
በምድራችን ላይ የሚደረጉት ነገሮች በጊዜ፤ በሚፈጸምባቸውና በሚፈጽሙት ሰዎች ይለያዩ እንጅ፤ ድግግሞሽ ናቸው። ባህታዊ አምኃ ኢየሱስ በወያኔ መንግሥት በተበደለው በጎንደር ህዝብ መካከል ቆመው ያሰሙን ድምጽ፤ በጣሊያን ወረራ ጊዜ እነመምህር ገብረ ኢየሱስ ላሰሙት ድምጽ ድጋሚ ነው። ወያኔ በወገን በአገር ላይ የሚፈጽመውን ግፍና መከራ በዝምታ በማለፍ ላይ ያላችሁ፤ ከህዝብ ጋራ አለመታየትን የመረጣችሁ ካህናት ሰባክያንና ጳጳሳትም፤ በጣሊያን ጊዜ ጣሊያንን ላለመስቀየም ዝም ያሉትንና ከህዝብ መካከል የተደበቁትን የካህናትን ዝምታ ደገማችሁ። የተደገመ ነው ብልም፤ ወያኔዎች በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚፈጽሙት መከራና ግፍ፤ ጣሊያኖች ከፈጸሙት መከራና ስቃይ ጋራ ስናነጻጽረው፤ ወያኔዎች የፈጸሙት ከተመሳሳይነቱ እጅግ የራቀ፤ የባሰና የከፋ እንደሆነ፤ በዚህ ዘመን ዝም ያላችሁትንና፤ ከህዝብ መካከል የተደበቃችሁትን ካህናት፤ በጣሊያን ጊዜ ዝም ካሉትና ከህዝብ ከተደበቁት ካህናት እጅግ በጣም የከፋችሁና የባሳችሁ ናችሁ። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply