• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የትግሬ-ወያኔ የዐማራ እና የኦሮሞ ነገዶችን ሕዝብ ጨርሶ ለማጥፋት ያቀደው ሚስጢራዊ አዲስ ሤራ

August 17, 2016 01:11 am by Editor 2 Comments

ላለፉት 25 ዓመታት የትግሬ-ወያኔ በሕዝብ ላይ የፈጸመው ግፍና በደል ከመጠን በላይ በመሆኑ፣ ሕዝቡን ለእምቢተኝነት አነሳስቷል። ይህ ግፍና በደል መጠን የለሽ በመሆኑ፣ በአገሪቱ ልዩ ልዩ ክፍሎች፣ በተለይም በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋ፣ በወሎ፣ በሐረርጌ፣ በአርሲና በወለጋ ክፍለ-ሀገሮች የሚኖረው ሕዝብ፣ የትግሬ-ወያኔ «ለብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ዕኩልነት» ሲል «አመጣሁት» ያለውን «ሕገ-መንግሥት» የማይቀበለው መሆኑንና፣ የዚሁ  «ሕገ-መንግሥት» ተብየ መገለጫ የሆነውን ሠንደቅ ከተሰቀለበት በማውረድ፣ ከጥንት ጀምሮ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት መገለጫ፣ የነፃነት ቀንዲል የሆነችው ሠንደቅ ከፍ-ብላ እንድትውለበልብ እያደረገ መሆኑ በግልጽ ተስተውሏል። ይህም የትግሬ-ወያኔ አመጣሁት ያለው ዕኩልነትና የነገዶች አንድነት ውሸት መሆኑን፣ ባንፃሩ ግን የትግሬ-ወያኔ የውስጥ ቅኝ ገዥ ኃይል እንደሆነ፣ በተከታታይ በተደረጉት የሕዝባዊ እንቢተኝነት ሰላማዊ ሰልፎች በግልጽ ታይቷል።

ይህ የሕዝብ አመጽ ያርበደበደው የትግሬ-ወያኔ ቡድን፣ የሚይዝ የሚጨብጠውን በማጣቱ፣ የእርሱ ምርኮኛ የሆነውንና በጥቅማጥቅም የገዛውን የትግራይ ትውልድ በነቂስ አስታጥቆ፣ በዐማራና በኦሮሞ ነገዶች ሕዝብ ላይ ለመዝመት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስተማማኝ ከሆኑ የውስጥ ምንጮቻችን ያገኘናቸው መረጃዎች ያሳያሉ። የትግሬ-ወያኔ ከሚያደርገው ሠፊ የጥፋት ዝግጅቶች ውስጥ፣ የትግራይን ትውልድ «በትግልህ ያገኘኸውን ልዩ መብትና ነፃነት፣ ትምክተኞች፣ ነፍጠኞች፣ የድሮው ሥርዓት አራማጆችና ዐማሮች ሊነጥቁህ ነውና ዐማራን ለማጥፋት ዝመት፣ ተንቀሳቀስ» በማለት፣ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በጠለምት፣ በአርማጭሆ ነዋሪዎች ላይ ክተት አውጇል። በአጠቃላይም በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋና በወሎ የዐማራ ነገድ ሕዝብ ላይ መጠነ ሠፊ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመፈጸም ዝግጅቱን አጠናቋል። በመሆኑም ሰሞኑን በጎጃምና በጎንደር የተለያዩ ከተሞችና ገጠሮች ቅጥር የነፍሰ ገዳይ ቡድኖችን በማሰማራት ሌሊት ሌሊት ወጣቱን እየፈነ ወደ ማሰቃያ እስር ቤቶቹ እያስገባ መሆኑ ታውቋል።

ይህ ድርጊቱ ፍላጎቱን ሙሉ በሙሉ ሊሳካለት እንደማይችል በመረዳት፣ በመላ ኢትዮጵያ የሚያካሂደው ሌላም ሠፊ የጥፋት ዕቅድ አቅዶ ለተግባራዊነቱ በጥድፊያ እየሠራ መሆኑ እየተሰማ ነው። ይህም መጠነ ሠፊ የሆነ ጥፋት ያነጣጠረው በዐማራና በኦሮሞ ነገዶች ሕዝብ ላይ እንደሆነ ታውቋል። የትግሬ-ወያኔ በእነዚህ ነገዶች ሕዝብ ላይ የጥፋት ተልዕኮውን ለመወጣት ያቀደው ዕቅድ፣ «በዐረብ ኢሚሪቶችና በሻዕቢያ የሚታገዙ አሸባሪዎች፣ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ እየተንቀሳቀሱ ነው» የሚለውን ሀሳብ የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ፣ በተለይም ሽብርተኝነት ለመዋጋት በሚል ሸሪክ የሆነውን የምዕራቡን ዓለምና የአሜሪካንን ልብ ለማማለል እንደሆነ ይገመታል። በዚህ ረገድ በቅርብ ቀናት ውስጥ የትግሬ-ወያኔ በሐረር፣ በድሬደዋ፣ በጎንደር፣ በባሕር ዳርና መሰል ከተሞች፣ የሕዝብ ክምችት በሚበዛባቸው ቦታዎች፣ በመንግሥታዊ ተቋሞች፣ በመገናኛ አውታሮች ወዘተርፈ ፈንጅ በማፈንዳት እኩይ ዓላማውን በተግባር እንደሚያውል ውስጥ አዋቂዎች አስጠንቅቀዋል። ፈንጂዎችን ራሱ አፈንድቶ፣ «የዐማራ እና የኦሮሞ ጽንፈኞች እንዲህ አደረጉ» በማለት ለደጋፊዎቹ  የተቀነባበረ የሤራ መረጃ በማቅረብ፣ «ሕገ-መንግሥት» ተብየውን አግዶ፣ የአስቸኳይ ጊዜ ወታደራዊ አገዛዝ በማወጅ፣ በሁሉም ቦታዎች ለወያኔ ጄኔራሎች የመግደልና የማሰር ሥልጣን በመስጠት በዐማራውና በኦሮሞው ነገዶች ሕዝብ ላይ መጠነ ሠፊና አሰቃቂ ዕልቂት ለመፈጸም ቁርጠኛ አቋም መያዙ ታውቋል።

በሰኔ 1980 ዓ.ም. «ነፃ ላወጣህ መጣሁ» ባለውና በራሱ ነገድ በሆነው የሀውዜን ከተማ ነዋሪ ሕዝብ ላይ ያን የመሰለ የተቀነባበረ ሤራ ሠርቶ ሕዝብ ያስጨረሰ ድርጅት፣ «ጠላቶቼ ናቸው» ባላቸው የዐማራና የኦሮሞ ነገድ ሕዝብ ላይ ይህን ዓይነቱን ድርጊት አያቅድም፣ አይፈጽምም፣ አያደርጉትም፣ አይሆንም የሚያሰኝ አመክንዮ አይኖርም። ኢትዮጵያዊ የሆኑትንና «ለትግሬ-ወያኔ ዓላማ አንገዝም፣ አባልም አንሆንም» ያሉትን የትግራይ ልጆች፣ «አባሎቼ ናቸው» የሚል የተቀነባበረ የሐሰት መረጃ፣ ለደርግ የመረጃ አካላት እያቀበለ ወገኖቹን ያስጨፈጨፈ ድርጅት ይህን አያስብም አይባልም። በሂደት እንዳስተዋልነው፣ ወያኔ «አደርገዋለሁ፣ አጠፋዋለሁ» ብሎ ያቀደውንና ያለው በተግባር ከመፈጸም ወደ ኋላ ያለበት አንድም አጋጣሚ አላየንም። ይህንም እኩይ ድርጊት አያደርገውም ለማለት የሚያስችል ምክንያት ለማቅረብ አስቸጋሪ ነው።

የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን፣ ዐማራንና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን አጠፋለሁ ብሎ አቅዶ heroመነሳቱ ይታወቃል። በዕቅዱ መሠረትም 5 ሚሊዮን ዐማራ አጠፋ። የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አመራርን ከሦሥት ከፈለ፥ የአገር ቤትና ስደተኛ ሲኖዶሶች እንዲሁም ገለልተኛ በሚል። የሃይማኖቱ ነባር ተቋሞችን፣ ለምሣሌ ያህል፥ የዋልድባን፣ የዝቋላ አቦን እና የማኅበረሥላሴን ገዳማትን አቃጠለ፤ ቅጥረ ግቢያቸውን መነጠረ። የሃይማኖት አባቶችን አሰደደ። ቱባ ባለሥልጣኖቹ ዐባይ ፀሐየ፤ ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣ ሣሞራ የኑስ ሌሎችም በአደባባይ፣ «ዐማራና ኦርቶዶክሱን አከርካሪውን ሰብረነዋል፣» «ገድለን ቀብረነዋል» ማለታቸውን አንዘነጋም። እናም ባለፉት 25 ዓመታት ገድለው ካልጨረሱት ውስጥ የቀረውን የዐማራና የኦሮሞን ነገዶች ሕዝብ «አስቸኳይ ወታደራዊ» አገዛዝ በማወጅ ሊጨርሱት ቁርጥ ሀሳብ ማድረጋቸውን የዐማራውና የኦሮሞው ነገድ አባሎች ለአፍታም መጠራጠር አይኖርባቸውም። ስለሆነም፣ የትግሬ-ወያኔ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ወደ ጥፋት ተልዕኮው ሳይገባ፣ ዐማሮችና ኦሮሞዎች ዕቅዱን ለማክሸፍ መተባበር ይጠበቅባቸዋል።

ከሁሉም በላይ «ሺህ ጋን ቢታለብ ወይ በገሌ» እንዳለችው ድመት፣ ዐማራው በብሔርተኞቹ ድርጅቶች በቀና ስለማይታይ፣ ልጆቹ በመካከላቸው አለን የሚሏቸውን ጥቃቅን ልዩነቶች በማርገብ፣ በአንድነት በመቆም ለወገናችን መከታ መሆን ይጠበቅብናል። የዐማራው ምሁራንና ፖለቲካኞች በአንድነት መቆም፣ የአንድነት ኃይሉን ለተፈላጊው አጠቃላይ የኢትዮጵያውያን አንድነት ጽኑ መሠረት ስለሚሆን፣ የዐማራው ምሁራን በቅድሚያ የነገዳቸውን አንድነት ዕውን በማድረግ፣ በሌሎች አቻ ቡድኖችና ድርጅቶች ላይ መልካም ተጽዕኖ ማሳደር ይጠበቅባቸዋል። ይህን ለማድረግ ስበቦችን መደርደር አስፈላጊ አይደለም። በወገናችን አንገት ላይ ሳንጃ ተጥሏል፤ በግንባርና ደረቱ ላይ አፈሙዝ ተደግኗል። ስለዚህ ይህ ጊዜ አይሰጥምና በዐማራ ስም የተደራጃችሁ ድርጅቶች ከያላችሁበት «አለን» ብላችሁ በጋራ የምትሠሩበት መንገድ ካሁኑ ካልጀመራችሁ፣ ይህንም ለወገናችሁ በግልጽ ካላሳያችሁ፣ የጥፋቱ አካል እንጂ፣ የመፍትሔው አካል ናችሁ ብሎ ማኅበረሰቡም ሆነ ታሪክ  ሊያወሳችሁ እንደማይችል በእርግጠኝነት መናገር ድፍረት አይሆንም። ስለሆነም ሁላችንም ለዐማራው ኅብረትና አንድነት ኅሊናችን ከፍተን በቅንነት እንነሳ! በዚህ የመከራ ጊዜ የዐማራው ልሂቅ በአንድነት ቆሞ፣ ለወገኖቹ ቤዛ ካልሆነ ምንጊዜም ዐማራው አንድ ይሆናል ለማለት ያስቸግራል። እንኳን የአንድ ታላቅና ታሪካዊ ነገድ ልጆች ቀርቶ፣ በክረምት እባብና ጓጉንቼር በአንድ ጉድጓድ ይኖራሉ። ይህ ክፉ የወያኔ ዘመን ዐማራውን ቀርቶ፣ ዐማራና ኦሮሞውን በአንድ ካላሰላለፈ የኢትዮጵያ አንድነት ርቆ የተሰቀለ ባዶ ተስፋ ከመሆን አያልፍም።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

ዐማራነት ነፃነት፣ ዕኩልነት አንድነት ነው!

ኢትዮጵያ በቆራጥና ጀግና ልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Bereket says

    August 20, 2016 05:06 am at 5:06 am

    What are you talking about ,did u forget there are millions of ethiopians dont want to think about ethinc or are hybridid with amhara ,tigrians , oromo pepole , and more so please dont focus on groups of ethinc .if u want to see your back u have all blood after all our all human being blood is red , think twice unity for one nation is strength ,

    Reply
  2. NW_Group Agency says

    August 25, 2016 08:21 am at 8:21 am

    ኢትዮጵያ በቆራጥና ጀግና ልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule