• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የትግሬዎች መንግሥት አወዳደቁና ክፋቱ!

August 18, 2016 12:00 am by Editor Leave a Comment

ባሁን ሰዓት፤ በገዥነት ሕልሙ እየተንሳፈፈ ካለው የትግሬዎች ቡድን በስተቀር፤ ኢትዮጵያን አደጋ ላይ የጣላት ይሄው ቡድን፤ የውድቀት አፋፉ ላይ መሆኑ ለሁላችን ግልጽ ነው። አሁን ካለንበት ሰዓት እስከመጨረሻው ውድቀቱ ያለው ጊዜ ግን፤ በጣም የከፋና የተመሰቃቀለ ነው። ይህ የሚሆነው፤ ከፊል በዚህ ወራሪ ቡድን ተግባር ሲሆን፤ ከፊሉ ደግሞ በኛው በታጋዩ ክፍል ያለነው ለዚህ ውድቀት በማድረግና ባለማድረግ ላይባለው ሂደታችን ነው። በተጨማሪ ደግሞ፤ የሃያ አምስት ዓመት የዚህ ቡድን ፀረ-ኢትዮጵያ አገዛዝ፤ ሀገራችንን ለከፋ ወደፊት አዘጋጅቷታል። ሀቁን ተቀብለን ከአሁኑ መደረግ ያለበትን ካላደረግን፤ በኋላ ይሄን ብናደርግ ኖሮ ብለን የመቆጫ ሰዓት አናገኝም፤ ያኔ ሁኔታውን አንገዛውምና!

ይህ ወራሪ ቡድን፤ የመጨረሻ እስትንፋሱን የሚያወጣው በቃሬዛ ነው።ሕዝቡ አቸናፊ ሆኖ እንደሚወጣ ምንም ዓይነት ብዥታ ባይኖረንም፤ የሚከተለው ምን ይሆን?የሚለው ስጋትሀቅ ነው። ያንን ሳጋት የበለጠ ለማክፋት ይህ የትግሬዎች ቡድን ሲጥር፤ ታጋዩ ክፍል የሚሠጠው መልስ ወሳኝ ነው። ህዝቡ ማቸነፍ የሚችለው፤ ከዚህ ቡድን በልጦ ሲገኝ ነው። ጎልብቶ ሲገኝ ነው። ጎብዞ ሲገኝ ነው። ይህ ቡድን ምን እያቀደ ነው? ብሎ ቀድሞ ሲዘጋጅ ነው። ምን ሊያደርግ ይችላል? የሚለውን ወስዶ አደናቃፊ ዝግጅቶችን ሲያሰላ ነው። አስኪ ይህ ቡድን ሊያደርጋቸው የሚችሉትን እንመልከት፤

  • እንዳየነውና እንደሰማነው፤ አልቃይዳ ወይንም አልሸባብ ወይንም አይሲስ ብሎ ታጋዩን ያልሆነ ቀለም በመቀባት፤ የውጪ ሀገሮችን ድጋፍ ለማግኘት ይጥራል። አይሆንም ማለት ሞኝነት ነው። ዛሬም ድረስ በሺር አል አሳድ ሶሪያን የሚገዛው፤ አሜሪካና አውሮፓ በከፍተኛ ድጋፍ ተቃዋሚዎቹን ቢረዱም፤ በሶቪየቶችና ቻይናዎች ድጋፍ ነው። እኒህም ሆኑ ሌሎች ሀገራት፤ ስሌታቸውን የሚያተኩሩት፤ ለኔ ሀገር ሁኔታው ምን ያስገኝልኛል? ብለው ነው።
  • ከዚህ አያይዞ፤ የውጭ ቅጥረኞች በማለት ታጋዮችን በሀገር ቤት ለማስጠላት ይሞከራል። እያደረገውም ነው። ይህ፤ ጊዜ ለመገብያ የሚጠቀምበት ዘዴ ነው። ወረሩኝ ብሎም ጦርነት በጎረቤት ሀገሮች ሊከፍት ይችላል። ይህ ሁሉ፤ የሕዝቡንና የታጋዩን እንቅስቃሴ ለማለዘብ ነው። ጊዜው አልፏል።
  • ዋናው የዚህ የትግሬዎች ቡድን አስከፊ ተግባር፥ ጉልበቱን መጠቀም ነው። ይህ እብሪተኛ ቡድን መቼም ቢሆን የሚተማመነው፤ “ጉልበቴ ከሁሉም ይበልጣል!” ብሎ ነው።አሁንም ሁሉን ነገር “በጉልበቴ እወጣዋለሁ!” ብሎ፤ አረመኔያዊ ተግባሩን ቀጥሎበታል። ነገሮችን አጢኖ መመልከት ድክመት ይመስለዋል። በሰላም ባዶ እጁን አቤቱታ ሊያሰማ የወጣውን ሕዝብ፤ እስካፍንጫው የታጠቀ አጋዚ አሰልፎ በቀጥታ በሰልፉ ላይ በመተኮስ አሁን በመቶዎች የሚቆጠሩትን እየገደለ ነው። ነገ ደግሞ በሺዎች የሚቆጠሩትን ይረሽናል። እስኪሞት ድረስ ሌላ ዕውቀት የለውም። ካልገደለ ውሎ የሚያድር አይመስለውም። ሕዝብ ቆርጦ ከተነሳ፤ መመለሻ የሌለው መሆኑን ሊረዳው አይችልም። የዚህ ቡድን መነጽር፤ የተቃወመኝን ገድዬ፤ ጉዳዩን አጠፋለሁ ነው።
  • ታጋዩን ከሕዝቡ ለመነጠል ይጥራል። ደደብ ሆኖ ነው እንጂ፤ ታጋዩ እኮ ሕዝቡ ነው! ሊገባው አይችልም። ታጋዩን ሊከፋፋል ይሞክራል። ታጋዩን እኮ፤ ከዚህ ቡድን ሕልውናና ጥፋት የበለጠ የሚያንገበግበው የለም። ለነገሩ ይህ አዲስ አይደለም። እስከዛሬ ያቆየው፤ የሕዝቡ በአንድ አለመነሳት ነበር። በዘር፣ በሃይማኖትና በጥቅም መከፋፈሉን ተክኖበታል። አሁን ግን ሕዝቡ ይህን ሁሉ ጥሶ እንዲወጣ የዚህ ቡድን ለከት የለሽ በደል አስገድዶታል።
  • “አሸባሪዎች ናቸው!” ብሎ ማላዘን የዕለት ተግባሩ ነው። ነገ ደግሞ የየሰዓት ጸሎቱ ይሆናል። ለዚህም የሃይማኖት አባቶችን አሰልፎ ያስወግዛል፣ ይማጠናል፣ ያባብላል። የቤተክህነትና የመስጊድ መሪዎችን አቅርቦ ሊናዝዝ ይቻላል። አብሮም ሆዳም የመንግሥት ሠራተኞችንና የጦር መሪዎችን አሰልፎ ሊያስወግዝ ይቻላል።
  • መላ የፌዴራልና የክልል አስተዳደራዊ መዋቅሮችን የስለላ ድርጅት ያደርጋቸዋል። እያንዳንዱን ትግሬና የስመ ኢሕአዴግ አባል ተራ ሰላይ ያደርጋል። ከታጋዩ ከድተው ወደኔ ገቡ ብሎ የውሸት ታጋዮችን በቴሌቪዥን ሊያቀርብ ይችላል።ተዘረፈ ብሎ የመንግሥትን ካዝና ወደ መቀሌ ሊያሻግረው ይችላል። ይህ ቡድን ሌብነት ኒሻኑ ነው።
  • ለመታያ የተቀነባበረ የሱ ደጋፊ ሰላማዊ ሰልፎችና ትዕይንቶች ሊያዥጎደጉድ ይችላል። በማስፈራራት፣ በመደለልና በማስገደድ ሰልፍ እንዲወጡ ሊያደርግ ይችላል። ይህን ማንም አይስተውም። ሆኖም ግን የራሱን የመንፈስ ጭንቀት እንኳን አይበርድለትም። አምባገነን መንግሥታት ሙያቸው ነው። ትናንት መንግሥቱ ኃይለማርያም አድርጎታል።
  • ሲያስበረግገው የሚያድረው የሕዝቡ ቁጣ፤ በፓልቶክ፣ በፌስቡክ፣ በሬዲዮና በድረገጾች ላይ ዘመቻውን እንዲያበዛ ያደርገዋል። መስሎት ነው። ኢንተርኔቱን ይዝጋው፤ ሕዝቡ በኢንተርኔት ሳይሆን በሚኖርበት ሀቅ ተገፋፍቶ ነው የተነሳው። ፓልቶክ ደግሞ ሕዝቡን ወደ አንድ አመጣና በትክክለኛው ጠላቱ ላይ እንዲያተኩር ረዳው እንጂ፤ ችግሩ ያስተዳደር በደል ነው። የዜና ልውውጡን ሊያግት ቢሞከርም፤ በየቦታው ያለው የሱ ግፍ ያነሳሳው ነው።
  • በማታለልና በማውገርገር የተካነው ይህ የትግሬዎች ቡድን፤ እደራደራለሁ፣ ለውጥ አደርጋለሁ፣ ሽምግልና እገባለሁ ሊል ይቻላል። ይህን እያለ ግን፤ በጎን በከፋ ሁኔታ ያው መግደሉን ይቀጥልበታል። ይህን የሚለው ጊዜ ለመግዣ ብቻ ነው። ተገዶም ቢሆን ለድርድር ቢቀርብ፤ ሥልጣኑን ማጋራት ወይንም የሰረቀውን ሀብት መመለስ አይፈልግም። ሥልጣኑን የሚያስረክበው ወድሞ ነው።

ይህ ሁሉ ተግባሩ፣ አንድ ቀና አንድ ሌሊት ሊገዛለት ቢችልም፤ በአንጻሩ ግን፤ ትግሉን በትግሬዎችና በኢትዮጵያዊያን መካከል በማድረግ፤ የትግራይን ሕዝብ ለነገ ዕልቂት ያዘጋጀዋል። ይህ እየመጣ ያለ ሀቅ ነው። በርግጥ አሁን ሊለወጥ የሚችልበት ሰዓት ነው። ይህን ደግሞ እንደሚከተለው አቀርበዋለሁ።

ምንም አንኳ ይህን ፈጻሚው የትግሬዎች ቡድን ቢሆንም፤ በዚያው አኳያ፤ የታጋዩ ክፍል ጥረት፤ ሊያስተካክለው ወይንም ሊያባብሰው ይችላል። በአሁኑ ወቅት ታጋዩ ያለበት ሁኔታ አመቺ አይደለም። በርግጥ ሕዝቡ ራሱ እየመራ ያለበት ይህ እንቅስቃሴ፤ ወደፊት እንዲሄድና ለስኬት እንዲበቃ፤ መልክ መያዝ አለበት። ማዕከል ሊኖረ ይገባል። ይህ ማለት፤ አሁን ካሉት ድርጅቶች አንዱ ወይንም ሌላው ይምራው ማለት አይደለም። አሁንም መሪው በቦታው ሕይወቱን እየከፈለ ያለው ሕዝቡ ራሱ ነው። ታዲያ በውጪም ሆነ በሀገር ውስጥ ያለን የታጋዩ ክፍል ነን የምንል ሰዎች፤ እገዛችን መሆን ያለበት፤ ይህን ሕዝባዊ አካል መርዳትና ማጠናከር ነው። ለዚህ አመራር ተገዥ መሆን ነው። በየቦታው በመደረግ ላይ ያለው ሰላማዊ ሰልፍ፤ እንዲያው ከየሰማዩ ዱብ ዱብ ያለ አይደለም። ሕዝባዊ ቅንጅት አለው። ወጣቶቹ ከፍተኛውን መስዋዕትነት እየከፈሉ ያዋቀሩት የደማቸው ሐረግ ነው። ይህን ማጎልበት አለብን። የኔን ድርጅት ወይንም የኔን ድርጅት እያልን፤ ድርጅቶቻችን በሕዝቡ ላይ ለመጫን ያጎበጎብነው፤ ልጓማችንን መያዝ አለብን።

ጎንደር የተሰለፉት ወጣቶች፤ የእስልምና ተከታይ ወኪሎችና የኦሮሞ ወጣቶች ጉዳይ ጉዳያችን ነው!አሉ። የኦሮሞ ወጣቶች ተከትለው፤ ጠላታችን አማራ አይደለም ጠላታችን ወያኔ ነው! አሉ። የትግሬዎችን ቡድን አከርካሪ ሰበሩት። ይህ በተግባር መያያዝ አለበት። ጊዜውና ምቾቱ ያለን እኛ በውጭ የምንገኝ ይሄን አንድነትን የመፈለግ ጥረት ማጎልበት እንችላለን። አለዚያ፤ እንደ ግብፁ ሙባረክ ሳይሆን እንደ ሶሪያው አሳድ የተጓተተና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ብዙ ታጋዮች የሚያልቁበት ሀቅ መልበሳችን ነው።ግንቦት ሰባት የራሱን ንጉስ ለማንገስ ሲሯሯጥ፣ ኢሕአፓ የራሱን ለማንገስ ሲጣደፍ፣ ሰላማዊ የራሱን፣ መድረክ የራሱን ሲያዘጋጅ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል፤ አንድነት አጥቶ፤ ይጓተታል። ሶሪያ ውስጥ የየውጪ ሀገሮች፤ ማለትም የቱርክ፣ የሊባነን፣ የኩዌት፣ የአሜሪካ ደጋፊ ታጋዮች ተለያይተው በየበኩላቸው ባንድ በኩል፤ ሶቪየት ኢራንና ቻይና ደግሞ የአሳድን ማዕከላዊ መንግሥት ደግፈው፤ የሶርያ ሕዝብ እያለቀ እንዳለበት ሀቅ፤ ተያይዘን እንዳንሰምጥ እሰጋለሁ።

አንድነት አለመሰለፋችን ትግሉን ጎድቶታል። አንድ ጠላት አለን ብቻ ሳይሆን፤ ሁሉም ድርጅቶች ሕዝቡ የበላይና ወሳኝ ነው ብለዋል። ታዲያ ይሄን ከተቀበሉ፤ ለምን የየራሳቸውን ጥንካሬ አጉነው፤ ሌሎችን እንደሌሉ በመቁጠር ይሯሯጣሉ? ለምን ሀገርን በማስቀደም የትግሉ አካል ለመሆን ፈቃደኛ አይሆኑም? ይህ ተጠያቂነታቸውን ያጎላዋል። ይህ ትግሉን በመጎተት ያስጠይቃቸዋል። የትግሬዎች ቡድን የሚያደገውን ጥፋትና የሚያደርሰውን በደል መዘርዘሩ በቂ አይደለም። ባሁኑ ሰዓት ደግሞ፤ ሕዝቡ ደሙን እያፈሰሰ ባለበት ወቅት፤ ስለ በደሉ መዘርዘር ትርጉም አጥቷል። አሁን ትግሉ ወደፊት መሄዱንና የድል ጎዳና መቀየሱን ነው ማብሰር ያለብን። አሁን፤ የሕዝቡን ድል መዘርዘር ላይ መሆን አለብን። ይህ ግን በምኞት አይመጣም። ተጨባጭ ሥራዎችን መሥራት አለብን። ይህ ደግሞ የሚጀምረው፤ ትግሉን በአንድነት ለማድረግ ወደ አንድ በመሰባሰብ ነው። ምንም እንኳ ይህ የአንድነት ጥሪ ለፍቶ ለፍቶ የሟሸሸ ቢሆንም፤ አሁን ክፍተት ተፈጥሮ ማዕከሉ ባዶ ሲሆን፤ እንደ ትግሬዎች ቡድን ዘሎ ለሚገባ የታጠቀ ቡድን በሩን በርግደን እንዳንተው እፈራለሁ። ሕዝባዊ ድል የሚገኘው፤ ሕዝቡ ሲመራና ሲታገል ብቻ ነው። ድርጅቶች የሚታገሉት ለድርጅታቸው ነው። የሕዝብ ድርጅት ደግሞ የለንም።

ከታላቅ አክብሮታ ጋር

አክባሪያችሁ  አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘጋጅ

ሐሙስነሐሴ፲፪ ቀን ፳፻፰ ዓመተ ምህረት( 08/18/2016 )

eske.meche@yahoo.com


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am
  • በትግራይ የሰላም ስምምነቱን መሠረት ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደሚፈጸም ተገለጸ December 13, 2022 09:20 am
  • ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ሌብነት የተከሰሱት የደኅንነት መ/ቤት ሠራተኞች ክስ ተመሰረተ December 13, 2022 09:06 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule