናት የነበሩ ወይም ገና ያልተወለዱ፤ ህወሃት ግፍ እየፈጸመ ለዓቅመ ዓመጽ ያደረሳቸው ናቸው፡፡

“ትውልድ አምጿል”!


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Lusif says

    August 14, 2016 05:43 pm at 5:43 pm

    I love your conclusions. Most youths have been born in the last twenty five years and living in misery. They have tried to be part of the system and help build their poor country. Instead they have been pushed away by the group of greedy, corrupt,nepotism system. They have been raising their concern that the ruling party and the government is doing is not right. Instead they have been labeled as, for example, if one is an Oroma his narrow minded, if one is Amahara he is remnants of Derge and feudalism. If one is from Tegray and other regions he is sick and deviant. Shabia puppet, redevelopment and anti peace elements, antidemocratic nationalist chauvinist and the like are some of the names who ask questions and demand answers.
    How long do the ruling party think it can go on like this? It may think for the next fourty fifty years. That is abject madness and collusion with reality.
    The people are speaking. They want their country. Livelihoods, political and economic rights into their hands. Right know every Ethiopian youth is aware that the country belongs to all of them. Everybody thinks that they were misled and regrets the mistakes they have been through.
    The struggle is underway in full scale. There is no Turing back. The objective is to gain the souvernity of the people. The goal is brotherhood, sisterhood, the keeper of each other, living in peace and prosperous life. I hope everything will work out well.

    Reply
  2. አለም says

    August 15, 2016 02:59 am at 2:59 am

    ጎልጉል፤ ጻድቃን በህወሓት ብሎግ ሆርን አፌርስ ስለ ለጠፈው ጽሑፍ ትንሽ ልበል። ሁለቴ በጥንቃቄ አንብቤለታለሁ። በዝብዝቡ መንገላታት አያሻንም። በግልጽ ያስቀመጣቸውን እንመልከት። 1/ ስለ ኢትዮጵያ ሁኔታ ከጓደኞቼ ጋር ተመካክረን ነበር ብሎናል፣ ጓደኞቹ እነማን እንደሆኑ ግልጽ ነው 2/ ስለኢትዮጵያ የነገረን የማናውቀውን አይደለም፤ ህወሓትን አሳጥቶ መጻፉ ለአንዳንዶች አስገራሚ መስሎ ይታይ ይሆናል። ጉዳዩ ግን፣ ህወሓት በራሱ ሊለው የማይችለውን ተመካክረው እያለላቸው ነው 3/ ምርጫ ይኑር፣ የምርጫ ውጤት ለመቀበል ፈቃደኛ መሆን አለብን ብሎአል 4/ የርሱ ሃብት ማካበት በራሱ ጥረት እንደሆነ ሊያሳምነን ሞክሯል 5/ ስዬን ጠቅሷል 6/ የኢትዮጵያን ሠራዊት በትኖ የህወሓትን መተካቱን በወቅቱ “National defense and economic development”ብሎ ያቀረበውን ሰነድ ቆንጽሎ ሙሉውን ሰነድ ሊደብቀን ሞክሯል 7/ ዛቻ ብጤም አሰምቷል፤ ካለዚያ ደም በደም እንሆናለን ብሎ። ድምዳሜዬ? 1/ የህወሓት አካሄድ እንደማያዋጣ ተረድቷል፤ ስዬ እንደሞከረው [ትዝ ይልሃል? አንዴ እስር ቤቱ ኦሮምኛ ይናገራል ያላትን?] 2/ ደቡብ ሱዳን ላይ ለአሜሪካኖች ዓላማ አስተባባሪ ሆኖ እየሠራ ነው፤ ስዬ ምዕራብ አፍሪካ ላይ። 3/ ህወሓት ከመለስ ሞት በኋላ መስማማት ስላልቻሉ ኃ/ማርያምን አስቀምጠው ካብ ለካብ እየተያዩ ነው፤ “ኮሌክቲቭ ሊደርሽፕ” በሚል ማጭበርበሪያ ኃ/ማርያምን ደብረጽዮን፣ በረከት፣ አባይ፣ ብርሃነ ገ/ክ ገንዘቡን ሥልጣኑን ተቀራምተውታል፤ አንዱ ችግር ይኸው ነው። አሜሪካኖች የችግሩን መጠን ያውቁታል፤ አታላይነቱ ስለገባቸው የመለስ መወገድ እረፍት ሆኗቸው ነበር፣ አሁን ደግሞ የዋለለ ጉዳይ እንዲቀጥል አይፈልጉም። ህወሓት ሶማሌን፣ ደቡብ ሱዳንን በኢትዮጵያውያን ደም እየነገደ አመቻችቶላቸዋል። ይህን ነገር መፍትሔ ስጡ እያላቸው ነው። የወገኖቻችን ደም መፍሰስ ምንም ያልመሰለው ለዚህ ነው። በተባበሩት መንግሥታት ጸጥታ ጉዳይ ኢትዮጵያ ወንበር ያገኘችው በአሜሪካና በእንግሊዝ እርዳታ ነው። አሁን የሚፈለገው ጻድቃን [ወይም ስዬ] እንደ ታዳጊ ቀርቦ የአሜሪካኖችን ዓላማ ያስፈጽማል፤ በዚያውም የህወሓትን የበላይነት ይታደጋል ማለት ነው። ፕሮፌሰር መሳይ ይህን እንዴት እንዳልተረዳው ገርሞኛል። በናይጄሪያ ያደረጉት ይህንኑ ነው፤ ጆናታን ጉድለክ በጄኔራል ሙሐመዱ ቡሃሪ የተተካው በአሜሪካኖች እርዳታ ቦኮሃራምን ለመዋጋር በሚል ነው። ብዙ ሌላ ሐተታ በማቅረብ እንዳላሰለች ጉዳዩን ለማስረዳት የቀረበው በቂ ይመስለኛል። [በነገራችን ላይ የህወሓት ብሎግ ሆርን አፌርስ በእንግሊዝኛ የተረጎሙት ለህወሓት አመቻችተው ነው፤ ጊዜ ካገኛችሁ ትርጉሙን ከአማርኛው ቅጂ ጋር አስተያዩ። አሁንማ የጻድቅቃንን ኢንተርቪው እያሰሙን ነው። ፐብሊክ ሪሌሽንስ ነው ነገሩ፤ ለምርጫ ውድድሩ ፓርቲ ሳይኖር ተጀምሯል!]። ሌላ የሚያሣስበው የነዶ/ር ብርሃኑ መወላገድ ነው፤ ከጻድቃን ባላነሰ ለአገራችን መቅሠፍት ናቸው የሚል ግንዛቤ ላይ ደርሻለሁ። ብትፈቅዱ ይህን አስተያየቴን አትሙልኝ። እኔም ለአገሬ ማሰቤ ነውና፣ ሌሎች ይስሙትና የሚመስላቸውን ግንዛቤ ይውሰዱ። አመሰግናለሁ።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule