• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

መጪው ቅዳሜ ለት በመላው ኦሮሚያ ሰላማዊ ሰልፍ ይካሄዳል

August 4, 2016 08:44 am by Editor 1 Comment

እሁድ እለት በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ በአስርታት ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ ወያኔን ተቃውሞ በሰላም ወደ ቤቱ ተመለሰ። በጣም ጥሩና ታሪካዊ ሰልፍ ነበር። በእለቱ ከጥቂት ሰዓታት በኋል ግን በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ አወዳይ ከተማ ወጣቶች ሰልፍ ወጥተው በአጋዚ አልሞ ተኳሾች 26ቱ ቆስለው እስከ አሁን 6 ሞተዋል።

ይሄንን እንደምሳሌ ጠቀስኩ እንጂ ኦሮሚያ ውስጥ ወያኔ ሰላማዊ ሰልፈኞችን በጥይት እሩምታ ሲፈጅ አዲስ አይደላም። ባለፉት 9 ወራት ካ600 በላይ ዜጎች ተገድለዋል፣ 5000 የሚሆኑ የመቁሰል ጉዳት ደርሶባቸውል። ይሄንን ቁጥር ወስደን ብናሰላው፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ በየእለቱ ባማካይ ከሁለት እስከ ሶስት ሰዎች ኦሮሚያ ውስጥ በመንግስት ታጣቂ ሃይሎች ሲገደሉ እንደነበረ ማየት ይቻላል። ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈጸም የአምባገኖች ጸባይ ነው ተብሎ ሲታለፍ ነበር። ነገር ግን ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጣ የሚገደልው የኦሮሚያ ህዝብ ብቻ መሆኑ ግልጽ እየሆነ ሲመጣ ነገሮችን መለሰን እንድናጤን አድርጎናል።

ለመሆኑ በተለያዩ ክልሎች ለወጡ ሰላማዊ ሰልፈኞች የተለያየ ምላሽ ምክንያቱ ምንድነው?

1) የኦሮሚያ ሰልፈኞች የጦር መሳሪያ ይዘው አለመውጣታቸው። ምክንያቱም እንደሚታወቀው ባለፉት 25 አመታት ተደጋጋሚ ትጥቅ የማስፈታት ዘመቻ በኦሮሚያ ሲካሄድ ነበር። እናም በግልጽ የታጠቀው ህዝብ አናሳ ነው። በተጨማሪም የኦሮሞ አመራሮች ህዝቡ መሳሪያ ይዞ እንዳይወጣ ሲማጸኑ ነበር። ይሄም የተደረገበት ምክንያት ያቺ ሀገር እና ህዝብ ወደ ዳግም ጦርነት ሳይገቡ በነፍጥ-አልባ ትግል ለውጥ ለማምጣት ካለ ምኞት የተነሳ ነው። ነገር ግን ይህን የኦሮሞን ሰላም ወዳድነት ህወሀቶች እንደ ፈሪነት መቁጠራቸው ገሃድ ወጥቷል።

2) ባለፉት 9 ወራት በኦሮሚያ ውስጥ በተካሄደው ትግል ብዙ ከተሞች ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ ሲወጡ እንኳን የትግሬዎች ንብረት እና ህይወት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጓል። ይህ አቋም ግን ህወሀቶች እንደ ጅልነት (naivety and harmlessness) የተቆጠረ ይመስላል።

ባጠቃላይ የህወሀት መሪዎች እንድን ህዝብ የሚሰሙት በጠመንጃ ሲጋፈጣቸው እና ዘመዶቻቸው ሲነካ ብቻ መሆኑን ደጋግመው አረጋግጠዋል። ለኦሮሞ ህዝብ ያላቸውን መጠን ያለፈ ንቀት እና ጥላቻ በተደጋጋሚ አሳይተዋል። እናም አንድ እጅ ብቻውን ማጨብጨ ስለማይችል የኦሮሞ ህዝብ እራሱን ከተከፈተበት የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለመታገድ የስትራቴጂ ለውጥ ሊያደርግ እየተገደደ ነው። ሆኖም ግን ወደዚህ ዓይነቱ መመለሻ የሌለው መንገድ ከመግባታችን በፊት የመጨረሻ እንድል መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። በዚሁም መሰረት የሚቀጥሉት እርምጃዎች ይወሰዳሉ:

1. በመጪው ቅዳሜ በኦሮሚያ ከተሞች የተቀናጁ ሰልፎች ይካሄዳሉ። እነዚህ ሰልፎች ልክ እንደ ከዚህ በፊቶቹ ሁሉ ፍጹም ሰላማዊ ይሆናሉ። በሰላማዊ ሰልፎቹ ላይ መንግስት ኦሮሞ ላይ እያካሄደ ያለውን ግድያ ባስቸኳይ እንዲያቆም፣ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ካላንዳች ቅድመ ሁናቴ እንዲፈቱ፣ ኦሮሚያን በኣጋዚ ጦር ማስተዳደር እንዲቆም፣ ህዝቡ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብቱ እንዲጠበቅ የሚሉና የመሳሰሉ ሌሎች መሰረታዊ መብቶችን መከበር የሚጠይቁ ጥያቄዎችና መፈክሮች እንዲንጸባረቁ ይደረጋል።

2. ለዚህ ሰልፍ ፍቃድ አይጠየቅም። በህጉ መሰረት ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የሚያስፈልገው መንግስትን ማሳወቅ ብቻ በቂ ነው። ይህ ጽሁፍ እንደማስታወቂያ እንዲረዳ ለኦሮሚያ እና ለፌደራሉ መግስት መሰራቤቶች ገቢ አድርገናል።

የኦሮሚያም ሆነ የፌደራል የታጠቁ ሀይሎች ሰላማዊ ሰልፎቹን ለማስተጓጎልም ሆነ በእለቱ በህዝቡ ላይ ጥቃት የሚፈጽሙ ከሆነ ቀጥሎ ለሚመጣው አደጋ ተጠያቂ እንደሚሆኑ በዚሁ ማስጠንቀቅ እንወዳለን። የተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብም ለምስክረነት ይህን ግልጽ ማስታወቂያ በጥሞና እንዲያነብልንና ከጎናችንም እንዲሰለፍ ባክብሮት እንጠይቃለን።

‪#‎OromoProtests‬

Filed Under: Politics Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. koster says

    August 11, 2016 10:43 pm at 10:43 pm

    Free Bekele Gerba and all political, religious leaders as well as journalists and bloggers. There is only state terrorism in Ethiopia and the main terrorists are TPLF fascists bred and nurtured by the US/UK/EU and their allies – the Arabs. Ethnic federalism/ethnic cleansing is a total failure and should be dismantelled with the fascists and their constitution. Federalism in a free and democratic Ethiopia and with the participation and full understanding of the Ethiopian people. The current ethnic federalism only serves TPLF and OLF and harmfull to the Amharas. The number of languages to be used and the adminstration divisions should be decided by a freely and democratically elected parliament. The forcefully land grabbing and expansion of TPLF is wrong and it should be corrected. Wolqait will not be part of Tigrai unless the fascists kill all Amharas. Besides all should stand together on this issue because it is unjust and we all should stand for truth and justice.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
Copyright © 2026 · Goolgule