• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የነፍጠኞች ፖሊቲካ

August 2, 2016 05:08 am by Editor 6 Comments

ነፍጠኛነት ባህላችን ነው፤ ፖሊቲከኛነት አዲስና ባዕድ የትግል ዘዴ ነው፤ ፖሊቲከኛነትና ነፍጠኛነት ተቃራኒ ተግባሮችን ያመለክታሉ፤ ተቃራኒ ተግባሮች አብዛኛውን ጊዜ ተቃራኒ ዘዴዎች ያስፈልጋቸዋል፤ ለምሳሌ መፍጨትና መቡካት ተቃራኒ ተግባሮች ናቸው፤ መፍጨት ሲበታትን፣ ማቡካት ሰብስቦ ያያይዛል፤ የሚፈጭ ሰው ማቡካት ይችላል፤ እንዲሁም ማቡካት የሚችል ሰው መፍጨት ይችላል፤ ፈጪ አቡኪ መሆን የሚችለውን ይህል ወይም አቡኪ ፈጪ መሆን የሚችለውን ያህል ነፍጠኛ ፖሊቲከኛ ወይም ፖሊቲከኛ ነፍጠኛ መሆን ይችላል ወይ? መልሱ ግልጽ ነው፤ አይችልም፤ የነፍጠኛ ትግል በጠመንጃ ነው፤ የፖሊቲከኛው ትግል በቃላት፣ በንግግር ነው፤ በሌላ አነጋገር የነፍጠኛ በዱላ፣ የፖሊቲከኛ ትግሉ በመላ ነው፡፡

የፖሊቲካ ሥልጣንን ነክሶ ይዞ ሕዝብን በሕዝብ በዱላ እያደባደቡ በማሸነፍም ሆነ በመሸነፍ የሥልጣንን ክብር ማግኘት በጭራሽ አይቻልም፤ በዱላ ትግል በሁለቱም ወገን ያሉ ወጣቶች ይጎዳሉ፤ በተሸናፊው በኩል የተሰለፉ ወጣቶች የመረረ ኑሮአቸውን የሚጀምሩት ወዲያው ነው፤ መቃብራቸውም ሆነ ቁስላቸው ክብር የለውም፤ የየግሉ አበሳና ለቅሶ ሆኖ ይቀራል፡፡

በድል አድራጊው በኩል የተሰለፉ ወጣቶችም ቢሆኑ ማርና ወተት የሚያገኙት በጣም ጥቂቶች ናቸው፤ አብዛኛዎቹ ያለ ማጋነን ዘጠና በመቶ የሚሆኑት ጠመንጃ ተሸክመው በወገናቸው ደረት ላይ ሳንጃ ደቅነው እየወጉና እያሰቃዩ በየዕለቱ ከርሳቸውን ለመሙላት ያለፈ ኑሮ የላቸውም፤ ወይም እውነቱን ፍርጥ አድርጎ ለመግለጽ ዘጠና ከመቶ የሚሆነው ከአሸናፊው ወገን ያለ ወጣት አሥር ከመቶ ለሚሆነው አሽከር ወይም ሎሌ ሆኖ ወገኑን በስቃይ እየጠበሰ ለሆዱ የሚያድር ይሆናል ማለት ነው፡፡

አብዛኛውን አሸናፊንም ሆነ ተሸናፊውን የሚያዋርደው ወይም ክብርን የሚነሣው የአሸናፊና የተሸናፊ ትግልም ሆነ የትግሉ ውጤት ከአብዛኛው የአገሩ ሕዝብ ፈቃድ ውጭ የተደረገ የጉልበተኞች ግብግብ ነው፤ እንዲህ ያለ ግብግብ የሚደረገው ከሕዝቡ ጋር ሳይሆን በሕዝቡ ላይ ነው፤ ሁለቱም ተደባደቢ ወገኖች የሕዝብ ወገን መስለው ለመታየት ይሞክራሉ፤ ሆኖም ተፎካካሪዎቹ እርስበርሳቸው የሚታገሉት በዱላ እንደሆነ ሁሉ ከሕዝብም ጋር ያላቸው ግንኙነት በዱላ ነው፤ የሁለቱም መሠረታዊ እምነትም ሆነ ዓላማ፣ መሣሪያም ሆነ ዘዴ ዱላ ብቻ ነው፤ እንዲያውም አንዳንዴ ዱለኛነታቸው ድንበር እየጣሰ የሌሎች አገሮችን ሉዓላዊነት ይነካል፤ በዛሬው ጊዜ በዓለም ውስጥ ዋና ዱለኛ አገር አሜሪካ ነው፤ በሱ ጥገኝነትና በሱ ጥላ ስር ያሉ አምባ-ገነን አገዛዞች በበኩላቸው ዱለኛነትን ይለምዳሉ፡፡

የሕዝብን የገነፈለ ዓመጽ ከዱለኛነት ጋር እንዳናዛምደው ጥንቃቄ ያስፈልጋል፤ አንድ ሕዝብ በማይሰማ ደነዝ አገዛዝ ውስጥ ለብዙ ዓመታት ሲቆይ ተደብቆ የነበረው ሁሉ ገሀድ ይወጣል፤ በእንግሊዝኛ አንድ የአነጋገር ፈሊጥ አለ፤ የግመሉን ወገብ የሰበረው ሰንበሌጥ ይባላል (the straw that broke the camel’s back)፤ ሰንበሌጥ በእውነት የግመልን ወገብ የመስበር አቅም ኖሮት አይደለም፤ ነገር ግን ጭነቱ ተከምሮ፣ ተከምሮ በመጨረሻ የግመሉ ወገብ ሊሸከመው የማይችለው ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ የሚጨመር ሰንበሌጥ የተከመረውን ሸክም ከመጠን በላይ ያደርገውና የግመሉን ወገብ ይሰብረዋል፡፡

አበሳና ግፍም ከዓመት ዓመት እየተከመረ፣ ኑሮ እየከረረ፣ ከሞት ይልቅ ስቃይ እየመረረ፣ የግመሉን ወገብ እንደሰበረው ሰንበሌጥ ለዘመናት በሕዝብ ላይ በተከመረ ግፍ ላይ አንድ ግፍ ጣል ማድረግ የግፍ ግንፋሎትን ይፈጥራል፤ ትእግስት ይደርቃል፤ ጨዋነት ዋጋ ያጣል፤ እንኳን ሰው ድንጋይም ይገነፍላል፤ እሳተ ገሞራ የሚባለው በመሬት ውስጥ ያለው ድንጋይ ሙቀት ሲበዛበት እየቀለጠ መሬትን ሰንጥቆ ሲገነፍል ነው፤ ሕዝብም እንዲሁ ነው፤ ግፍ ሲበዛበት፣ ዙሪያው ገደል ሲሆንበት ይገነፍላል!

መገንፈል በሞት ውስጥና በሞት መሀከል መተራመስ ነው፤ ልዩ ኢላማ የለውም፤ በመንገዱ ላይ የሚያገኘውን ሁሉ ይጠብሳል፤ ሀሳብም፣ ስሜትም የለበትም፤ንዴት ብቻ ነው፤ አደጋውም ያለው እዚያ ላይ ነው፡፡

ሐምሌ 2008

(ምንጭ: Mesfin Wolde-Mariam Blog)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions, Politics Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. koster says

    August 3, 2016 12:28 pm at 12:28 pm

    le lijochachin miker new Prof. 23 years is more than enough. No fascist in world history transferred power freely and willingly. Unfortunately, the fascists from TIGRAI will not transfer power freely and willingly since they know they will loose a lot. Bloodshed is inevitable unless we are preaching slavery.

    Reply
  2. Tabor says

    August 4, 2016 05:25 am at 5:25 am

    Professor, we know that you believe in peaceful struggle. You have been preaching that noble policy for 25 years. But Woyane neither understands nor believes in your way. What Woyane knows is ruling the country with an iron hand till dooms day. Unfortunately, Professor that day is coming soon. The poor does not loose any thing. The big looser is Woyane with his clicks, who controlled this beautiful country for a quarter of a century, upon the demise of the Derg.

    Reply
  3. አቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ says

    August 6, 2016 01:11 pm at 1:11 pm

    የተከበሩ እና የተወደዱ አባታችን ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም።
    “የነፍጠኞች ፖለቲካ” የተሰኘችውን እና በተለያዩ ድህረ ገጾች የጦመሩትን አነበብኩ።ፕሮፌሰር እዚህ’ጋ ጥያቄ አለኝ የሚባልበት ወቅት ላይ ባለመሆናችን ተገቢ አይደለም ብዬ ማስረጃዬን በትህትና አቀርባለሁ።
    እኔ ያለኝ ቅሬታ ከመሠረታዊ ጽሁፍዎ ነው።የነፍጠኝነትን ባሕላችን መሆን ከገለጹ በኋላ፤በዚሁ አንደኛው አንቀጽ መግቢያ ላይ “ፖሊቲከኛነት አዲስና ባዕድ የትግል ዘዴ ነው፤”***ፖለቲካን*** ግን በምን ዓይነት የተሳሳተ ትርጉም እንደወሰዱት ባይገባኝም ለአገራችን ኢትዮጵያ እንደ አዲስ ፥”አዲስና ባዕድ የትግል ዘዴ ነው፤”በማለት ትንተናዎትን {ወደ አልተፈለገ የእርስ በእርስ ጦርነት እንዳናመራ} በሚል ስጋትዎትን ይገልጻሉ።
    በመሠረቱ ፖለቲካ ማለትን ለእርስዎ ለማስረዳት ሳይሆን አንባቢውም የሰፋ ግንዛቤ ይጨብጥ ዘንድ፣ውክፔዲያ ሲተርጉመው:-“ፖለቲካ የሚለው ቃል ከግሪኩ πολιτικος («ዜጋ») ከሚለው ቃል የመጣ ነው። በአሁኑ ወቅት ፖለቲካ ማለት በቡድን ያሉ ግለሰቦች የጋራ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሚያስችላቸው ሂደት ነው። በዚህ ምክንያት ምንም እንኳ ፖለቲካ የሚለው ቃል ብዙ ጊዜ ከሃገርና ከመንግስት ጋር የተገናኘ ቢሆንም በሌላ አንጻር የሰው ልጆች በቡድን ሆነው በሚገኙበት ማናቸውም ስብስብ ይገኛል፣ ለምሳሌ በኩባንያወች፣ በትምህርት ቤቶች፣ በሃይማኖት መዋቅሮች፣ በቤተሰቦች ውስጥ ሳይቀር ፖለቲካ አለ። የኃይል አመዳደብ፣ የቁጥጥር፣ የውሳኔ ላይ መድረስ፣ የምጣኔ ሃብት ክፍፍል ጥያቄወች በሁለትና ከዚያ በላይ ባሉ ሰወች መካከል ሲነሱ ያንን ጥያቄ ለመፍታት በሚደረግ ሂደት፣ በዚያ ፖለቲካ አለ። ከዚህ አንጻር በአንዳንዶች አስተሳሰብ አብዮት፣ ጦርነት፣ ማህበረሳባዊ ግጭት ፖለቲካ ሳይሆኑ የፖለቲካ ሂደቱ ክሽፈት ናቸው። በሌሎች አስተያየት እኒህም የአጠቃላይ ሂደቱ አካል ስለሆኑ እንደ ፖለቲካ ይወሰዳሉ።ፖለቲካን የሚያጠናው የትምህርት አይነት የፖለቲካ ሳይንስ ወይም የፖለቲካ ጥናት ይባላል።” ይላል።ከዚህች ትርጉም በተጨማሪ እነፕሮፌሰር ያስተማሩንን ጨማምረን ለኢትዮጵያ “ሥነ-መንግሥት ወይም ኪነ-ሥልጣን”ፖለቲካ አዲስ እንዳልሆነ ግልፅ ተጨባጭ ነው።
    እናም ለነዚህ ችግሮቻችን ዕውቀቱም ቀድሞም ስለነበረን በነፃነታችን ለሦስት ሺህ ዓመታት መኖራችን ታሪክ የሚያውቀው ሐቅ ነው።ለፖለቲካ የምንሰጠው ትርጉም እንደዘመኑ የምንፈታው ከሆነ ሁሉንም ነገር <> ያለፈው ትውልድ ሊፈታው ይገባል።ከተፈጥሮ አንጻር ላብራራው የትኛውም እንስሳ ይሁን አውሬ ሰውን ጨምሮ የተፈጥሮ መከላከያ የሌለው የለም።ጥይት’ኮ ያለባሩድ ድንጋይ ብቻ ነው።ፖለቲካ ደግሞ በልሳን የሚደረግ የሰው ልጅ መግባቢያ አንዱ የዕውቀት ዓይነት ይሁን እንጂ በራሱ ጥንካሬ እንደፈለጉት በጊዜና በቦታ ምርጫ የሚጓዝ አይደለም፤ለዚህ ነው ኃይል የሚያስፈልገው።መቶ በመቶ እርግጠኛ ነኝ፤ፕሮፌሰር ለዚህ አባባሌ ብዙ መረጃዎችን ማቅረብ እንደሚችሉ።አለበለዚያ ለሃያ አምስት ዓመታት “ጅቡ እየቆረጠመኝ ስለሆነ ዝም ብላችሁ ተኙ”በሉንና እርፍ ይበሉት።እኔ ግን አቅሜ በፈቀደ ሁሉ ይህን የዘረኛ ጉጅሌ ቡድን ተዘርጥጦ እስኪወድቅ ትግሌን አላቆምም።በመሳሪያ መፋለሙን ዛሬ ሳይሆን በጠዋቱ ነው የደገፍኩት፤ለምን ቢባል እኔ እዚያው ትግራይ ውስጥ”ወያኔን”ያሁኑ ጉጅሌን ኖሬና የስነልቡናቸውን ሁኔታ ቢያንስ ለሁለት ዓመታት ተቀምጬ ነው ያወቅኳቸው።ለዚህም በሥነ ግጥም ሰሚ ካለ ብዬ የወገርኩበትን “ትርጁማን ፈልጉ” ብዬ የወገርኩበትን ተቃመሷት።”ጉጅሌ” ከወደቀም በኋላ ቂጡ ተገልቦ ታሪኩን ከማጋለጥና ተዋንያን የነበሩትን ከማስለቀም እና ተመጣጣኝ የደም ክፍያ እንዲጠየቅ ከማድረግ አልመለስም።
    ነፍጠኛ ተባለም አልተባለም ፕሮፌሰር መስፍን ወ ማርያም እንደ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ ሽምግልና አውቃለሁ ብዬው ብቅ ጥልቅ እያሉ ብቻ የማይፈታ ሃሳብ መሰንዘሩ ተገቢ አይመስለኝም።ይልቅ ተሰሚነትና አመኔታ የሚጣልብዎ ኢትዮጵያዊ አባት ስለሆኑ ይበልጥ ሊያስተባብሩ የሚያስችል ሃሳብ ሊሰጡ በተገባ ነበር ባይ ነኝ፤በዚህ የዕድሜ ፀጋ ድካምዎ ላይ።እግዚአብሔር ዕድሜና ጤና እንዲሰጥዎትና የኢትዮጵያን የመጨረሻ መጀመሪያውን ያሳይዎ ዘንድ በጸሎት አልረሳዎትም።

    ?? ሊበላ የመጣ ጅብ…???
    xxxxxxxxxxxxxxxxxxxxx
    ሃያ አምስት ዓመታት እየተነገረው፤
    የሰው ደም ሲጠጣ ዛሬም ለሚኖረው፤
    በመግለጫ ብዛት ያቆማል የሚል ሰው፤
    አውቆ የተኛን ክፉ እንደመቀስቀስ ነው።
    ምን ዓይነት ዕብድ ነው”ታጋይ” ነኝ እያለ፤
    ሕዝብ በግፍ ሲገደል 
    ሞቱን ያቀለለ???
    በጉጅሌ አገዛዝ ኑሮ ያልመረረው፤
    ወያኔ አለዚያም ባንዳነት ያደረው፤
    ካልሆነ በስተቀር ሌላው ኢትዮጵያዊ፤
    በቅስፈቱ አልታየም ከመለስ ዜናዊ? ? ?…
    እኮ መልሱን ስጡኝ እኔም ላዳምጣችሁ፤
    በምን ቋንቋ ቢሆን ሕዝብን ታምናላችሁ???
    ወይስ በትርጁማን ጉጅሌው በሚያውቀው፤
    በበባዕድ መሳሪያ ክንዱን በሚያደቀው?
    በሚያርበደብደው በሕዝብ-አመፅ ትግል፤
    ቆርጠን ካልጀመርነው:-
    አይገኝም “ያ!!!” ድል!!!
    የቻለም በቻለው:-
    ያልቻለም በሚያውቀው፤
    በጠንካራ ክንዱ:-
    ጠላት በሚያደቀው፤
    በአንድነቱ አብሮ መግቢያ ካላሳጣው፤
    ዛሬም አይማርም 
    ባይቀጡ ካልቀጣው።
    ርኩስ ነው ጉጅሌ ደደብ የማይገባው፤
    ከፋሺሽት ተወልዶ ባንዳነት የጠባው።
    ቋንቋውን ያጠና ልሣኑን ያወቀ፤
    በተጠንቀቅ ላይ ነው ቀን እየጠበቀ።
    ምን አልጋ ቢነጠፍ ምን ቢለማመጡት
    ሊበላ የመጣ ጅብ አይጠግብም ቢሰጡት::
    በሚያርበደብደው በሕዝብ-አመፅ ትግል፤
    ቆርጠን ካልጀመርነው:-
    አይገኝም “ያ!!!” ድል!!!

    XXXXXX ooo <> ooo XXXXXXXXX

    ሱዳንስ ያውቀናል በቅርቡ በሩቁ፤
    ይብላኝ ለነሐጎስ:-ለነትግል ብርቁ።
    ከዛሬ በስተቀር ነገን ለማያውቁ፤
    በብረት ጀግነው ለተጨማለቁ።
    የትግራይ ምንደኞች እየተሳሳቡ፤
    በባንዳ አመላቸው
    ሊሸጡን ካሰቡ ?
    ኢትዮጵያዊ ስማ ልብህ አያመንታ
    መሀል ዳር ይሆናል ዳሩ ከተፈታ ።
    ስለዚህ <> ይሁን መዳረሻው፤
    ለኮሶ መድኃኒት ኮሶ ነው ማርከሻው።
    ትመር እንደሆነ፣ ምረር እንደኮሶ፤
    ትመሪ እንደሆነ፣ ምረሪ እንደኮሶ፤
    ጠላት ካልደቆሱት አይጠፋም ጨርሶ፤
    ሕሊናም አይፀዳም በዕምባ ታብሶ።
    እናም አንጀት ቆርጦ፤
    ልብ ውስጡን ቢደማም፤
    ሕሊናን ካልጸዳ፣ነፃነት አይሰማም።
    እስኪ ለነጋችን ዛሬን እንኳን ንቁ፤
    ከእባብ እንቁላል የዕርግብ አትጠብቁ።
    እናም መራር ትግል፣ከኮሶ የመረረ፤
    እስትንፋስ ሕላዌን በሰብ ካልቀመረ፤
    በነፃነት ሕይወት መኖር ካልጀመረ፤
    ጠዋትና ማታ ባርነት ካደረ፤
    ምኑን አለሁ ይላል፣ሞተ እንጂ በቁሙ፤
    ተስፋውን ሲገድሉት፣ሕልሙን ሲያጭልሙ፤
    ስለዚህ <> ይሁን መዳረሻው፤
    ለኮሶ መድኃኒት ኮሶ ነው ማርከሻው።

    Reply
  4. አቢይ ኢትዮጵያዊ says

    August 6, 2016 01:30 pm at 1:30 pm

    የተከበሩ እና የተወደዱ አባታችን ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም።
    “የነፍጠኞች ፖለቲካ” የተሰኘችውን እና በተለያዩ ድህረ ገጾች የጦመሩትን አነበብኩ።ፕሮፌሰር እዚህ’ጋ ጥያቄ አለኝ የሚባልበት ወቅት ላይ ባለመሆናችን ተገቢ አይደለም ብዬ ማስረጃዬን በትህትና አቀርባለሁ።
    እኔ ያለኝ ቅሬታ ከመሠረታዊ ጽሁፍዎ ነው።የነፍጠኝነትን ባሕላችን መሆን ከገለጹ በኋላ፤በዚሁ አንደኛው አንቀጽ መግቢያ ላይ “ፖሊቲከኛነት አዲስና ባዕድ የትግል ዘዴ ነው፤”***ፖለቲካን*** ግን በምን ዓይነት የተሳሳተ ትርጉም እንደወሰዱት ባይገባኝም ለአገራችን ኢትዮጵያ እንደ አዲስ ፥”አዲስና ባዕድ የትግል ዘዴ ነው፤”በማለት ትንተናዎትን {ወደ አልተፈለገ የእርስ በእርስ ጦርነት እንዳናመራ} በሚል ስጋትዎትን ይገልጻሉ።
    በመሠረቱ ፖለቲካ ማለትን ለእርስዎ ለማስረዳት ሳይሆን አንባቢውም የሰፋ ግንዛቤ ይጨብጥ ዘንድ፣ውክፔዲያ ሲተርጉመው:-“ፖለቲካ የሚለው ቃል ከግሪኩ πολιτικος («ዜጋ») ከሚለው ቃል የመጣ ነው። በአሁኑ ወቅት ፖለቲካ ማለት በቡድን ያሉ ግለሰቦች የጋራ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሚያስችላቸው ሂደት ነው። በዚህ ምክንያት ምንም እንኳ ፖለቲካ የሚለው ቃል ብዙ ጊዜ ከሃገርና ከመንግስት ጋር የተገናኘ ቢሆንም በሌላ አንጻር የሰው ልጆች በቡድን ሆነው በሚገኙበት ማናቸውም ስብስብ ይገኛል፣ ለምሳሌ በኩባንያወች፣ በትምህርት ቤቶች፣ በሃይማኖት መዋቅሮች፣ በቤተሰቦች ውስጥ ሳይቀር ፖለቲካ አለ። የኃይል አመዳደብ፣ የቁጥጥር፣ የውሳኔ ላይ መድረስ፣ የምጣኔ ሃብት ክፍፍል ጥያቄወች በሁለትና ከዚያ በላይ ባሉ ሰወች መካከል ሲነሱ ያንን ጥያቄ ለመፍታት በሚደረግ ሂደት፣ በዚያ ፖለቲካ አለ። ከዚህ አንጻር በአንዳንዶች አስተሳሰብ አብዮት፣ ጦርነት፣ ማህበረሳባዊ ግጭት ፖለቲካ ሳይሆኑ የፖለቲካ ሂደቱ ክሽፈት ናቸው። በሌሎች አስተያየት እኒህም የአጠቃላይ ሂደቱ አካል ስለሆኑ እንደ ፖለቲካ ይወሰዳሉ።ፖለቲካን የሚያጠናው የትምህርት አይነት የፖለቲካ ሳይንስ ወይም የፖለቲካ ጥናት ይባላል።” ይላል።ከዚህች ትርጉም በተጨማሪ እነፕሮፌሰር ያስተማሩንን ጨማምረን ለኢትዮጵያ “ሥነ-መንግሥት ወይም ኪነ-ሥልጣን”ፖለቲካ አዲስ እንዳልሆነ ግልፅ ተጨባጭ ነው።
    እናም ለነዚህ ችግሮቻችን ዕውቀቱም ቀድሞም ስለነበረን በነፃነታችን ለሦስት ሺህ ዓመታት መኖራችን ታሪክ የሚያውቀው ሐቅ ነው።ለፖለቲካ የምንሰጠው ትርጉም እንደዘመኑ የምንፈታው ከሆነ ሁሉንም ነገር ያለፈው ትውልድ ሊፈታው ይገባል።ከተፈጥሮ አንጻር ላብራራው የትኛውም እንስሳ ይሁን አውሬ ሰውን ጨምሮ የተፈጥሮ መከላከያ የሌለው የለም።ጥይት’ኮ ያለባሩድ ድንጋይ ብቻ ነው።ፖለቲካ ደግሞ በልሳን የሚደረግ የሰው ልጅ መግባቢያ አንዱ የዕውቀት ዓይነት ይሁን እንጂ በራሱ ጥንካሬ እንደፈለጉት በጊዜና በቦታ ምርጫ የሚጓዝ አይደለም፤ለዚህ ነው ኃይል የሚያስፈልገው።መቶ በመቶ እርግጠኛ ነኝ፤ፕሮፌሰር ለዚህ አባባሌ ብዙ መረጃዎችን ማቅረብ እንደሚችሉ።አለበለዚያ ለሃያ አምስት ዓመታት “ጅቡ እየቆረጠመኝ ስለሆነ ዝም ብላችሁ ተኙ”በሉንና እርፍ ይበሉት።እኔ ግን አቅሜ በፈቀደ ሁሉ ይህን የዘረኛ ጉጅሌ ቡድን ተዘርጥጦ እስኪወድቅ ትግሌን አላቆምም።በመሳሪያ መፋለሙን ዛሬ ሳይሆን በጠዋቱ ነው የደገፍኩት፤ለምን ቢባል እኔ እዚያው ትግራይ ውስጥ”ወያኔን”ያሁኑ ጉጅሌን ኖሬና የስነልቡናቸውን ሁኔታ ቢያንስ ለሁለት ዓመታት ተቀምጬ ነው ያወቅኳቸው።ለዚህም በሥነ ግጥም ሰሚ ካለ ብዬ የወገርኩበትን “ትርጁማን ፈልጉ” ብዬ የወገርኩበትን ተቃመሷት።”ጉጅሌ” ከወደቀም በኋላ ቂጡ ተገልቦ ታሪኩን ከማጋለጥና ተዋንያን የነበሩትን ከማስለቀም እና ተመጣጣኝ የደም ክፍያ እንዲጠየቅ ከማድረግ አልመለስም።
    ነፍጠኛ ተባለም አልተባለም ፕሮፌሰር መስፍን ወ ማርያም እንደ ሽምግልና አውቃለሁ ብዬው ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ ብቅ ጥልቅ እያሉ ብቻ የማይፈታ ሃሳብ መሰንዘሩ ተገቢ አይመስለኝም።ይልቅ ተሰሚነትና አመኔታ የሚጣልብዎ ኢትዮጵያዊ አባት ስለሆኑ ይበልጥ ሊያስተባብሩ የሚያስችል ሃሳብ ሊሰጡ በተገባ ነበር ባይ ነኝ፤በዚህ የዕድሜ ፀጋ ድካምዎ ላይ።እግዚአብሔር ዕድሜና ጤና እንዲሰጥዎትና የኢትዮጵያን የመጨረሻ መጀመሪያውን ያሳይዎ ዘንድ በጸሎት አልረሳዎትም።

    ?? ሊበላ የመጣ ጅብ…???
    xxxxxxxxxxxxxxxxxxxxx
    ሃያ አምስት ዓመታት እየተነገረው፤
    የሰው ደም ሲጠጣ ዛሬም ለሚኖረው፤
    በመግለጫ ብዛት ያቆማል የሚል ሰው፤
    አውቆ የተኛን ክፉ እንደመቀስቀስ ነው።
    ምን ዓይነት ዕብድ ነው”ታጋይ” ነኝ እያለ፤
    ሕዝብ በግፍ ሲገደል 
    ሞቱን ያቀለለ???
    በጉጅሌ አገዛዝ ኑሮ ያልመረረው፤
    ወያኔ አለዚያም ባንዳነት ያደረው፤
    ካልሆነ በስተቀር ሌላው ኢትዮጵያዊ፤
    በቅስፈቱ አልታየም ከመለስ ዜናዊ? ? ?…
    እኮ መልሱን ስጡኝ እኔም ላዳምጣችሁ፤
    በምን ቋንቋ ቢሆን ሕዝብን ታምናላችሁ???
    ወይስ በትርጁማን ጉጅሌው በሚያውቀው፤
    በበባዕድ መሳሪያ ክንዱን በሚያደቀው?
    በሚያርበደብደው በሕዝብ-አመፅ ትግል፤
    ቆርጠን ካልጀመርነው:-
    አይገኝም “ያ!!!” ድል!!!
    የቻለም በቻለው:-
    ያልቻለም በሚያውቀው፤
    በጠንካራ ክንዱ:-
    ጠላት በሚያደቀው፤
    በአንድነቱ አብሮ መግቢያ ካላሳጣው፤
    ዛሬም አይማርም 
    ባይቀጡ ካልቀጣው።
    ርኩስ ነው ጉጅሌ ደደብ የማይገባው፤
    ከፋሺሽት ተወልዶ ባንዳነት የጠባው።
    ቋንቋውን ያጠና ልሣኑን ያወቀ፤
    በተጠንቀቅ ላይ ነው ቀን እየጠበቀ።
    ምን አልጋ ቢነጠፍ ምን ቢለማመጡት
    ሊበላ የመጣ ጅብ አይጠግብም ቢሰጡት::
    በሚያርበደብደው በሕዝብ-አመፅ ትግል፤
    ቆርጠን ካልጀመርነው:-
    አይገኝም “ያ!!!” ድል!!!

    ትርጁማን ተገኘ።

    በደም-ሕብር ልሳን ድልን የተቀኘ፤
    ለፍትህ ነጻ-አውጪ ትርጁማን ተገኘ።
    ግንቦት ሰባት ነው ጉጅሌን ያጠና፤
    በሁለ-ገብ ትግል የሚናገር ጀግና፤
    በረሃ  የወረደ፤አምርሮ  የሸፈተ፤
    በየከተሜ ልብ አመፅ የከተተ፤
    ኢትዮጵያዬ እንዳለ፣
    ላይምር እየማለ፤
    ግንቦት ፯ እና የኢትዮጵያ አርበኞች፤
    ቛንቋ ለመተርጎም ሆነዋል አንደኞች።
    ሁልህም ማለሙን፣ቅዠቱን አቁመህ፤
    ይህንን ዘረኛ ታገል ተሽቀዳድመህ።
    እናም ተቀላቀል አመፅ አሳያቸው፤
    ባመፅ ካልታገልን ምንም አይገባቸው።
    እናም-ና ውጣ /ውጪ እንታገል:-
    ለጉጅሌው እርኩስ አግኝተናል ፀበል።
    ባላገር ተደፍቶ፤ከተማው ተጠምቶ፤
    የሚ-ጠጣ ጠፍቶ፤
    የሚበላ ሞልቶ፣ሞልቶ ተትረፍርፎ፤
    ረሃብተኛ ሁሉ በተስፋ ታቅፎ፤
    ፍትህን ሌላ ሰው ታግሎ እንዲያመጣለት፤
    እራሱ እየኖረ ሌላው እንዲሞትለት፤
    ሁሉም ከጠበቀ በሰው የራሱን ተስፉ፤
    በብልጥ-ለብልጥ-ሞት የገዳይ ሲከፋ፤
    ሃያ ዓመታት ሙሉ እየተነገረው፤
    የሰው ደም ሲጠጣ ዛሬም ለሚኖረው፤
    በመግለጫ ብዛት ያቆማል የሚል ሰው፤
    አውቆ ስለተኛ ማንም አይቀሰቅሰው::
    ምን ዓይነት ዕብድ ነው ይሻሻላል ያለ፤
    ሕዝብ በግፍ ሲገደል ሞቱን ያቀለለ:-
    እኮ መልሱን ስጡኝ እኔም ላዳምጣችሁ፤
    በምን ቋንቋ ቢሆን ትናገራላችሁ፧፧፧
    ወይስ በትርጁማን ጉጅሌው በሚያውቀው፤
    በመራር ሕዝብ አመፅ ክንዱ በሚያደቀው፧
    በሚያርበደብደው በመሳሪያ ትግል
    ቆርጠን ካልጀመርነው 
    አይገኝም ያ ድል::
    ምን አልጋ ቢነጠፍ ምን ቢለማመጡት:-
    ሊበላ የመጣ ጅብ አይጠግብም ቢሰጡት::
    እናማ ስንቶቹ እያዩ ተሞኙ፤ 
    በሌላው መገደል ማጣት እያገኙ።
    እንደው የታወቁትን ጉጅሌስ አይነካም፤
    በሰው አስገድሎ በደም ግን አይረካም።
    ለዚህ ነው በባዕድ እየተመከረ፤
    ዕርዳታውን ሲምግ ሲገድል የኖረ።
    ሕዛቡ ግን ሲማገድ ባመዱ የምትሞቁ፤
    በናንተም ምክንያት መሞቱን እወቁ።
    እናም-ና/ነይ ውጣ /ውጪ እንታገል:-
    ለጉጅሌው እርኩስ አግኝተናል ፀበል።
    በደም-ሕብር ልሳን ድልን የተቀኘ፤
    ለፍትህ ነጻ-አውጪ
    ትርጁማን ተገኘ።

    Reply
  5. eunetu says

    August 12, 2016 04:40 am at 4:40 am

    ፕሮፌሰር!ሰላምን የማይፈልግ ሰው ካለ እሱ የአእምሮ በሽተኛ መሆን አለበት፤ ሆኖም ግን የሰላምን ትርጉም በጉልበት የተካ መንቻካ ትቢተኛ በፋነነበት ምድር ቢያንስ ቢያንስ ሕዝቡ እራሱን ከተናካሽ አውሬ ለመጠበቅና ለመከላከል መዘጋጀት አይኖርበትም እንዴ?ሰላም እኮ ያንድ ወገን መሸነፍና ጥረት ማድረግ ብቻ ሳይሆን የሁለቱም ወገኖች ፈቃደኝነትን የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፤ ታዲያ አንዱ ሁልጊዜ በጉልበቱ እየተመካ በሌላው ህይወት ላይ የሚቀልድ ከሆነ የሰላም ፈላጊው የዋሁ ወገን የህይወት ትርጉም ምን ሊሆን ነው?የሰላም ትርጉም ከሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወገኖችን በሚያጋጭ ጉዳይ ላይ ግራና ቀኝ ያሉት ወገኖች ተስማምተው በጋራ መኖር ወደሚያስችላቸው ስምምነት ደርሰው ህይወትን በጋራ መኖር መቻል ይመስለኛል፤ ታዲያ አንዱ በይ ሌላው ተመልካች፣ አንዱ በጉልበቱ አሳሪና ገዳይ፣ሌላው ታሳሪና ተገዳይ በሆነበት አገር ሰላም ሰላም አሁንም ሰላም ሰላም ማለቱ ፋይዳው ምንድነው??? ፕሮፌሰር!ባይሆን በመከላከል ደረጃ መዘጋጀት የለብንም?ምናልባት በመስቀል መከራን ታግሶ እንደበግ የታረደውን የማርያም የሥጋ ልጅ የሆነውን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ምሳሌነት ተከትለው ከሆነ!እሱ በሞቱ ምክንያት የሚመጣውን ውጤት ከወዲሁ ስለሚያውቅ ነው፤ የእኛው ጉዳይ ግን እንኳን መንግሥተ ሰማይን የሚያስከፍት ሊሆን ይቅርና ገዳዮቻችንን ለበለጠ በደልና ፍርድ እያስገሰገሥናቸው ነውና እባካችሁ ሌላው ቢቀር የወገናችንን እንደ በግ በአውሬ እስከነፍሱ/በቁሙ መበላትን ለመከላከል እንዘጋጅ??? ወደሞት የሚነዱትን ታደጉ ስለሚል በእጃችን ያለው ግን የማናነበው የአምላክ ቃል የሆነው መጽሃፍ ቅዱስ!!!ለመልካም የወገን ነፍስ አድን ሥራ አብረን እንነሳ? እናንተም ገዳዮች ከታሪክ መማር ከቻላችሁ ቀን እንደሚመሽ፣ ሌሊቱም እንደሚነጋ እወቁ!!! ቢያንስ በስሙ ለስሙ ቁመንለታል /እንኳንም ካንተ ተወለድን/ለምትሉት ወገናችሁ ቋሚ ጠላት አታዘጋጁለት???

    Reply
  6. Nega says

    August 18, 2016 04:57 pm at 4:57 pm

    Professor Mesfin always tells the truth. He is not waiting to be liked by people (b/c he said what everyone wants to hear). He said it as is and that is a MAN with courage.

    Wish you health and longer life.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am
  • የኤሊያስ መሠረትን ፌክ መረጃ ማን ያጋልጥ? February 19, 2025 06:00 pm
  • አዘርባጃን፡ የሻዕቢያን ሸምቀቆ ማጥበቂያ?! February 19, 2025 12:29 am
  • የአሜሪካ ድምፅ/ቪኦኤ ይዘጋ ተባለ  February 12, 2025 03:37 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule