* “ብልጡን ባለ ራዕይ መሪ” ክፉኛ ናፍቋል!
የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር /ህወሃት/ አመራሮች ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ከመግደልና ከማስገደል እንዲታቀቡ ታዘዋል። ግድያው የሚቀጥል ከሆነ ከወትሮው በተለየ ርምጃ እንደሚወሰድ ተነግሯቸዋል። “ወልቃይትን ለባለቤቱ ህዝብ ብንመልስ ይሻላል” በሚሉና “አንመልስም” ሲሉ በሚቃወሙ መካከል ክርክር የጀመረው ህወሃት ስምምነት ሊደርስ አልቻለም። ሁኔታው መለስን ከመቃብር ቀስቅሷል።
አባይ ጸሃዬ፣ ሳሞራ የኑስና ሌሎች ባለስልጣናት አሜሪካ እንደነበሩ ለጎልጉል ጠቁመው የነበሩት የመረጃው ምንጮች እንዳሉት ባለስልጣናቱ ግድያ እንዲያስቆሙ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ተቀብለዋል። በአማራ ክልል የተነሳው ተቃውሞ ያሳሰበው ህወሃት በተመሳሳይ አሜሪካ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወደ ሰላማዊ ድርድር እንዲመጡ ጫና እንድታደርግ ጠይቀዋል። ለዚህም ይመስላል በአሜሪካ በኩል የተቀናቃኝ ድርጅት መሪዎችን በተናጠል ማነጋገር ተጀምሯል።
ህወሃት በግድያው ከገፋበት ከአሜሪካ በኩል የሚሰጠው ምላሽ እንደ ወትሮው በኤምባሲ ወይም በህዝብ ግንኙነት በኩል እንደተለመደው “ጉዳዩ አሳስቦናል” የሚል ተራ መግለጫ እንደማይሆን ማረጋገጫ መሰጠቱን ጎልጉል የሚያምናቸው የዲፕሎማት ምንጮች ከአሜሪካ ተናግረዋል። እንድ መረጃ አቅራቢዎቹ ቀጣዩ የአሜሪካ አቋም በውጭ ጉዳይ መ/ቤቱ (ስቴት ዲፓርትመንት) ዋና ኃላፊ ወይም ከፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት (ኋይት ሃውስ) በኩል የሚተላለፍ እንደሚሆን ይጠበቃል። ባለፉት ሳምንታት ግማሽ ያህል የህወሃት ባለስልጣናት አሜሪካ ደርሰው መመለሳቸውን ለስርዓቱ ቅርብ የሆኑ ሌላ ዜናን ለማስተባበል ሲሞክሩ ሳያስቡት ማረጋገጫ ሰጥተዋል።
በሌላ ዜና በህወሃት ውስጥ “ወልቃይትን መመለስ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው” በሚሉና “ሊመለስ አይገባም” በሚል የሃሳብ ልዩነት መፈጠሩ ታውቋል። የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ምንጮቹን ጠቅሶ እንዳለው በዚሁ ጉዳይ የተሰየመው የህወሃት አመራሮች ስብሰባ ለቀናት ቢወያይም ስምምነት ላይ ሊደርስ ግን አልቻለም።
“ወልቃይትን እንመልስ” ባዮቹ ወገኖች አማራ ክልል የተነሳው ተቃውሞ አስፈሪ፣ የከረረ፣ እስከወዲያኛው ለስልጣናችን የሚያሰጋ ስለሆነ ወልቃይትን መልሶ አገሪቱን ማረጋጋት የግድ ነው ይላሉ። “ወልቃይትን መመለስ የለብንም፣ እንዴት ተደርጎስ ይመለሳል? ውርደት ነው” በሚል አቋም የያዙት ደግሞ ሁለት መከራከሪያ አላቸው።
እንደ ዘጋቢያችን መረጃ ከሆነ እነዚህ ክፍሎች ሁለት ነጥቦችን በማቅረብ የተከራከሩት “አንመልስም፣ ከመለስንም መሰረተ ልማቱንና ያፈራነውን ሃብት ምን እናደርገዋለን?” በሚል ጥያቄዎች የታጀቡ ናቸው።
“ወልቃይት የኖሩት ወገኖቻቸን ሃብት አፍርተዋል። ለማን ነው ጥለውት የሚሄዱት?” የሚሉት እነዚህ ወገኖች አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ/ሃይል በመጠቀም በተጀመረው መንገድ መቀጠል እንዳለበት የሚመኙ ሲሆኑ፣ ምኞታቸው ካልተሳካ መሰረተ ልማቱን በሙሉማፈራረስ ሌላው የመጨረሻ ውሳኔያቸው ነው።
በዚህ ሁለት ሃሳብ የሚነታረከው የህወሃት አመራሮች ስብሰባ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ዕለት ድረስ ከውሳኔ ላይ አልደረሰም። ይሁንና በዚህ ውሳኔ ላይ እንደ ከዳ የሚነገርለት ብአዴን አቋሙ እንዲጠየቅ አልተደረገም።
ህወሃት ለረጅም ዓመታት በተለያዩ መንገዶች ሲያፍን የቆየው የሕዝብ ዓመጽ በአገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች መፈንዳቱ ሥርዓቱን ክፉኛ አናግቶታል፡፡ በፓርቲ ወይም በድርጅት ሳይመራ በሕዝብ እምቢተኝነት የገነፈለው ተቃውሞ በስልትና በግለት እየጠነከረ መምጣቱ ህወሃት የመግደል እርምጃ እንዲወስድና ከምዕራባዊ ጌቶቹ ጋር እንዲቃቃር እያደረገው ነው፡፡ በሥልጣን መቆየት በአንድ በኩል፤ በሌላ ደግሞ ከምዕራባውያን ጋር ስሙም መሆን የወጠረው ህወሃት ከዓቅሙ በላይ የሆነው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ከቀን ወደ ቀን እያየለበት በንጹሃን ላይ ጥይት መተኮሱን አላቆመም፡፡
ይህ አካሄድ ህወሃትን ለክፍፍል እንደሚዳርገው ከተለያየ አቅጣጫ ይነገራል፡፡ ለዘመናት ህወሃትን ስትንከባከብ የነበረችው አሜሪካ በተወሰነ መልኩ ጉዳዩን የማክረር ሁኔታ ይታይባታል፡፡ የአሜሪካንን ፖሊሲ የማስቀየር አቅም ያላቸው ጋዜጦች ኢትዮጵያ በአናሳዎች የምትመራ ከዴሞክራሲ የራቀች አገር መሆኗን እንደ አዲስ ለፖለቲከኞቻቸው እያስተዋወቁ ነው፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ነጻ አካል ምርመራ እንዲደረግ የተደረገውን ውሳኔ ህወሃት አልቀበልም ባለ ወቅት በመንግሥታቱ ማኅበር የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ሰማንታ ፓወር ህወሃት “ነጻ ምርመራውን መቀበል አለበት” በማለት በትዊተር የከረረ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
መጪው ጊዜ የከፋ እንደሚሆን የገመቱ፣ ለዘብተኛ ለመሆን የሚፈልጉና በሃብት የደለቡ የህወሃት ሰዎችና አሽከሮቻቸው “በጥገናዊ ለውጥ” ሁኔታዎች እንዲረግቡ ይፈልጋሉ፡፡ ምዕራባዊ አገራት በመቆየት ዘምነናል የሚሉና የምዕራባውያን ድጋፍ እንዳላቸው በተለያየ መልኩ የሚጠቅሱት በዚህ ውስጥ ይካተታሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ህወሃት/ኢህአዴግ ከየቦታው የሰበሰባቸውና በየአገሩ ተወካይ (አምባሳደር) አድርጎ ያስቀመጣቸው ተላላኪዎቹም ይገኙበታል፡፡ እነዚህ ክፍሎች በራሱ በህወሃት ከረከሰው ሽምግልና እስከ ዕርቅ ለመሄድ የሚጥሩትንም ይጨምራል፡፡ ብንከስርም ወልቃይትን ለባለቤቱ እንመልስ ባዮቹ የዚህ ዓላማ አራማጆች ናቸው፡፡ የነዚህ ተቃራኒዎች ማሸበርና መግደል በመቀጠል “ካልገዛን እንሞታለን” ብለው ህወሃትን ከጌቶቹ ከማቃቃር እስከ “አሜሪካ ከከፋት ጉዞ ወደ ቻይና” የሚሉ የተሰባሰቡበት ነው፡፡ የበረሃ ገድላቸውን እየጠቀሱ “ደጋፊዎቻቸው” ጠብመንጃ እንዲወለውሉ የሚቀሰቅሱና “ሪፓብሊካቸውን” በአየር ኃይል ጭምር ለመከላከል የወሰኑ በዚህ ምድብ ውስጥ ተከማችተዋል፡፡
የእነዚህና ሌሎች ኃይላት ትንቅንቅ ህወሃትን አደገኛ ፈተና ውስጥ እንደጣለው ይነገራል፡፡ አራት ዓመታት በሙት መንፈስና ሌጋሲ ሲመራ የቆየው ህወሃት/ኢህአዴግ ታዛዥነት፣ መደማመጥና “ብልጠት” ጠፍቶበት “ባለ ራዕይ መሪውን” ክፉኛ ናፍቋል፡፡
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
Habtegebriel says
The only option TPLF has ..to give back the area to the Owners(Gonder) Province..unless it would be the end of Tplf.
ባይሳ says
ወያኔ የበረሃ ፖለቲካና ሀገር ሲመራ የሚኖረው የፖለቲካ አመራር በአይነቱም በይዘቱም የተለያየ መሆኑን ለማወቅ አስቸጋሪ እንዳልሆነ ሳይገባው የቅረ እይመስለኝም።ህዝቡ በቃኝ ብሏል።ትግሉ እየጠነከረና እየመረረ ነው።የወያኔ አመራሮች በጭፍን አስበው የታጠቀ ሀይል አለን ትግራይን ገንጥለን እንጓዛለን ማለት እሳት እንደመጨበጥ ነው።አስታራቂ የሚሆነው የሽግግር መንግስት ማቋቋም ወይም ስልጣን ለህዝብ ማስረከብ ብቻ ነው።ህዝብ እየገደሉ መቀጠል ያረጀ አስተሳሰብ ነው።
Habesha says
Now it is time to return Wolkayit to its original administaration Gondar. Else this will bring end to TPLF for ever. and You can not eat what you collect during the last 25 years peacefully. Stop killing Ethiopians. stop stop.
Tadesse says
Choose from,Meles Zenawi and all that propaganda that brings only slavery and Jesus Christ and freedom.It might take time but the devilish system will be eradicated from Tigray totally,I have a dream.
tesfai habte says
የወያኔ የዲቃላ ስብስብ መንግስት እንኳንስ ለኢትዮጵያ ለትግራይም የማያስብ፡ ለራሱ ብቻ ብደስታ ለመኖር የሚራራጥ፡ የኣመሪካን ወይተር (ተላላኪ) ኢሰብኣዊ ተግባር ለመስራት ብቻ ደስ የሚያሰኘው ፍጡር ነው።
Rural news says
By next week there will be no more protests and cyber zeraf-zeraf.
the gonderes,gojames and oromos are all saying ,the people of AA are not taking any action (protest or strike) while the farmers sacrifice
their lives.one man from gojam said,resentfully,people in Addis Ababa were shopping and partying when the people of gojam were facing wayane bullets.why don’t they show their solidarity by closing markets,shops and staying at home?
Addis Ababa being the diplomatic capital of Africa,any strike by students,workers,bus and taxi drivers,traders,etc will be a big blow to woyanes.by the look of things the current sporadic protests will just fizzle out soon for the delight of woyanes.
Atamam says
That will be the next step, sir! It’s coming, trust me.
mitima says
Unless a few blood sucking evils need the chaos and violence to kill innocent ethiopians the wolkayt issue is simple. let the people vote to remain or leave tigray region. Even UK vote for brexit. by the way it isnt wealth or any infrastructure development makes it difficult to give up wolkayte for the tplf. Azeb Mesifine is the one who is messing up things cause she will be out of tplf. And more than 70percent of TPLF will be more than happy to see that day if it wasnt for meles it wasnt take all this long to return wolkayt to amhara region and kick out azeb. Imagine Azeb Mesifin joining the amhara party Biaden…..
mertcha says
When the time comes for the Wolqayit region to be returned to Gonder administration, the ethnic Tigrayans who are already settled in Wolqayit should remain there with their Amhara brothers and sisters. Ethnic crimes like those in Gura Ferda and Beni Shangul should never ever occur again. Ethiopians should be able to live peacefuly in any region of their choice. The ugly word of the Woyanes, “kilil”, and the whole “kilil system” should be abolished once and for all! With the help of God, the era of the corrupt and brutal killers seems to be advancing to its very end!