• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ይድረስ ለእኛ—ከእኛ!

August 11, 2016 04:01 am by Editor 1 Comment

ይድረስ ለእኛ-ከእኛ! – ከላይ ልጀምር ካ’ናቱ፣
በብረት ኃይል ተከቦ – ከተኮፈሰው በከንቱ፣
ይድረስልኝማ ለወያኔ – ለጊዜያዊው ባለጉልበቱ፤

… “ለሕዝባዊነት መጣሁ” ብሎ – ሕዝብን በጥይት መቁላት የለምና፣
አቆልቁለህ እየውማ – የምትሄድበትን ጎዳና!
የጭካኔ መጠንህ ጫፍ ደረሰ – የውሸት ቋትህ ሞላ፣
የ’እውቀት‘ ገደብህ አበቃ – ከእንግዲህ ላይኖርህ የቀረ ‘መላ’፣
ከወደቁ ወዲያ መንፈራገጥ.. እንዳይሆን ለመላላጥ፣
ሳሩንም ላለመጋጥ.. መሬቱንም ላለመናጥ…፣
ከአውሬነት ባህል ተላቆ – ሰውነትን ይሻልና፣
ይድረስ! ይድረስ! እልሃለሁ፤ ይድረስ! እንደገና፤
ዛሬ እንኳን እንደማመጥ – ይቅርብህማ ወንድሜ፣
በግፍ ተሞልተህ ጉዞ – ላይሆንህ መልካም ዕድሜ፣
“አበቅቴ ውሉን ሳይስት” – የአመሻሽ ጀንበር ሳትጠልቅብህ፣
ቆም ብለህ ማሰብ ጀምር – እንደ “ጆቤ”ህ፣ እንደ “ፃድቃን”ህ!

ይድረስ ለወንድማችን! የወገንህን ስቃይ ለምታራዝም፣
አውቀህም ሆነ፣ ሳታውቅ  – ለጥቃቅን ጥቅማ-ጥቅም፣
ለሀላፊና ጠፊ  – አብሮህ ለማይኖር  ቁስ፣
ህሊናህን ለምትዳርግ  – ለማይድን የጸጸት ውርስ፣
ለዘር ማንዘርህ ‘ለሚተርፍ‘ የስም ስብራት “ቅርስ”፤

ይድረስ ለእህታችን! የወገንሽን ጭንቅ ለምታበዢ፣
አውቀሽ እንደዘበት፣ ሳታውቂ  በስህተት ለምትናውዢ፣
በልጦ ለመገኘት፣  በምትከውኚው ድርጊት-ሃላፊ፣
የማያልፍ ክፉ ስም ተክለሽ  – ሳትጠቀሚ ለምታልፊ፣
የትውልድ እናት ሆነሽ  – የስምሽን ክብር ለምታጎድፊ፤

ይድረስ ለእኛ-ከእኛ!
ሕዝብ በመዶሻ ሲቀጠቀጥ፣ ምስማር ለምናቀብል ከንቱ፣
የዘረኝነት አጥሩን ሲያጥር፣ ማገር ለሆንን ለስርዓቱ፣
የጭቆና መረቡን ሲዘረጋ፣ እየተጋገዝን ለምንተበትብ፣
አስተዋጽዖ ለምናደርግ፣ ለከፋፍለህ ስልቱ ግብ፤
ለ”ልማታዊ መንግስት” ፌዝ፣ ለዘረኝነት “ፌዴራሊዝም”፤
ኃይል፣ ጉልበት ሆነን፣ እድሜውን ለምናራዝም፤

በ”ላም አለኝ በሰማይ..ቤት”፣ በአፓርትመንት ተስፋ፣
ዶላር ለምናፈስለት፣  ጨቋኝ እንዲደልብ፣ እንዲፋፋ፣

ይድረስ ለእኛ!
በመሃላ፣ በጩኸት..፣ ባደባባይ፣
“ክርስቲያን” ነኝ፣ “ሙስሊም” ነኝ ባይ፣
በማዕረግና ቅጽል ብዛት አይደለም እምነቱ፣
በቂምና በሸፍጥ አይደለም ስግደት፣ ጸሎቱ፤
መስጂድ፣ ቤተ-ክርስቲያን.. እምናምስ፣
የመለኮት ጸጋ ማደሪያውን እምናረክስ፣
በኢ-አማኝ መሰሪዎች ሴራ፣ ጽላተ-ታቦቱን እምንከስ፣
የእምነት መሰረተ-ስርዓቱን፣ ዶግማ-ቀኖና እምናፈርስ፣
መቅሰፍት መጥራት ነው በራስ፣ ቅስፈት መመኘት ነው ለሀገር፣
የዘላለም ዓለም እሳት፣ እማይበርድ የሲዖል ጣር፤

ይድረስ ለእኛ!
“መሬት እሰጣችኋለሁ..” ሲል፣ በካሬ ሜትር መትሮ፣
ከየት አምጥቶ? ብለን ብንጠይቅ፣ ባለቤቱን በግፍ አባሮ፤
ከጉልበተኞች ተጠግቶ — ተገን የሌለውን ደሀ ገፍቶ፣
የሚያለቅሱ ህጻናትን እምባ — በግፍ ረግጦ የተገነባ፣
በሞራል፣ በህግም፣ በኃይማኖት — ከቀማኛ ሌባ ተሻርኮ መብላት፣
ያስጠይቃል ጊዜው ሲደርስ  — ሀገር ለባለሀገሩ ሲመለስ፤
ከስማችንም፣ ከገንዘባችንም ሳንሆን በከንቱ እንዳንቀር፣
እናም ጎበዝ! እናስብበት፣ ጊዜው ሳያልፍ እንምከር።

ይድረስ ለእኛ!
ሳይማር ላስተማረን — ወርቅ፣ አልማዝ ላበደረን፣
ምላሻችን አይሁን ጠጠር  —  የበላንበትን ወጭት አንስበር፤
ለፍትህ፣..ለነጻነቱ፣ ሕዝብ የሚያደርገውን ወሳኝ ትግል፣
በአእምሮ ድህነት ተጠፍረን፣ ማገዝ እንኳን ባንችል፣
እኛ ከዋናው ጠላቱ ብሰን፣ ጉሮሮው ላይ አጥንት አንሰንቅር፤
የፈሪ ዱላችንን እንደታቀፍን፣ ባይሆን “መሃል እንስፈር”፤
የ”እሱ” ክፋት መች አነሰና፣ ሀገር እሚያቃጥል በሰበብ-አስባብ፣
ለእሳት ቤንዚን ከማቀበል፣ ከእኩይ ተግባር እንታቀብ፤
ማስጣል እንኳ ቢያቅተን፣ የጊዜ ምስጢር ዘማ፣
በ”ያባትህ ቤት ሲዘረፍ..” ብሂል፣ አገራችንን አናድማ!

ይድረስ ለእኛ!
አመንዣጊ ለሆንን እንደ ጌኛ፣
በሆዳችን ለምናስብ፣
ለማይመስለን በልተን እምንጠግብ፤
ከረሃብተኛ ጉሮሮ ነጥቀን፣  በጠኔ ከደከመ ጨቅላ፣
ህሊናችንን ሸፍነን፣ ሆዳችንን ለምንሞላ፣
በዛሬ ብቻ “አስረሽ-ምችው”፣ የትውልዱን ነገ ለምናጨልም፣
ትርፍራፊያችን እንኳ እንዳይቀር፣ በክፋት ለውሰን ለምናወድም፤

ይድረስ ለእኛ!
ውጭም ሆነ-ውስጥም ላለን፣
ለቅንጥብጣቢ ስጋ፣ እንደውሻ ለሚጣልልን፣
ከደሀ አፍ ተነጥቆ፣ ዳረጎት ለሚሰፈርልን፣
ለደረቅ ፍርፋሪ እንጀራ፣ ተበልቶም ለማያጠረቃ፣
በወገን ቁስል ላይ፣ እንጨት መስደድ ያብቃ!

ይድረስ  ለእኛ – ከእኛ!  – “እኛና -እናንተ” ሳንባባል፣
ይልቁንስ በጋራ እናፍልቅ ላገራችን መድኅን ፀበል!!

ነሐሴ 2008 ዓ/ም
(ኦገስት 2016)

(ይህ ግጥም ከሁለት ዓመታት በፊት የተሰራጨ ሲሆን፣ ጥቂት ስንኞች ተጨምረውበት ዳግም የቀረበ ነው።)

Filed Under: Literature Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. tazabiw says

    August 13, 2016 07:31 pm at 7:31 pm

    Dear Getch
    i am very proud to know you and to call you my friend.
    i read it and it is true!!!
    we have to comeback to our senses and join the struggle to get rid of the Woyane Junta!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule